#ሰንበትን #ለመጠያዬቅ። #ኦባንግሻ የት ነው ያለኽው?
#ሰንበትን #ለመጠያዬቅ ። #ኦባንግሻ የት ነው ያለኽው? ባለህበት እግዚአብሄር ይጠብቅህ። አሜን። "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሌሎች የሰብአዊ መብት ሞጋቾቼ ቀጣይ ተሰጣቸው ዕድል ለአንተ #ተነፈገ ወይንስ #ፈቅደህው ይሆን??? እነሱስ ስለምን ዝም አሉ። ብቻ የሰላም ያድርገው። አሜን። #ምዕራፍ ፲፯ አንተ ብርቱ የሰላም ወዳጅ፤ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ፤ የኢትዮጵያዊነት #ዘብ #አደር አቶ ኦባንግ ሜቶ የት ነው ያለኽው? #በህይወት አለህን? ጤንነትህ #ደህና ነው ወይ? ትዳርህ ተሳካን? ግን እንዴት አለህልኝ የምር ወዳጄ ኦባንግሻ??? አማኑኤል አባቴ ይጠብቅህ። አሜን። የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችህን ኤክሱን እና ፌቡ አልፎ አልፎ መልዕክት ከፃፍክ ብዬ እጎበኛቸዋለሁኝ። ትንሽም #ፍንጭ የሚሰጥ ነገር አላገኜሁም። በቃ! ኦባንግሻ የአንተ ታሪክ በዚህ መልኩ ቄሱም፤ መጸሐፋም #በዝምታ ይቋጭን??? ለነገሩ ኮነሬል ጎሹ ወልዴስ የት ናቸው። ስለ ክቡርነታቸውም ሰምቼ አላውቅም። ኢትዮጵያ እንደገቡ ደማቅ፤ ክብራቸውን የመጠነ አቀባበል በቤተ መንግሥት መደረጉን አይቼ ነበር። ከዛ በኋላ ግን??? ወፍ ዜና ነጋሪ የለም። ወይ አጋጣሚ እነ ማህበረ - ሌንጮ ስኮዬር፤ ዶር ዲማ ነገዕወ በፓርላማ በሚንጎባለሉበት ዘመን፤ እነ አቶ ዳውድ ኢብሳ ያሻቸውን ባሻቸው ሰዓት በሚናገሩበት ዘመን፤ እነ አቶ ስብኃት ነጋ በክብር ወደ አሜሪካ ተልከው የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንደ አሻቸው ሲያምሱት፤ ሲያተራምሱት እያዬንም ነው። ከሳቸው ምን ብጣቂ #ርህራሄ ይገኛል ተብሎ የክብካቤ ሞዝቦልድ እንደ ተሰናዳ ባይገባኝም። የጭ...