መረጃ በወቅቱ ካልቀረበ ይፋድሳል፤ ዕሴቱንም ይቀንሳል፤ በሌላ በኩል አንድ ሥርዓተ #መንግሥት ሥርዓትን መፍቀድ ግዴታው ነው።
መረጃ በወቅቱ ካልቀረበ ይፋድሳል፤ ዕሴቱንም ይቀንሳል፤ በሌላ በኩል አንድ ሥርዓተ #መንግሥት ሥርዓትን መፍቀድ ግዴታው ነው። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" #ምዕራፍ ፲፰። #እፍታ ። የዶክተር ገዱ ምስክርነት እና የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የመስካሪ ፈላጊ ሂደት ምን ያመሳጥርልናል? #ተመክሮዬ ። እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። አንድ ጭብጥ በጣም ሲገርመኝ ሰነበተ። የእኔ የህይወት ተመክሮ የፖለቲካ ፓርቲ ቋሚ እና መደበኛ ሠራተኛ ስለነበርኩኝ ድርጅቴ ኢሠፓ ለተልዕኮ ሲያሰማራኝ ከቡድን መሪ፤ የቡድን ጸሐፊ ጋር ነበር። በተጨማሪም እራሳቸውን ችለው የሚጓዙ ቲሞች ከኖሩም ከፖለቲካ ድርጅቱ በቀጥታ አመራር የሚያገኙ ወደ ተግባር ከመሰማራታቸው በፊት ወጥ የሆነ የተልዕኮ አቅጣጫ ይሰጣቸዋል። ከተልዕኮ መልስም ሪፖርት ማቅረብ ግዴታቸው ነው። የአቅም ማኔጅመንት የሚታቀደው፤ የሚፈጸመው ከጉዞው #ግብረ መልስ ይሆናል። እኔ የቡድን መሪ ሆንኩኝ፤ ወይንም ሌላ የቡድን መሪ ኖረኝ የማይጓደልበት የዲስፕሊን መርኽ ድርጅቴ ኢሠፓ ነበረው። ለዚህ ነው እኔ የፖለቲካ ፓርቲዬ ኢሠፓ መራራ ስንብት ካደረገ በኋላ በድንግልናዬ የቀጠልኩት። እንኳንስ ፓርቲ የሆነ ተቋም አባልም፤ አካልም መሆን እማልፈቄደው የተፈጠርኩበት ድርጅቴ የፖለቲካ ዲስፕሊኑ፤ ተመክሮው፤ እኛን የቀረጸበት መንገዱ አንቱ ነበር። ከጠቀመ ላጋራችሁ ፈቀድኩኝ። 1) እኛ ለተልዕኮ ስንላክ የተልዕኳችን አጠቃላይ መንፈስ #ይነገረናል ። ሁላችንም በተልዕኳችን ላይ #እኩል ግንዛቤ እንዲኖረን የወል ማብራሪ...