ልጥፎች

«ሚስጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም።»

  «ሚስጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም።» ራሺያ በእኩል ኢትዮኤርትራን #ከውስጥ ታቀርባለች። ሚስጢር ነው። #ለፈላስፊት ኢትዮጵያ ለመሰጠቷ፤ ለብቃት ልዕልናዋ፤ ለልቀት ቅብዓዋ የመንፈስ ዘቢደሯ ነኝ።   "አቤቱ ልቤ አይታበይብኝ።" አሜን እላለሁኝ። እኔው።   (መዝሙር ምዕራፍ ፻፴ ቁጥር ፩)   • «ሩሲያ በኢትዮጵያ እና ኤርትራን መካከል 'ታማኝ' አደራዳሪ መሆን ትችላለች? ለምንስ ማደራደር ፈለገች?»   https://www.bbc.com/amharic/articles/cwd09rr212mmo   #ምዕራፍ ፳።   ራሺያ ሊቃናቶቿ፤ መሪዋ፤ ህዝቡም ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ አገራት እና ህዝቦች ቀና ልቦና አላቸው። ከውስጣቸው እንደሚያቀርቡን አውቃለሁኝ። በስደትም የቤተሰብ ያህል ነው እኔን የሚገጥመኝ።    #ለምን ?    "ሚስጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም።" ይላሉ ባለቅኔ ጎንደሮቹ። በኢትዮጵያም ይሁን በኤርትራ በኩል ለራሽያ ያለው የቅርበት ሁኔታ እንደ መሪወቹ ሊለያይ ይችላል። ራሺያወች ግን ለሁለቱም እኩል አክብሮት፤ እኩል ወዳጅነት አላቸው።   በኢትዮጵያ የብልጽግና ሹማምንቶች ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የሚበልጡባቸው ሌሎች አገሮች እንደሚኖሩ አስባለሁኝ። ቅድሚያ የሚሰጣቸው፤ በአቀባበል ይሁን በትኩረት የበለጠ ክብር የሚሰጣቸው እንዳሉ ይሰማኛል።   በማንኛው የመንግሥት እርምጃወች ዘንድ ማን ይከፋል? ማን ደስ ይለዋል? ተብሎ እንደሚተመን ይገባኛል። ይህም ሆኖ የራሽያ ሊቃናት፤ የራሺያ መሪወች፤ ፕሬዚዳንት ፑቲን፤ ህዝቡ ሁሉም ለእኛ የውስጥ የሆነ ውስጥነት አላቸው። ለምን? #ሚስጢር ነው።   #ድርድር እና ስኬቱ በግምቱ - በስሱ።  ...

ነገረ አርቲስት አንተነህ ትኽርቁ።

  #ዕንባ ሲሳነው። ዕንባ #በቃሽኝ ብሎ አፋጠጠኝ። ይገባዋልም። #ስንት እኛወች አለን???? https://www.youtube.com/watch?v=L_8wH3-eBTU «አርቲስቱ በወልቂጤ ከተማ በግፍ ተገደለ #rip #antenehe #ethiopiamovie #seyfufantahun » • ድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ እናቶች ያለ ሃይማኖት ልዩነት በወል ሱባኤ ቢገቡ። ፈጣሪን ቢለምኑ። • አላሃቸውን ቢማጸኑ የሚል ሃሳብ በትህትናና አቀርባላቸዋለሁኝ። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውልም።" ዛሬ ዕውን ሆኖ ያጋጠመኝ ክስተት ነው። #ምዕራፍ ፳። የዕንባ ጠብታ የቁስለት ጠብታ የምሬት ጠብታ እኔን እያማታ ዕንባው እና ማታ ለመነ ምህረትን ሳያመነ ---- ታታ ---- ታታ። #ዛሬ ልዩ ቀኔ ነው። ማስተዋልን ከተሰጠኝ በላይ እንዳስተውል የሆንኩበት ዕለት። #ውስጤ ለውስጤ ጥያቄው እና መልሱ። ዛሬ ቀጠሮ ነበረኝ - ከሰዓት። ግን ማስተዋልን የበለጠ እንዳስተውል የእዮር ስጦታን አገኜሁኝ። በዝምታ ለማሳለፍ ወስኜ ነበር። ፌስቡክም ላለመግባት። ብሎጌንም ላለመጎብኜት። #ልለምናችሁ ። እናንተም እሺ በሉኝ እባካችሁን? ግን ደህና አደራችሁን ማህበረ ቅንነት። የጥዋት ጉዳዬን ከውኜ ዜና ፍለጋ ላይ እያለሁ ሌላ ገጠመኝን አስተናገድኩኝ። ማህበረ ቅንነት እኔን ጨምሮ ብዙ የተጎዱ ነፍሶች፤ የታመቀ ሃዘናቸውን ዋጥ አድርገው የያዙ በቤታችን ቤተኞች አሉ። ዕንባማ ወገኖቻችን ለካ አብረውን አሉ። ይገኛሉ። ስለሆነም በምንጽፈው፤ በምንሞግተው ሃሳብ ላይ ብርቱ #ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል። የጽናት የውሃ ልክ የሆኑ ቤተኞቻችን አሉ። በህመማቸው ላይ ሌላ መከራ አንጫንባቸው። አደራ። ያው ፔጃችን ከፎቶ ላይ ኤክስ አይፈቀድም። ስድብም ፈ...

ሕጻናትን

  «አርሲ ውስጥ ባለፉት ዓመታት በተፈፀሙ ጥቃቶች ብዙ ሰዎች የተገደሉባቸው የትኞቹ ናቸው?» BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/c8r4y50vdrdqo «በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ አደረጃጀት በደቡብ ምሥራቅ ዞን ሥር በተካተተው የቀድሞው አርሲ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተፈፅመዋል።   በዋናነት ማንነት እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ እንደሆኑ የሚነግርላቸው እነዚህ ጥቃቶች አሁንም የቀጠሉ ሲሆን የብዙ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፈዋል። በተጨማሪም በርካቶች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው፣ አስገድዶ መሰወር፣ መፈናቀል እና ከፍተኛ የንብረት ውድመትም አስከትለዋል።   በአካባቢው በሚኖሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀመው ማንነት ተኮር ጥቃት በ2014 ዓ. ም. መጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል። ከ2016 ዓ. ም. ወዲህ ደግሞ ጥቃቱ ተባብሶ መቀጠሉን ኢሰመጉ በዚሁ የምርመራ ሪፖርቱ ገልጿል።   ከ2014 ዓ. ም. ጀምሮ እስካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ድረስ ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ በአርሲ በተፈፀሙት ጥቃቶች "458 ሰዎች" ሲገደሉ፤ "38 ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ በሥፍራው ባለሙያዎችን አሰማርቶ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ኢሰመጉ አስታውቋል።   ይህ ሪፖርት ይፋ ከሆነ በኋላም የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፉ መሰል ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተፈፅመዋል። ከ2016 ጀምሮ የተፈፀሙትን ዋና ዋና ጥቃቶች በዚህ ዘገባ ዳስሰናል።»   • «ጥቅምት 2019 ዓ. ም. «   «በሽርካ ወረዳ በሳምንት ልዩነት ውስጥ በተፈጸመ አዲስ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሕጻናትን ጨም...

ቅዱስ #ሲኖዶስ ሆይ!

  ቅዱስ #ሲኖዶስ ሆይ! የት ይሆን #ያለህው ? ግን አለህን? መኖርህን #አሳዬን እባክህን?   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ምዕራፍ ፳።   አዳሩ አደርን ብቻ እንበለው ---- ይሆን? የሰው ልጅ #ቄራ በተከፈተባት ምድር ----- ተፈጥረን፤ መያዣ መጨበጫው #መሰገጫው ----- ጠፍቶብን የመፈጠራችን ምክንያት እንዲህም፤ እንዲያም -----ሾላልኮብን፤ ተንጠፍጥፈን ተንቃረን --- አንቃረርን። በሰው ለሰው #ጥፋት ፍርስራሽ -----ተጠምደን በቁም ሰው #እያፈረስን ላለነው ኡኡ! እንበል አልን ሰሚ ቢገኝ አንገጠን እየ ------ ጠበቅን። የጃራ መንፈስ ጥዶ አንገርግቦ እንሆ ቆላላን እምስ አደረገን አማስን ፈጀን በቋያ --- በወበቅ ---- ፈጃጀን የርግማን ናዳ የምርቃት መነሳትን በውን አየን። ………ሰማዕታቱን በምሬት ተሰናበትን ህፃናቱ በመፏለያቸው ጊዜ፤ እንደ አነቡ አለፋ ጊዜያቸውን ጥለው መጭ አሉ -----//// አፈር ተላብሰው ወደ ጉድጓድ ሄዱ እንደ ደረሱ ምን አሉ? ምንስ ቢሉ? እና ------ ፍሉ ገረፈን እንቅልፍ ገፎ ሰላም ነሳን ነገ አሮ #ሃራም ታጥቆ ተስሎ - እየጠበቀን መቼ #ተማርን ? ብቻ ግንስ ለግን ……… ለእኛ ለዕብኖች ወዮልን? ኢትዮጵያ አገሬም ጠጪው #ወዮልሽን ? ዕቃ የጠፋብሽ የማይመስልሽ አገሬ ሆይ! የሞት፤ የሃዘን፤ የሰው አጨዳ #አና ብሎ እንደ ሲሳይ ወዮ! ለአንቺ ዛሬም ብግነት - ነገም ብክለት የርህርህና --- ልግመት የተዋህዶ ግላይ፤ የቆሰለ በመገፋት ይዬው፤ ይዳኜው -------/////--------ይፍረደው -----ከላይ። ወዮ! ለአንቺ ኢትዮጵያ ነገ ንዴት ተጎንጭቶ፤ ማግሥት በኮሶ ተጠቅልሎ፤ በቀራንዮ ተቁላልቶ ወዮ! ለአንቺ መጪው ቀናት ማት አርግዞ ተፋጅቶ፤ ዕልቂት ነግሶ ምንጣሮን -...