አክብሮት የፍቅር ተፈጥሮ እንደምን ሊሆን ቻለ?

አክብሮት የፍቅር ተፈጥሮ እንደምን ሊሆን ቻለ? #በርግጥም አክብሮት የፍቅር ተፈጥሮ አካል ነው። #ስትወደው ታከብረዋለህ። #ስትወደው ትንከባከበዋለህ ያከበርከውን ሰብዕና፤ ማህበረሰብ፤ ተቋም አመክንዮም። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ" ** መነሻ በር። አቨይ አባቴ መምህር እና የቤተ መፃህፍት ሰው ነበር። የዝምታ ንጉሥ ነበር። የአበይን የበቃ ሳቅ አይቼ አላውቅም። የበሞቴ ልዕልቴ የእሽታ ንግሥቴ የእቭዬ ሰብዕና ደግሞ ጠሐይ ነው። ሳቂተኛ ናት። እንዲያውም እናቷ ጢጢዬ አፍሽ የሰፋው ከሳቅ ብዛት ነው ትላታለች። እኔም የሁለቱን አጣምሬ ይዣለሁኝ። ያልሳቅኩበት ፎቶ የለም። ከልቤ ከሆነ ጎረቤቶቼ አብዛኛውን ጊዜ እረፍት ሄዳለች ብለው ስለሚያስቡ ከሩሜ የፀጥታ ግርማ ብዛት፦ ሳቄን ስለቀው ደግሞ ያን ያህል አውዳቸውን አለች ያሰኛቸዋል። ድሮ ድሮ በሩቅ ሰው ሳይ እስቅ ነበር። ዛሬ ዘመኑ አስተማረኝ። ወደ ፍቅር ተፈጥሮም እንዳዘነብል ዬረዳኝ ይኽው ነው። ድሮ ባቡር ውስጥ ሆነ አውቶብስ ውስጥ ባዶ ቦታ ካገኜሁ አስፈቅጄ መቀመጥ ነበር። ዛሬ እንደዛ ዬለም። ሰው የሌለበት ወንበር ፈልጌ እቀመጣለሁኝ። የእኛ ቀለም ያላቸው ሁሉ ዕይታቸው ያስፈራል። አያስጠጋም። ይገፈትራል። ልጅ እያለን እናታችን "እጃችሁን ዘርጉ" ትለናለች። እንዘረጋለን። ከዛ "ጣታችሁን እዩ" ትለናለች። እናውቀዋለን እንላለን። "አታውቁትም" እዩት ትለናለች። እሺ ብለን መዳፋችን አገላብጠን እናያለን። ከዛ "ምን አያችሁ ብላ ትጠይቀናለች።" ጣት መዳፍ እንላታለን። ሌላስ ሌላ ምንም እንላታለን። ወይ ቀድማ የነገረችን እናስታውሳታለን። እሷ ጣቶቻችን እያሻሸች ትንሽ እጣ የቀለበት እጣት ጠቋሚ እጣት አውራ እጣ የሚዛን እ...