ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም የፖለቲካ እስረኛ እንዳይኖር ጽኑ ምኞቴ ነው። ሳልሞት ይህን ባይ፤ እረፍቴ ሰላምን ሰንቆ በሆነ ነበር።
#ኑሩልን ። አሜን። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #አይዟችሁ ! እንደሚናፍቃችሁ አውቃለሁኝ እኔም ካቴናውን አውቀዋለሁና፤ #መጽናናትም እንደሚናፍቃችሁ አውቃለሁኝ በዘወትር የፈተና ቡፌ አስተናግጃለሁና፤ ከቤተሰብ ጋር #አፍላፍ ገጥሞ ፍቅርን መኮምኮሙ ሽው ሊላችሁ ይችላል፤ የናፍቆትን ወጀባዊ #ግርፊያ አውቀዋለሁና፤ ጠሐዮዋ #ብርቅ ልትሆንባችሁ ትችላለች፤ የቁም እስረኝነቱንም የመኖሬ መልክ ነውና፤ እናትን #እቅፍ አድርጎ መሳም፤ ውስጥን ገልጦ ማሳየት ትዝ ሊላችሁ ይችላል፤ መከራውን አውቀዋለሁና፤ #ወገኖቼ ሆይ! ጽናታችሁ፤ ብርታታችሁ፤ ጥንካሬያችሁ ይገርመኛል። በተለይ በዘመነ ህወሃትም እስረኛ እንደ ነበሩት እንደ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፤ እንደ አባት ጸሐፊ ታዲዮስ ታንቱ ዓይነት አሳር የማያልፈው ግን በተፈጠረበት ልክ ለመቆም፤ ለመዝለቅ የቆረጠ ሰብዕና ይመስጠኛል። እራስን ጎድቶ መኖር ብዙም የማይፈቀድለት ገጠመኝ ነው። እናንተ ግን ኖራችሁበት። ቤተሰብም ተጎዳ። #ኢትዮጵያስ ምን ትላለች? #አለች አይደል፤ እራሷ ትመልሰው። እኔ ፈላስፊትኢትዮጵያ በግርማ ሞገሷ፤ በማዕረጓ ልክ፤ በአቅሟ በተፈጠረችበት miracle ኦርጋኒክ ተፈጥሮ ልክ አለች ብዬ አምናለሁኝ። መናድን ለሚመኙ፤ ስብራቷ ለሚናፍቃቸው አሻም ያለው እዮራዊ ሽልማቷ ነውና። አወን ኢትዮጵያ አለች። ለልጆቿ ሙሉ የመኖር ነፃነት የመገብ አቅም በፖለቲካ ሊቃናቷ በመሆኑ እንደ እናት፤ እንደ እምዬ ለመሆን #ዘመን ፈተናት። #ብቻ ብቻ …… አይዟችሁ! ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። ለቤተሰቦቻችሁ ስንቅ ለማቀበል በማይቆጠቡ፤ አቅም፤ ጥንካሬ ፈጣሪ ይሰጥ ዘንድ እመኛለሁኝ። #ቸር ዜና...