የአካዳሚ ነፃነት የትውልድ አውንታዊ ብቅል ነው!
እንኳን ደህና መጡልኝ መ ሠ ረት። „የፃድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ የፃድቅናንን መንገድ ታቃናለህ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ Seregute©Selassie 14.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። · እ ፍታ። እንዴት አመሻችሁ ውዶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ይህቺ እንደነፍሴ የምወዳት አገር እምዝምታ ሲዊዝሻ ጸጥታውን እዬመገበችኝ ነፍሴን ታፍነሽንሸኛለች። እኔ ግርግር ጩኽት - ሁካታ- የአገር ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አልፈቅደውም /ሰላማዊ ስልፉ/። ድምጽ የባዘበት ቦታ ይጨንቀኛል። አንድም ከቤቴ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማ ነገር የለም። እቃ ሲታጠብ በጸጥታ፤ በር ሲከፈትም ሲዘጋም በዝግታ ነው። ራሱ ጎረቤቶቼ ስለመኖሬ ወይንም ስላለመኖሬ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም። ጸጥ ረጭ። እናላችሁ ሲዊዚሻን ሳስባት ለእኔ ተብላ የተፈጠረች ይመስለኛል። አብሶ እኔ ያለሁበት ቪኒቲ። ቪንቲ የቁልምጥ ስሙ ነው። ከዚህ ከተማ የተፈጠሩትም የገጠሙኝ ሁሉ ቤተሰብዐው ስብዕና ያላቸው ናቸው። ይህችን እንደ ወግ ቢጤ ካደርኩኝ ስለዛሬው ቁም ነገር ልንገራችሁ … ትውልድ። · ትውልድ። ትንተና የለውም እንዲሁ በመደዴው ስሄድበት ግን ትውልድ በመኖር ውስጥ ያለ የአገር መኖር ማለት ነው። አገር ለማኖር ደግሞ የትውልድ መኖር ብቻውን በቂ ነው ሲባል ጥማድ በሬ ገዝቶ ማሳ የሌለው ገበሬ ይሆናል። እና የትውልዱ መኖር መበራከት ብቻውን አገርን የማስቀጥል አቅም ሊኖረው አይችለም። ማሳው በበጎ በፈቃደኝነት፤ በባለቤትንት፤ በታማኝነት፤ በምክንያታዊነት መታ...