የኦነግን ዓላማ ለመሸከም አቅም የለንም። አቅም ለማዋጣትም አንፈቅድም!
እንኳን ደህና መጣችሁልኝ ምርመራ። ክፍል አንድ። „እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“ መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ይህ የኦሮማማ አይዲኦሎጂ ትርፍ ነው ። ውዶቼ ክብረቶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? የበታችነት ባይረስ ፋሽታዊ ዕሳቤን እንደሚወልድ አሁን እያስተዋልኩኝ ነው። ፋሽታዊነት መንፈሱን የሚመራው መርህ ጥላቻ ነው። ጥላቻ ደግሞ የመንፈስ ሪህ ነው። ሥነ - ልቦናንም ያደቃል። ጠቡ ከሰውኛ ተፈጥሮ እና ስኬት ጋር ስለሆነ። ይህ የመንፈስ ሪህ ለመፈወስ ደግሞ አላዛሯ ኢትዮጵያ መንገዱን ገና አልጀመረችውም። እርግጥ ነው ቀደም ባለው ዶር አብይ አህመድ የፈላስማው ዶር ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ከዶር ምህረት ደበበ ጋር ማይንድ ሴት ላይ አብረው ይሰሩ ነበር። እኔም የዶር አብይን መንፈስ የተዋወቅኩት በዚህ መስመር የፍቅራዊነት እንቡጢጣ ፕሮጀክቴን ስሰራ አፍሪካ ላይ ምን በመከናወን ላይ እንዳለ ሳስ ነው ያገኘኋቸው። ዶር አብይ አህመድ በፖለቲካው መድረክ ጎላ ብለው ከመውጣታቸው በፊት ሲወገዙ ፊት ለፊት ወጥቼ ለመሞገት ያስቻለኝም ያ የቆዬ ጥሪት ስለነበ...