አጤ አስቻለው ፈጠነ (Ardi) ተከድኖ የቆዬውን ትንፋሽዋ ጎንደር ቃና የሙዚቃ ቅኝት ገለጠ። ለእኔ ሙዚቃ ብቻ አይደለም ፍልስፍናም ጭምር።
አጤ አስቻለው ፈጠነ (Ardi) ተከድኖ የቆዬውን ትንፋሽዋ ጎንደር ቃና የሙዚቃ ቅኝት ገለጠ። ለእኔ ሙዚቃ ብቻ አይደለም ፍልስፍናም ጭምር። ዬእኔ ድንግል ትጠብቅልኝ። አሜን። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።" • https://www.youtube.com/watch?v=RRqTpYYb7d4 እናትዋ ጎንደር | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video) | SewMehon Films #በር ። በሙዚቃ ጥበብ ዘርፍ ቅባአው የለኝም። ለፀጋዬ ራዲዮ ራሱ የተፈጥሮ ሙዚቃወችን ነበር እምጠቀመው። ጓደኞቼ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ይዘውልኝ ይመጣሉ። ዬመሳሪያ ቅኝቱ ይሻለኛል። በሥሜ ሙዚቃ ሲወጣም ሥራዬ ብለው ጓደኞቼ አዳምጠው ዘንድ ይጋብዙኛል። የቅኔው ዕንቡጥ ዶር ቴወድሮስ ካሳሁን ሰብልዬን ሲያመሳጥር አልሰማሁም ነበር። ጓደኞቼ ጋብዘው አስደመጡኝ። ደካማ ነኝ። አቅጄ ሙዚቃ ከፍቼ አዳምጬ አላውቅም። ያለ ፀጋው አይሆንም። እኔ የወንዝ ዬወራጅ የፏፏቴ የዝናብ የእንሰሳት የእጽዋት ሹክሹክታ እና ዝማሬ ይመስጠኛል። ገንዘብ አውጥቼም እገዛለሁኝ። የዝናብ እራሱ እወዳለሁ። የሳተ ጎመራ ላርባ ጎርፍን ማዬትም ያስደስተኛል። ብቻ ፈንገጥ ያሉ ፍላጎቶች አሉኝ። ባባቴም በአበይ፤ በእናቴም በእብዬ ወገን ቤተ ክህነታዊ ቢሆኑም አበይ የመፀሐፍ ንባብ ላይ፤ በፍልስፍና ኩነት፤ በዝምታ ተፈጥሮ ዬሰከነ ነበር። እናቴ ደግሞ በፍልቅልቅ ሳቂታ በሞድ እና በሙዚቃ ጥበብ የተመሰጠች ነበረች። ከሁለቱም ለተፈጥሮዬ የተፈቀደልኝን ወስጃለሁኝ። #ፏ ። በኢትዮጵያ ዬቤተክርስትያን ዬዝማሬ ቅኝት አራራት፤ ግእዝ እና ዕዝል ፀጋወቻችን በቅዱስ ያሬድ ተፈጠሩ። መንዙማም በእስልምና። ለነፍስ፤ ለመንፈሥ ትፍስህት። ለስጋ ለጋህዱ ዓለም መኖር ደግሞ አንች ሆ...