#በጥሞና መመርመር
ለአቶ ተላይ ገብሩ ያለኝን አክብሮትም በትህትና እገልፃለሁኝ። ከአቶ ተላይ ገብሩ ፔጅ የተገኜውን አቶ ውብሸት ያጋሩት ነው ሙሉውን እኔው ያጋራሁት። #በጥሞና መመርመር ስለምፈልግ ነው ሼር ያደረኩት። ዳታ አለው። በማዕከላዊ ጎንደር ከ80 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ሲኖር አማንያን መጎዳታቸውም ታሳቢ ቢደረግ እላለሁኝ። /////======//// 1. "ነሐሴ 2010 ዓ.ም. — ጅግጅጋ፣ ሶማሌ ክልል፦ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፤ ካህናትና ምዕመናን በመሰዊያው ፊት በግፍ ተገደሉ፤ ንዋየ ቅድሳት ተዘረፉ፤ ምዕመናንም ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቀሉ። 2. ሐምሌ 2011 ዓ.ም. — ሲዳማ፦ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፤ ካህንና ምዕመናን ተገደሉ፤ ነዋሪዎችም ተፈናቀሉ። 3. ሐምሌ 2011 ዓ.ም. — አሰቦት ገዳም፣ ምዕራብ ሐረርጌ፦ ጥንታዊው ገዳም በታጣቂዎች ተከበበ፤ ገዳማውያን ተገደሉ፤ የገዳሙ ይዞታና ደን ተቃጠሉ፤ አባቶችና እናቶች ከመንፈሳዊ መኖሪያቸው ተፈናቀሉ። 4. መስከረም 2012 ዓ.ም. — አዲስ አበባና ቢሾፍቱ፦ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ወቅት በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና በምዕመናን ላይ የጅምላ እስር፣ ድብደባና ወከባ ተፈጽሞ የበዓሉ መንፈሳዊ ድባብ ታወከ። 5. ጥቅምት 2012 ዓ.ም. — ዶዶላ፣ ምዕራብ አርሲ፦ ኦርቶዶክሳውያን በማንነታቸው ተለይተው ጥቃት ተከፈተባቸው፤ ምዕመናን ተገደሉ፤ ንብረታቸው ወደመ፤ ክርስቲያኖች ተፈናቀሉ። 6. ጥቅምት 2012 ዓ.ም. — ኦሮሚያና አዲስ አበባ፦ የአክቲቪስት ጃዋር መሐመድን ተከበብኩ መግለጫ ተከትሎ በተቀሰቀሰው መጠነ-ሰፊ ሁከት በርካታ የኦርቶዶክስ አማኞች ተገደሉ፤ ንብረታቸው ወደመ፤ ምዕመናንም ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ። 7. ጥቅምትና ጥር 2012 ዓ.ም. — ሐረርና...