#በጥሞና መመርመር
ለአቶ ተላይ ገብሩ ያለኝን አክብሮትም በትህትና እገልፃለሁኝ።
ከአቶ ተላይ ገብሩ ፔጅ የተገኜውን አቶ ውብሸት ያጋሩት ነው ሙሉውን እኔው ያጋራሁት። #በጥሞና መመርመር ስለምፈልግ ነው ሼር ያደረኩት። ዳታ አለው።
በማዕከላዊ ጎንደር ከ80 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ሲኖር አማንያን መጎዳታቸውም ታሳቢ ቢደረግ እላለሁኝ።
/////======////
1. "ነሐሴ 2010 ዓ.ም. — ጅግጅጋ፣ ሶማሌ ክልል፦ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፤ ካህናትና ምዕመናን በመሰዊያው ፊት በግፍ ተገደሉ፤ ንዋየ ቅድሳት ተዘረፉ፤ ምዕመናንም ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቀሉ።
2. ሐምሌ 2011 ዓ.ም. — ሲዳማ፦ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፤ ካህንና ምዕመናን ተገደሉ፤ ነዋሪዎችም ተፈናቀሉ።
3. ሐምሌ 2011 ዓ.ም. — አሰቦት ገዳም፣ ምዕራብ ሐረርጌ፦ ጥንታዊው ገዳም በታጣቂዎች ተከበበ፤ ገዳማውያን ተገደሉ፤ የገዳሙ ይዞታና ደን ተቃጠሉ፤ አባቶችና እናቶች ከመንፈሳዊ መኖሪያቸው ተፈናቀሉ።
4. መስከረም 2012 ዓ.ም. — አዲስ አበባና ቢሾፍቱ፦ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ወቅት በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና በምዕመናን ላይ የጅምላ እስር፣ ድብደባና ወከባ ተፈጽሞ የበዓሉ መንፈሳዊ ድባብ ታወከ።
5. ጥቅምት 2012 ዓ.ም. — ዶዶላ፣ ምዕራብ አርሲ፦ ኦርቶዶክሳውያን በማንነታቸው ተለይተው ጥቃት ተከፈተባቸው፤ ምዕመናን ተገደሉ፤ ንብረታቸው ወደመ፤ ክርስቲያኖች ተፈናቀሉ።
6. ጥቅምት 2012 ዓ.ም. — ኦሮሚያና አዲስ አበባ፦ የአክቲቪስት ጃዋር መሐመድን ተከበብኩ መግለጫ ተከትሎ በተቀሰቀሰው መጠነ-ሰፊ ሁከት በርካታ የኦርቶዶክስ አማኞች ተገደሉ፤ ንብረታቸው ወደመ፤ ምዕመናንም ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ።
7. ጥቅምትና ጥር 2012 ዓ.ም. — ሐረርና ምሥራቅ ሐረርጌ፦ በጥቅምት ወር ሁከት አብያተ ክርስቲያናትና ንብረቶች ተቃጠሉ፤ ምዕመናን ተገደሉ፤ ነዋሪዎችም ተፈናቀሉ፤ በጥር ወር የጥምቀት በዓል አከባበር ወቅትም በምዕመናን ላይ ጥቃት ተከፍቶ ሰዎች ተገደሉ፣ ቆሰሉም።
8. ሰኔ – ሐምሌ 2012 ዓ.ም. — ሻሸመኔ፣ ባቱ፣ አርሲና አካባቢዎቻቸው፦ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ፤ አብያተ ክርስቲያናትና መኖሪያ ቤቶች ተቃጠሉ፤ ምዕመናን ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቀሉ።
9. መስከረም 2013 ዓ.ም. — መተከል፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፦ በኦርቶዶክስ ማኅበረሰብ አባላት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ምዕመናን ተገደሉ፤ አብያተ ክርስቲያናትና ቤቶች ተቃጠሉ፤ የተረፉትም ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቀሉ።
10. ኅዳር 2013 ዓ.ም. — አክሱም ጽዮን፣ ትግራይ፦ በጦርነቱ ወቅት በአክሱምና በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ዙሪያ ሰላማዊ ምዕመናንና ካህናት በጅምላ ተገደሉ።
11. መጋቢት 2013 ዓ.ም. — ደቦስ (ባቦ ደምበሊ)፣ ምዕራብ ወለጋ፦ በቅዱስ አቦ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ንጹሐን ምዕመናን በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ቤተሰቦችም ተፈናቀሉ።
12. ጥር 2014 ዓ.ም. — ወይብላ ቅድስት ማርያም፣ አዲስ አበባ፦ በጥምቀት በዓል ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ሲመለስ በጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይትና አስለቃሽ ጭስ ምዕመናን ተገደሉ፤ በርካቶችም ቆሰሉ።
13. ሰኔ 2014 ዓ.ም. — ቶሌ (ጊምቢ)፣ ምዕራብ ወለጋ፦ በሰላማዊ ነዋሪዎች (በአብዛኛው የኦርቶዶክስ አማኞች) ላይ በተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት ንጹሐን ተገደሉ፤ ቤቶች ተቃጠሉ፤ ምዕመናን ተፈናቀሉ።
14. ስታዲየም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፣ አዲስ አበባ፦ ከመስቀል አደባባይ ይዞታና ከበዓላት ጋር በተያያዘ በቅጽረ ግቢው ውስጥ በጸሎት ላይ በነበሩ አረጋውያንና ምዕመናን ላይ የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ምዕመናን ታፍነው እንዲወድቁና እንዲጎዱ ተደረገ።
15. መስከረም 2015 ዓ.ም. — ቅበት፣ ስልጤ ዞን፦ ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው ጥቃትና ማግለል ደረሰባቸው፤ ከመኖሪያ ቀዬአቸውም ተፈናቀሉ።
16. ጥር – የካቲት 2015 ዓ.ም. — ኦሮሚያና የተለያዩ አካባቢዎች፦ በሕገ-ወጥ የጳጳሳት ሹመት የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና ለመንጠቅ በተደረገ ሙከራ ወቅት ካህናትና ምዕመናን በጅምላ ታሰሩ፣ ተገረፉ፤ ከስራ ተባረሩ ፤ ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገቡም መንገዶች ተዘጉባቸው።
17. የካቲት 2015 ዓ.ም. — የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በካቢኔ ፊት፦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ ንግግራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ አቋም በማጣጣልና በሊቃነ ጳጳሳት ላይ በማሾፍ ሕገ-ወጥ ቡድኑን ከሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር በእኩል ያዩበት ንግግር በማድረጋቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ይፋዊ የተቃውሞ መግለጫ አወጣ።
18. የካቲት 2015 ዓ.ም. — ሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል፦ ቤተ መቅደሳቸውን ከሕገ-ወጥ ወረራ ለመጠበቅ በቅጽረ ግቢው በጸሎት የተሰባሰቡ የኦርቶዶክስ ወጣቶችና ምዕመናን በጸጥታ ኃይሎች ጥይት ተመትተው ተገደሉ፤ በርካቶችም ቆሰሉ።
19. የካቲት – ግንቦት 2015 ዓ.ም. — ሸገር ከተማ፣ ኦሮሚያ፦ "ሕገ-ወጥ ናቸው" በሚል ሰበብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በዶዘር ፈረሱ።
20. መጋቢት 2015 ዓ.ም. — ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዲስ አበባ፦ በዓድዋ በዓል ወቅት በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ውስጥ በጸሎት ላይ በነበሩ ምዕመናን ላይ አስለቃሽ ጭስ ተተኩሶ ድብደባ ተፈጸመ፤ ምዕመናን ተገደሉ፤ በርካቶችም ቆሰሉ።
21. ከ2015 ዓ.ም. ጀምሮ — ደራ ወረዳ፣ ሰሜን ሸዋ፦ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ተከታታይ ጥቃቶች ካህናትና ምዕመናን ተገደሉ፤ ታገቱ፤ አብያተ ክርስቲያናት ተዘጉ፤ ነዋሪዎችም ተፈናቀሉ።
22. ጥር 2016 ዓ.ም. — መተሐራ አካባቢ፦ ከቁልቢ ገብርኤል በዓል በመመለስ ላይ በነበሩ ምዕመናን ላይ የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት ከፍተው ሰዎች ተገደሉ፤ ሰዎችም ታገቱ።
23. የካቲት 2016 ዓ.ም. — ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም፦ ታሪካዊው ገዳም በታጣቂዎች ተደፍሮ መነኮሳትና አገልጋዮች ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ በግፍ ተገደሉ።
24. መጋቢት 2016 ዓ.ም. — ዶዶላ፣ ምዕራብ አርሲ፦ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ቤተሰቦቻቸው በታጣቂዎች ተገደሉ።
25. ግንቦት 2016 ዓ.ም. — አሰኮ ወረዳ፣ አርሲ ዞን፦ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንና መኖሪያ ቤቶች ተቃጠሉ፤ ምዕመናን ተገደሉ፤ ነዋሪዎችም ተፈናቀሉ።
26. ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ — በአማራ ክልል ግጭት በገዳማትና ምዕመናን ላይ የደረሱ ጉዳቶች፦ በጦርነቱ ሳቢያ በገዳማትና በአድባራት አካባቢ በተተኮሱ የከባድ መሣሪያና የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ምዕመናንና አገልጋዮች ተገደሉ፤ ቆሰሉ፤ ቅርሶች ተጎዱ፤ ነዋሪዎችም ተፈናቀሉ።
27. ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ — በኮሪደር ልማት ሰበብ ምዕመናንን ከአድባራት ማፈናቀል፦ በአዲስ አበባ ታሪካዊ ደብራት ዙሪያ የነበሩ ምዕመናን ቤታቸው ፈርሶ ወደ ዳርቻዎች ተፈናቀሉ፤ ይህም አድባራትን ከአጥቢያ አማኞቻቸው ነጥሎ የአገልግሎትና የምዕመናን እጥረት ፈጠረ።
28. ጥቅምት 2019 ዓ.ም. —አርሲ ዞን፦ መርቲ ሽርካና፣ጮሌ ወረዳዎች የኦርቶዶክስ ምዕመናን በታጣቂዎች ተገደሉ፤ ሰዎች ቆሰሉ፤ መኖሪያ ቤቶች ተቃጠሉ፤ በርካታ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቀሉ።
29. የመንግሥት ሚዲያዎች አድሏዊና ኦርቶዶክስ-ጠል የትረካ ዘመቻ፦ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ማድበስበስ፤በሞታቸው የግፍ መግለጫ በመስጠት የሚዲያ ቁማር መጫወት ፤ ሲኖዶስ በተፈተነበት ወቅት ለሕገ-ወጥ አካላት የአየር ሰዓት በመስጠት ቤተ ክርስቲያኒቱን በጠላትነት የመፈረጅና ይዞታዎቿን ጥያቄ ውስጥ የመክተት ዘመቻ አካሄዱ።
30. ኦርቶዶክሳውያንን ከመንግሥት የሥልጣን እርከኖች ማግለል፦ በፌዴራልና በክልል ቁልፍ የውሳኔ ሰጪነት ቦታዎች፣ በጸጥታና በሲቪል ሰርቪስ መዋቅሮች ውስጥ ኦርቶዶክሳውያንን የማራቅና የማግለል ስልታዊ አሠራር ተስፋፋ።
31. የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ኦርቶዶክሳውያን በመሆናቸው ብቻ ከአንገት ማህትብ እስከ ሚመገቡት ምግብ ድረስ ያለው ኦርቶዶክስ ጠል ፈተና::
33. የካቲት 2015 ዓ.ም. — ቡሌ ሆራ፣ ምዕራብ ጉጂ፦ በቤተ ክርስቲያን ቀውስ ወቅት ቤተ መቅደሱንና እምነቱን ለመጠበቅ በሰላማዊ መንገድ አደባባይ የወጣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣት ተማሪ በጸጥታ ኃይሎች ጥይት ተመትቶ በግፍ ተገደለ።
34. በ2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አቀብለው፣ ቅዳሴ ቀድሰው ከቤተ መቅደስ በመውጣት ላይ የነበሩ ካህን በመንገድ ላይ በድንጋይ ተወግረው በግፍ ተገደሉ።
35. ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ — በአማራ ክልል በድሮን ጥቃት መነኮሳት መገደላቸውና በገዳማት የደረሱ ጉዳቶች፦ በጦርነቱ ሳቢያ በገዳማትና በአድባራት አካባቢ በተፈጸሙ የከባድ መሣሪያና የድሮን ጥቃቶች ገዳማውያን መነኮሳት፣ አባቶችና ሰላማዊ ምዕመናን በግፍ ተገደሉ፤ ቆሰሉ፤ ጥንታውያን ቅርሶች ተጎዱ፤ ነዋሪዎችም ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ።
36. ጎሃ ጽዮን፣ ሰሜን ሸዋ (የኦሮሚያ አዋሳኝ ኬላ)፦ በመንገድ መፈተሻ ኬላ ላይ አገልጋይ ካህን በጸጥታ ኃይሎች በግፍ በጥፊ ተመቱ፤ መስቀላቸው፣ ክህነታቸውና ክብራቸው ተደፈረ፤ ከፍተኛ ማዋከብና እንግልትም ደረሰባቸው።
37. ና ወዘተ ....ከብዙ በጥቂቱ ማሳያዎች ናቸው። እናንተም ጨምሩበት ...........
ይህ ጽሑፍ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በአገልጋዮቿና በምዕመናኗ ላይ የደረሱትን ግድያዎች፣ የቃጠሎና የውድመት አደጋዎች፣ መጠነ-ሰፊ መፈናቀሎች እንዲሁም መዋቅራዊ በደሎች በግልጽ የሚያስረዳ የታሪክ ምስክር ነው።"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ