የሚገርመኝ
የሚገርመኝ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተንታኝ ማለት ዕውቀት በሙሉ ተጠቅልሎ የተሰጠው የዓለሙ ሁሉ የህሊና ባለቤት ነኝ ብሎ መገኜቱ ነው። ስለ ነፃ የገብያ ስርዓት፤ ስለ ውሃ ቴክኖሎጂ፤ ስለ ስነ - ፈለግ፤ ስለ ዲጅታሉ ዓለም፤ ከዚህም አልፎ ውስብስቡን የአየር ላይ ተዋጊ ጀቶች፤ ሮኬቶች፤ ድሮኖች ማይኩን አስተካክሎ ትንተናው ሸር ብትን ሲባልበት ነው። ልኬ አይደለም አይታሰብም። ሳይንሱንም፤ ፍልስፍናውም፤ ሁሉም ይተነተናል፤ ይመነዘራል። ጎንደሮች ብልሆች ናቸው "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ። የተንጠለጠሉትንስ ማን እንበላቸው ነው ጥያቄዬ? ራሺያ ሠራሽ ጄቶች እግር ባደረሰው ተንታኝ እየተቦካካ -ነው? በጦርነትም "የታክቲክ የስትራቴጂ ሽንፈት" የማይደመጥ ነገር የለም። ድፍረታቸው ይገርመኛል።
ሥርጉትሻ 29/10/2026.
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ