ልጥፎች

#ዝርግ

  #ዝርግ #ትርትር #ፍትልትል #ዝልግልግ #ዝልዝል #ትብስብስ መርጣችሁ የፈለጋችሁትን ሰይሙለት።   "ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፤ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል።"   (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፳፰) #ምዕራፍ ፳።   እንዴት አመሻችሁ ውቦቹ ቅኖቹ።    #ኦላ እራሱን #ከሶ ፤ ቃሉንም #ክዶ መግለጫ አውጥቷል። ትንሽ ረብ እስኪል መጠበቅ ስላለብኝ ነው የዘገየሁት። ሁለተኛውን መግለጫ ከBBC ነው ያገኜሁት፤ ከሥር አያይዘዋለሁኝ።    እኔ እንኳን ብናኝ የኢትዮጵያ መንፈስ የለለበት ድርጅት ጋር አቅም ማዋጣት አልሻም። አትራፊ ስላልሆነ። የመጀመሪያውን ስለፃፍኩበት ግድ ስለሆነ ነው ለማያያዝ። እርግጥ ነው ሰሞኑን ዝበት ከዛም ከዚህም ስላለ የማቃናት ተግባር ግድ ይለናል። በተለይ በትውልድ ጉዳይ ለምንሰራ ባተሌወች። ያለመመጣጠን፤ የመክበድ፤ የክህሎት መራራቅ፤ ሚስጢር የማመሳጠር አቅም ስስነት ብቻ ……… ብቻ ኢትዮጵያ ዕዳ ተሸከሚ ስትባል #ኦነግ የሚባል ድርጅት በታሪኳ ተፈጠረባት። ምን እንደሚፈልግ? ምን #እንዳሳካ የሚታወቅ ነገር የለም? ያው ፕሮጀክቱ ዱር ቤቴ ይቀናዋል፤ የሰው ልጅን ማስጨነቅ፤ ማሳደድ፤ መሰረዝ፤ ማፈናቀል፤ መረበሽ ተልዕኮው ነው። ይህን ተሸከም ሁለት ትውልድ አልፎ ሦስተኛ ተተካ። መሃከነ። ዕውነት ለመናገር ጃል መሮ እዩኝ እዩኝ የማይሉ ዝምተኛ ናቸው። አይናገሩም። ስለዚህም አይሞገቱም። ምን ጎድሎባቸው ጫካ ገቡ ቢባል #ጫና ለመፍጠር፤ እንደ ማስፈራሪያ፤ እንደ መቀጣጫ፤ ለ፬ኪሎው ስኬት #ሽፋን ለመስጠት ነው። እኔን የሚገባኝ ይህ ነው። የሆነ ሆኖ #ኦላ ሰሞኑን ያለወትሯቸው #ጭካኔያቸውን አመኑ። ጭካኔው ሲታመን በምክክር ነው። ዘርዘር አድርጌ ጽፌበታለሁ...

#ያሰናዳል።

  #የቁም #ሰማዕትነት እንዲህም አለ።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"   ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የአርሲ (ምሥራቅ አርሲ) እንዲሁም የሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ) አህጉረ ስብከት ሊቀ - ጳጳስ ናቸው። "በአርሲ ምን ያልሆነው አለ?" ይላሉ።   MK TV || ዐውደ ትሩፋት || በአርሲ ምን ያልሆነብን አለ ?   አንደበታቸው #ልስልስ ነው። ኃይለ ቃል፤ ብስጭት አለሰማሁም። ይልቁንም የጠለቀ #ትህትና አይቻለሁኝ። ጠቅላይ ሚ/ር አብይ ወደ ስልጣን በመጡበት ሰሞን በጌዴኦ ህዝብ ላይ የተከሰተ ከባድ ችግር ነበር። ያንጊዜ ጠቅላይ ሚር አብይ ቢዘገዩም ከቦታው ሲደርሱ ወጥ የሆነ #የልቀሶ ሁነት ገጥሟቸው ነበር።   #ብጹዑ አባታችን ከቦታው ሲደርሱም ሽብሸባ፤ ዝማሬ ሳይሆን #የወል #ለቅሶ በጥቁር ልብስ ነበር የጠበቃቸው። ካህናቱ፤ ዲያቆናቱም ከውስጣቸው ያለቅሳሉ። ይህን #የሃሞት ዘመን ፈጣሪ መፍትሄ ይሰጠው ዘንድ በብርቱ ከውስጥ ጸሎት ያስፈልጋል።   ዘፈን - በዝቷል፤ #ቡረቃ በርክቷል፤ የእርስ በርስ ፋክክሩ ጦፏል፤ ግን መጠያ ያጣው የእግዚአብሄር ቤት፤ ንዋየ ቅድሳት የነገ ተስፋወች ይገደላሉ፤ #ይላቀሳሉ ። ለምን ሆድ አይባሳቸው? #ማን አላቸው? #ምንስ አላቸውና?   እንዲህ ጠንካር ያሉ አባቶች፤ ሰማዕት ለመሆን የተሰናዱ #ብጹዓን አባቶች እንዲሁም የግንባር ሥጋው #ማህበረ ቅዱሳን እሳቱን እየደፈሩ በሞት ጥላ ሥር #እየተርገበገቡ ያሉ ከትናንት ሞት የተረፋ፤ ነገ ሞት የሚጠብቃቸውን፤ #ንጹኃንን በአካል ተገኝተው ከተጠቂወች ጋር ተላቅሰው፤ የተጠቂወችን ዕንባ አብሰው፤ ነገ በተስፋ ቀን ...

ለብልፄው #ምንዳ ለህወሃት #ዕዳ።

  ለብልፄው #ምንዳ ለህወሃት #ዕዳ ።   « #የተመድ ልዑካን እና የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች መቀለ ገቡ» BBC.   «በሰወቹም ጥፋት ሰወቹ ጮሁ ቃላቸውም ወደ ሰማይ ደረሰ።» (መጽሀፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፳፮)   #ምዕራፍ ፳።   እንዴት አደራችሁልኝ ክብሮቹ ውዶቹ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ሙያሌን በሚመለከት በብልፄው ትኩረት መሰጠቱን አዳምጫለሁኝ። ጥሩ ነው። ህዝብ በዚህ መሰል ሠውሰራሽ ቀውስ አሳሩን ሊይ አይገባም። በሌላ በኩል ውዳችን ኬንያም ኢትዮጵያ ስጋቷ ልትሆን አይገባም።   #የጊዜያዊው #ባለ አደራው እና አደረጃጀቱ።   የባለ አደራው አደረጃጀት፤ የአመራሩ ፈረቃዊ ስልት ከውስጤ የገባ አመክንዮ ነው። እኔ ለኢትዮጵያ አገሬ የምመኜውም ይህን መሰል #ቀና እና #ቅን ቲም ወርክ ነው።   አካሉ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር #ንክኪ እንደለለው ነው ያዳመጥኩት። ይህ #ብቁ እርምጃ እና #ውሳኔ ነው። በሌላ በኩል አንዱም ለሁሉም ሁሉም ለአንዱ የአመራር ጥበብ፤ የአያያዝ - ክህሎት፤ የተመክሮ - ልምድ #ማወራረስ ፤ ማዋህድም የሚቻልበት ስለመሆኑ ይረዳኛል።   እርግጥ ነው የተከፋ አስተያዬቶች አይቻለሁ። "ከአንድ አካባቢ ነው" የሚል። እንዚህ አይነት #ጥቃቅን ጉዳዮች ለዕንባ ተደራሽነትን #ያቆረፍዳል ። ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ በሊሂቃን በቀደመው ጊዜ፤ በዚህ ዘመን በሊቃናቱ ምክንያት ከዛች የጠቋቆረች ከፈን፤ ከተጎነባበች ጎጆ አልተወጣም። ይህም አልበቃ ብሎ ሰርክ ለጦርነት የሰው ልጅ #ማገዶነት አሳዛኙ ታሪካችን ነው።   በሌላ በኩል የሁለቱን ንግግር አዳምጫለሁኝ። ስልችት ካለን የህወሃት #የመግለጫ መጋዚን ያላባራ ፖለቲካ እና ከበሰጨኝ...