ለብልፄው #ምንዳ ለህወሃት #ዕዳ።
«#የተመድ ልዑካን እና የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች መቀለ ገቡ» BBC.
«በሰወቹም ጥፋት ሰወቹ ጮሁ
ቃላቸውም ወደ ሰማይ ደረሰ።»
(መጽሀፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፳፮)
#ምዕራፍ ፳።
እንዴት አደራችሁልኝ ክብሮቹ ውዶቹ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ሙያሌን በሚመለከት በብልፄው ትኩረት መሰጠቱን አዳምጫለሁኝ። ጥሩ ነው። ህዝብ በዚህ መሰል ሠውሰራሽ ቀውስ አሳሩን ሊይ አይገባም። በሌላ በኩል ውዳችን ኬንያም ኢትዮጵያ ስጋቷ ልትሆን አይገባም።
የባለ አደራው አደረጃጀት፤ የአመራሩ ፈረቃዊ ስልት ከውስጤ የገባ አመክንዮ ነው። እኔ ለኢትዮጵያ አገሬ የምመኜውም ይህን መሰል #ቀና እና #ቅን ቲም ወርክ ነው።
አካሉ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር #ንክኪ እንደለለው ነው ያዳመጥኩት። ይህ #ብቁ እርምጃ እና #ውሳኔ ነው። በሌላ በኩል አንዱም ለሁሉም ሁሉም ለአንዱ የአመራር ጥበብ፤ የአያያዝ - ክህሎት፤ የተመክሮ - ልምድ #ማወራረስ፤ ማዋህድም የሚቻልበት ስለመሆኑ ይረዳኛል።
እርግጥ ነው የተከፋ አስተያዬቶች አይቻለሁ። "ከአንድ አካባቢ ነው" የሚል። እንዚህ አይነት #ጥቃቅን ጉዳዮች ለዕንባ ተደራሽነትን #ያቆረፍዳል። ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ በሊሂቃን በቀደመው ጊዜ፤ በዚህ ዘመን በሊቃናቱ ምክንያት ከዛች የጠቋቆረች ከፈን፤ ከተጎነባበች ጎጆ አልተወጣም። ይህም አልበቃ ብሎ ሰርክ ለጦርነት የሰው ልጅ #ማገዶነት አሳዛኙ ታሪካችን ነው።
በሌላ በኩል የሁለቱን ንግግር አዳምጫለሁኝ። ስልችት ካለን የህወሃት #የመግለጫ መጋዚን ያላባራ ፖለቲካ እና ከበሰጨኝ ንግግር የወጣ ሊደመጥ የሚችል ንግግር ሆኖ ነው ያገኜሁት። የተረጋጋ ስኩን መንፈስ በንግግራቸው ውስጥ አዳምጫለሁኝ።
"የተመድ ልዑካን እና የተለያዩ አገራት አንባሳደሮች መቀለ ገቡ። BBC።"
ዓለም ዓቀፋ የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ የወሰደው እርምጃ የህወሃትን መጠነ ሰፊ ተስፋን የናደ ነው። ዓለም ዓቀፋ ማህበረሰብ የብልፄውን ባለአደራ መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ #ዕውቅና ሰጥቶታል።
በዚህ እርምጃ ብልፄው #ቀንቶታል - አትርፏልም፣ ህወሃት ደግሞ #ቀን ክዶታል። በዘልማድ ቋንቋ ህወሃት ወፍ አላወጣውም። ይህን የዓለማቀፋን ዲፕሎማሲያዊ ውሳኔ ለማሻሻል ይሁን ለመቀልበስ ህወሃት ብዙ ማገዶ ይጠይቀዋል።
ጫካ ውስጥ ሆኖ፤ በጎሌራ ትግል እንደ ገና በዓለም ዓቀፋ ማህበረሰብ ልብ ውስጥ ለመግባት ልፋት ይሆናል። ከማዕከላዊ መንግሥትም ጋር በርቀት ነው ህወሃት የሚገኜው። ለዛውም ከተፈቀደለት።
ብልጽግና የህወሃት ትውልድ ውጤት ነው። አሁን ያለው ጄነሬሽን የኢህአዴግ ጄነሬሽን ነው። የአመራር ለውጥ እንጂ ህገ - መንግሥቱ፤ የአሠራር ዘዬው፤ አባላት ይሁን አካላቱ የህወሃት ሙሉ መንፈስ ያለበት ነው። #ስፕሪቱ ህውሃታዊነት ነው። ህወሃት ያልተረዳው ይህን ነው። ይህ እኮ ትርፌ ብሎ ሊቀበለው በተገባ። ሃሳቡ ሁሉ ዞጋዊ ነው።
ህወሃት የቀረበት መንበረ - መንግሥቱን መምራት ብቻ ነው። በልኩ የፖለቲካ ውክልና ለማግኜት ተከብሮ እና ተቆላምጦ መቀጠል ይችልም ነበር። ህወሃት ቢታገስ፤ ጥሞና ቢወስድ የምርጫ ጊዜውን አፈንግጦ ባይጀምር ህወሃትነቱን ይዞ ለመወዳደር የገደበው ነገር አልነበረም። ሚዛን ለማስጠበቅ ዋና ተፎካካሪ ሆኖ የመውጣት ዕድል ሁሉ ነበረው። ዕድሉን #እንኩቶ ያደረገው ራሱ ነው። በተሳሳተ እልኃዊ ስሜት። አዛውንት ድርጅትን የሚፈላ ስሜት ከመራው ውጤቱ ዕዳን ይከማምራል።
አቅል፤ አደብ ጠፋ እና እንሆ መጨረሻው ሬት ሆነ። ያን ያህል ዘመን ትግል ላይ መኖሩ፤ የህወሃት ተመክሮው ትዕግሥትን ሊሸልመው ባለመቻሉ ለሦስተኛ ጊዜ ብረት መስሎ ጫካ - ለጫካ፤ ለዛው #በመጠመን። አሳዛኝ ገጠመኝ ነው።
ቢያንስ ከዛ ሁሉ ጥፋት፤ ውድመት፤ የህዝብ ሰቆቃ በኋላ እንኳን፤ ነፍሱን ያተረፈለትን፤ በብዙ ወጪ፤;በብዙ ድካም ግሎባል አትኩሮት ተገኝቶ የደቡብ አፍሪካን ክብር አድን ጉባኤውን ውሳኔ ህወሃት #ሊያከብር ይገባ ነበር። እንዲያውም ለዛ ጉባኤ የመታሰቢያ ሐውልት ሊያሠራ ይገባው ነበር። ትንፋሹን፤ ትርታውን ያተረፈለት ታላቅ የመዋለ ዘመን ሽልማቱ ነበር።
የደቡብ አፍሪካው ውሳኔን ከረር ያለውን ለማላላት፤ የህወሃት ትውልድ በኬንያ፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ማሻሻያ እንደ አደረጉበት ይሰማኛል። ከዚህም አልፎ ካዛ ሁሉ ጥፋት በኋላ በልዩ ሴሪሞኒ በሽልማት ነበር የሞራል ጥበቃ የተደረገው።
የተጎዳው የአማራ፤ የትግራይ፤ የአፋር ህዝብ ድቀት፤ ውድመት ግፍ ነበር የተሰራበት። እንደ ሰው ሲታሰብ። ግራቀኙ ይቅርታ አልጠየቁም፤ ግራቀኙ የተጎዳን መንፈስ ለመጠገን ጥረት አላደረጉም። ውሾን ያነሳ ውሾ ተብሎ ነበር ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተቋቋመው።
እኔ ተው! ጦርነት አትጀምሩ ብዬ ነበር። መቀሌ ተገባ ተብሎ ግራ ቀኙ አንዱ ሲያስለቅቅ ሌላው ሲይዝ፤ ሌላው ለቆ ሌላው ደግሞ ሲይዝ ድል ሲባልም ደስታችሁን በልክ አድርጉ ነበር ስል የነበርኩት። የደቡብ አፍሪካ ስምምነትን ቀድሜ ነው የዘገብኩት። ተመስገንም ብዬ ነበር። ጦርነት የጥላቻ የቂም የበቀል የሰው ልጅ ምታሮ ነው።
እንደ ገና እንዲህ ሌላ ጦርነት ያ መከረኛ ህዝብ ይከፈትበታል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ጦርነት ስለምን በደሃ አገር እንደሚናፈቅ አላውቅም። የሆነ ሆኖ ከደቡብ አፍሪካው የትንፋሽ እረፍት በኋላ መፈንቅል ተካሂዶ መሪወች እኛ ነን አለ ህወሃትሻ፤ አናርኪዝም ነው ብዬ በወቅቱ ጽፌያለሁኝ። አቶ ጌታቸው ረዳን ቀይሩልን አላችሁ የፈቀዳችሁት ተቀየረላችሁ። እሱም አላረካችሁም።
በሌላ አቅም፤ በሌላ ኩነት በዛው ዶክትሬን በነፃ ዓውጪ ግንባርነት የኢትዮጵያ መንበረ መንግሥት ህልም በሱዳን ጠረፍ በሸረሪና፤ በቆቦ አላማጣ የተከፈተው ጦርነት መልሱን ታውቁታላችሁኝ።
መቀሌን ስትለቁ ብር ያቃጠላችሁበት ቲወሪ ፈጽሞ ያልገባኝ አመክንዮ ነበር። ምን አለ ሊለምኑ ላፈሩ ወገኖቻችን ብታከፋፍሉት። የደረቅ ወንጀል እስረኞችን ለቃችሁ መቀሌን ከተማ ማስበጥበጥ፤ መቅጣት ለምን ፈለጋችሁት? ሁልጊዜ ከሳሽነት አይሰለቻችሁንም? ዝም ብለን የምናያችሁ፤ የምንታዘባችሁ አለን እኮ። ሳይለንት ማጆሪቲ ምን ይለኛል ብላችሁ እሰቡት። ሙሉ አቅም ያለው እሱ ነውና።
አንድ ወጣትም ሰሞኑን ህይወቱን ቀምታችኋል። ሰማዕት ነው። የሰላማዊ ሠራዊት አዛዥ ልጅ ሲባል ሰምቻለሁኝ። ለምን? መበቀል መቼ ይሆን የሚበቃችሁ። ቢያንስ ስለ ልጆቻችሁ፤ ስለ ቅርስ ውርሳችሁ፤ ስለ ተገነቡ መልካም ነገሮች ልትጠብቁ ሲገባ ማውደም? እግዚአብሄር አምላክ ልብ ይስጣችሁ። አሜን።
የኢትዮጵያ ዘመን በሁለነገራችሁ በቃችሁኝ እያላችሁ ነው። አዳምጡት። ቆመንልሃል ለምትሉት ህዝብ ቢያንስ ከስጋት ጋር አፋቱት። ሰላሙን ስጡት። በቃው! እንደ ኮበሌ አትወኩት እባካችሁ? በሰፊ እምትተማመኑበት፤ እንደ በኽር ልጅ እንክህ እንክህ የሚላችሁ የዲፕሎማሲው ማህበረሰብም በቃችሁን አላችሁ። የአሜሪካን ባለሙሉ ሥልጣን አንባሳደር ኧርቢን ማሲንጋን ገፍታችሁ ላካችሁ።
እምንሳሳላቸውን አባታችን ፓትርያርክ ብዙወቅዱስ አባ እዮብ አባ ማትያስን ሳይቀር ሳትቀበሉ ደጅ ተዘግቶባቸው መለሳችሁ። አልቅሻለሁኝ እኔ። ቻይ አባት ናቸው አባ። ከቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ሌላ ሲኖዶስ ፈጠራችሁ የሰማይ ቁጣ መልስ ሰጠበት። ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ መንበረ #ፕትርክና በማን እጅ ነው? ይህን ማገናዘብ እንደምን ያቅታል።
የማታምኑት ረቂቅ አምላክ ሁሉንም አየ መልስ ሰጣችሁ። አዳምጡት በማለት በትህትና እህታዊ ዕይታዬን እሰጣችኋለሁኝ። ቀኑ ለግሟል። ዘመኑ ሊያችሁ አልፈለገም። ድልም አልቀናችሁም። መውደቅን ስንቅ አድርጋችሁ ብትቀጥሉ ትርፋ ዕዳ መከመር ነው። ለሰማዩም ለምድሩም አልተመቻችሁም።
ቀን ሲጠፋ እስኪመለስ በጥሞና መቆየት ምን ያቅታል? የበለጠ እያጡ፤ የበለጠ እየተሸበሸቡ፤ ድርብርብ ስቃይ እየተቀለቡ ከመሄድ በስተቀር አሁን ያለው አጠቃላይ ግብረ መልስ ተስፋን የሰነቀ አይደለም ለእናንተ። የታጋይነታችሁ ዘመን ተመክሮ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ለመረዳት እንዴት አቃተው? የሚገርመኝ ይህ ነው።
#ክወና።
በ2010 ዓም የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ፤ ዶር ለማ መገርሳ፤ ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል፤ አቶ ደመቀ መኮነን ም/ ጠቅላይ ሚር፤ በአንድ ላይ ሆናችሁ መግለጫ አዲስ አበባ ላይ ሰጣችሁ። አሁን ደግሞ ከፋኖ፤ ከኦላ ወኪሎች ጋር አድራሻው ባልታወቀ ቦታ ዶር ደብረጽዮን ሁለተኛ ሰው ሆነው አየሁኝ። መዝኑት።
ትዕግሥት ስንት በረከት ያጎናጽፋል። የማተርያሉ ይቅር። የመንፈስ ልዕልና ያስገኛል። መታገሥን መዳኛው ያደረገ ሰብዕና ድህነቱ ይሁን ስኬት አለማግኜቱ ከሞራል ልዕልናው በታች ናቸው። የታገሰበት ቁምነገር የአሻራው፤ የሌጋሲው ቋሚ ተቋም ነውና። ይህ የሰሞኑ ገጠመኝ በእርስወ ሰብዕና ውስጥ ምን ያህል ምቾት ሰጥቶወት ይሆን???
ፎቶው ከBBC እና ከጉግል የወሰድኩት ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
18/11/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
//////()/////()////()///()
«የተመድ ልዑካን እና የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች መቀለ ገቡ» BBC.
«የተባበሩት መንግሥታት ልዑካን፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት የፌደራል መንግስት የትግራይ ዋና ከተሞችን ከተቆጣጠረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ክልሉ ተጓዙ፡፡
በልዑካን ቡድኑ ውስጥ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ጨምሮ ከስምንት ሀገራት የተውጣጡ አምባሳደሮች፣ የተመድ እና የአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንደሚገኙበት ትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የጉዞው ዓላማም በትግራይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በአካል ለመመልከት እና በቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል።
ልዑካኑ ከትግራይ ባለአደራ አስተዳደር ጋር ውይይት እንደጀመሩም የተገለጸ ሲሆን የሰብአዊ ዕርዳታ፣ ተፈናቃዮች፣ በትጥቅ የማስፈታትና መልሶ የማቋቋም ሂደት እንዲሁም የክልሉ የሰላም ጉዳይ ውይይት የሚደረግባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች ናቸው ተብሏል።
የአስተዳደርና የሕዝብ አገልግሎት ጉዳዮች ዋና አስፈፃሚ አቶ አሰፋ አብርሃ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከክልል እስከ ወረዳ የዘለቀ የአስተዳደር ሥርዓት አቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ለእንግዶቹ ማብራራቸውን ተገልጿል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑካን ከዛሬ ሕዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በመቀለ ከተማ እንደሚያደርጉ ዘገባው አመልክቷል።
ልዑካኑ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ ሁለቱ ኃይሎች ውይይት እንዲያደርጉ የሚያሳስብ መግለጫዎችን ማውጣታቸው ይታወሳል።
የተባበሩት መንግሥታት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ስለተቀሰቀሰው ጦርነት ጥልቅ ስጋት እንዳለው በመግለጽ፣ ተፋላሚ ወገኖች ግጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ወደ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቦ ነበር።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የህወሓት መሪዎች "መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመክፈት ባሳለፉት ደካማ ውሳኔ ማዘናቸውን" መግለጻቸው ይታወሳል።
አምባሳደሩ "ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች በዚህ ጦርነት ውስጥ ባለመግባት ብልህ እንዲሆኑ" በመምከር አሜሪካ ኢትዮጵያን ወደተሳሳተ መንገድ ለመምራት የሚሞክሩ ተጨማሪ አመራሮች ላይ ማዕቀብ ለመጣል አማራጩ እንዳላት አመልክተዋል።»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ