#እስቲ እናውጋው ...
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ምዕራፍ ፳።
#እስቲ እናውጋው የብልፄውን የነገረ በለጡን ሂደት።
ግን ለምንድን ይሆን የተመደቡበት #አገር የተከደነው? አልገብቶም። "ወይ ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽም ባላሳፈርሽ።" የአማራ ባለሥልጣናት ተነቀሉብን የሚሉ ሰምተናል። ለመሆኑ እያሉ ምን አድርገውላችሁ ይሆን? ምን ፍሬ ያፈራ ተግባር ለአማራ ልጅ ከውነው ይሆን ከስልጣን ተነሱብን ብላችሁ #የምትቆዛዝሙት? ኑረውም #አልነበሩም። ባይኖሩም #ምንም።
ያን ጊዜ #እንክህ እንክህ የነበረው የፍላጎታቸው ሴል የሰኔ 15ቱን ኬዝ ማኔጅ ለማድረግ ስለሚረዷቸው ብቻ ነው። ነገረ አማራ እና ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን በሚመለከት እራሱን የቻለ በሳል፤ ያስተዋለ ሂደት ይጠይቃል።
የአማራ ህዝብ በኽረ ጥያቄ ሳይሆን ሊቀድም የሚገባው የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በዘመነ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ልቦና፤ ህሊና ፕረዘንቴሽኑ በቅርበት ወይንስ በርቀት እንዴት ይስተናገዳል? የሚለው በለብለብ፤ በድረስድረስ፤ በግብታዊነት ሳይሆን #የጨመተ ጥናት ይጠይቃል።
ጭምትነት ሙሉ ቁመና አለው ስል በእኔ ግንዛቤ ከጥላቻ፤ ከማቅለል፤ ከቂም፤ ከበቀል የነፃ ቅን ሰብዕና ማለቴ ነው። ቂም አርግዞ በቀል የሚወልድ ሰብዕና "ጭምት #ምራቁን የዋጠ" የሚለውን ሰብዕና አያሟላም እና።
#ህ።
ግርም ያለኝ ግን "አገሬን ትቼ አልሰደድም ያሉት" የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ለስደት ሲመደቡ ይሁን ሲሉስ? "አንባሳደር" ፕሮፌሰር መስፍን አርያ እና ሁለት ባልደረባቸው #ለብልፄው ፈርመው እንደነበር መገለጡ ገረመኝ። ሙሁራን ሊቃውንት ናቸው። ሊቅነት የፋክት ብቃት ነው። የፋክት ብቃት እና ኢትዮጵያዊነት ማህለቁ ለህዝቡ ፍጹም ታማኝ እና ግልጽነትን ይጠይቃል። ተዚህ ላይ ምን አገኜን ይሆን???
ከውስጤ ነበር የምክክር ኮሚሽንኑን ሁነት እከታተል የነበረው። የአገሬን የኢትዮጵያ ጉዳይ አቅርቤ ነው እምከታተለው። ባምንበትም ይሁን ባላምንበት። ያው የምክክር ኮሚሽኑ ተግባር ሲጠናቀቅ #የእንትን ሞት እንደሚባለው ሆኖ ነው የተሸበለለው ተሸብሽቦ ይሁን ተጣጥፎ የቀረባችሁን ክብሮቼ የጹሁፌ ታዳሚወች ወስኑት። ያ ተናፋቂ የዘመናት ጥያቄ ምክክር እርቅ ሰላም ምህረት ይቅርታ ያሳካል የተባለው ተስፋ ቀርቶበት በተፋፋመ ፍጥጫ ሁለመናው ከነሃሴ 16/2018 በኋላ ግለቱ የፍትጊያው ጨምሮ ተጣጡፏል።
ምክክር ኮሚሽኑ ማንን ወግኖ ይተጋ እንደ ነበር ጨዋታ እና ቧልቱ በጠራራ ጠሐይ ብልፄው እንዲህም /// እንዲያም አኮመኮመን። "አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ" ዓይነት። የህልሙ ሃሳቡም #ተሸነፈ። ገለልተኛ ካልነበረ ለምን ተወነ? ጠንክረው ሲሞግቱ የነበሩ ወገኖች ያሉት ስለመሆኑ ትልቅ ማረጋጋጫ ነው። የዲፕሎማሲው ማህበረሰብም ይታዘባል።
የምክክር ኮሚሽኑ የገለልተኝነት አመክንይ የምር የተቋቋመበት ዓላማ #ከሽፏል። አፈፃጸሙ እራሱ ይገርመኛል። በማጠናቀቂያው ሴሪሞኒ ያልተገኙት ጠቅላይ ሚር አብይ ዲል ባለው የአጀንዳ ርክክብ ላይ ነበሩ። ተወጥኖ - ተጠናቀቀ የተባለበት የሂደት ጥድፊያ በራሱ ይገርማል።
ሌላው ለወሬ ነጋሪ፤ በአፈፃጸሙ ላይ ምክር ቢያስፈልግ እንኳን ዋና መሪው ከኢትዮጵያ በብዙ ማይል #ሊርቁ አይገባም ነበርን? ብልህነት ተሰንቆ ቢሆን ኖሮ። ለምን የምክክሩ ቁንጮ አንባሳደር ፕሮፌሰር መስፍን #እንዲርቁ ተፈለገ? ተስፋ ሲከፋው የትውልድ ነገ ይደፋ። ያው በየዘመኑ ያሉ የአመክንዮ አነሳስ እና አፈፃጸም ዕድሜ ጠገብ ሲሆን የታሪክ አካል ስለሚሆን።
ታሪክ ለእኔ፤ ባህል ለእኔ በአንድ የዘመን ማዕቀፍ ህዝብ በተሟላ ሁኔታ ተሳትፎ ዕድሜ ጠገብ ሲሆን ታሪክም፤ ባህልም ይሆናል ብዬ ስለማምን። 4000 ሺህ ህዝብ በአንድ ጉባኤ። ረጅም እና ሁለገብ ሁነቶችን ያካተተ ክንውን በዘመነ ብልጽግና፤ የብልጽግናን ፍላጎት ጸንሶ የብልጽግናን መንግሥት አፍነሽንሾ መጪ ያለ ሁነት። ዕድሜ ጠገብ ሲሆን ታሪክም፤ የባህል አካልም ይሆናል። የታደገው አመክንዮ ይኑር አይኑር እንደ ተርጓሚው ይሆናል።
ሌላው ግን መሰደድን ተጠይፎ ሌላ ስደት በሹመት ይባል በዲሞሽን ራቅ በልልኝ ሲባል ከፕሮፌሰር መስፍን ሞቶ ጋር እንደምን #እርቀ ሰላም እንደሚያወርድ ወፊቱ ትመልሰው።
!#ናልኝ እስኪ ፍሬውዬ።
ፍሬው ነገር ነገረ ሲነሪቲ ነው። በዕውቀትም፤ በትምህርት ደረጃም፤ በፖለቲካ ፓርቲ ቆይታ ያላቸው፤ አነሰ አደገም ለአካባቢያቸው እንደ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚዮቸውን እንደ መገልገያ መሳሪያ ተጠቅሞ አልይህ ዓይነት? ብልፄው እኮ #በለጡም ነህ እኮ።
#ዲፕሎማሲ። International Relation" ግን ዲፕሎማሲ ጠጭ፤ ሌባ፤ ሰነፍ" ሠራተኛ ይርበዋልን? ዶር አብይ አህመድ ናቸው አዲሶቹን ሚኒስተሮቻቸውን ሲሾሙ የአንድ አመት #የአካልተአካል የስለላውን ግብረ መልስ ሲገልጡ የነገሩን። አሁን ባለው የዘመኑ እጅግ ፈታኝ የፖለቲካ ባህሬ የዲፕሎማሲው ተግባር አይደለም ኢትዮጵያ የዓለም ዴፕሎማሲ ፈተና ላይ የወደቀበት ጊዜ ነው።
የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ አጢኖ ፖለቲካ ሳይንስ መማር ብቻ ሳይሆን በዘርፋ #International Relation ተኮር ልምድም፤ ዕውቀትም፤ ተመክሮም ያላቸውን ሊቀ - ትጉኃን መመደብ ይገባ ነበር። በዘልማድ የጡሮታ መውጫ፤ ወይንም የዲሞሽን ሥራ ማስኬጃ እርምጃ ከመውሰድ። በዚህ ምደባ አገረ - ኢትዮጵያ #የምትቀጣበት ዘርፈ ኩርኩም መሆኑን አስተውያለሁኝ። መጣያ፤ ማግለያ ታላቁን ግሎባል መስክ መሆኑ ያስገርማል። ቋንቋውም ፈታኝ ነው። ከአክሰንቱ ጀምሮ።
ከተመደቡት ውስጥ ጥቂቶች ልምዱም ተመክሮም ያላቸው ይኖራሉ። ሌሎች ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ ለማየትም #ስልችት ያሉባቸውን የኢህዴግ የገዛ ቤተሰቦቻቸውን አልያችሁ አልስማችሁ ብለው #ሽንገላን ጠጡልኝ ብለዋቸዋል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከሳቸው በላይ ሲነሪቲ ያለው አንድ ቀንጣ ነፍስ ማስተናገድ አይሹም።
በዚህ ዘርፍ ትዕግስቱም የላቸውም። ከህወሃት ጋር የተመሰጠረው፤ የማይታረቀው ተቃርኖም ይሄው ነው። የቀደመ ነገርን ማስጠጋት ኢትዮጵያ ላይ ማስጠጋት ከብዶ አያለሁኝ። የቀደመ ልምድ እና ተመክሮ ቀና ከሆነ ሰብዕና ካለው፤ ዲስፕሊንድ የሆነ ምራቁን የዋጠ ሰብዕና ጋር ከተዋህደ በራሱ #ተቋም ነው። ተቋም ነው ስል አንድም ሙሉዑ የሆነ ሰብዕ።
ሌላውም የዘመኑ የቅርቦችም ቢሆኑ ለጊዜ ማካሄጃ ያሰለፏቸውንም ከዚህ ዕጣ ያነሰ ገጠመኝ ሊገጥማቸው ይችላል። ለዚህ ነው እኔ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሰብዕናቸውም ይሁን ዘመናቸው #አሳቻ ናቸው የምለው። አቅልለው፤ አጣጥለው ይሁን አግንነው የሚዮቸው ወገኖቼ ሁልጊዜም ይገርሙኛል። ኢትዮጵያ ምን እና ምን እየሆነች እንዳለች፤ የትኛው አመክንዮ ሽሽት እንደተፈረደበት፤ የትኛው እቅፍ እንደተፈቀደለት ለመተንበይ ይቸግራል።
#ክወና።
የፖለቲካ ድርጅት ምደባ ተመዳቢው ከሰብዕዊነት፤ ከተፈጥሯዊነት ጋር ያለው ተዛምዶ መለኪያ የሚሆንበት ዘመን በእጅጉ ይናፍቀኛል። ስለሆነም የሰሞናቱን የሙሉ አንባሳደርነት ማዕረግ ያገኙትን ምስል ከምለጥፍ የአዋቂወችን አስተምኽሮ መለጠፍ ተሽሎኛል።
ውዶቹ ክብሮቹ እንዴት ናችሁልኝ? የፖለቲካ ምደባውን ዝርዝር ከሥር አያይዣለሁኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
16/11/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
()))))))))()(((((((()
"ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለ32 ሰዎች የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሹመት ሰጡ"
ፕሬዝዳንቱ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት:-
በውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ በዶር ጌዲዮን ጢሞቲወስ ሥር የሚሆኑ ባለ ሙሉ ሥልጣን አንባሳደሮች
1. አቶ ታገሰ ጫፎ
2. አቶ አገኘሁ ተሻገር
3. አቶ ዛዲግ አብርሃ
4. አምባሳደር ሲራጅ ራሺድ ጁንዲ
5. አምባሳደር መለስ ዓለም ተክዔ
6. አምባሳደር አንተነህ አለሙ ሰንበቴ
7. አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ይግዛው
8. አቶ መላኩ አለበል
9. ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
10. ስንታየሁ ወ/ሚካኤል (ዶ/ር)
11. ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)
12. መስፍን አርአያ (ፕ/ር)
13. ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር)
14. ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
15. አቶ አዳም ተስፋዬ አበራ
16. አቶ አምሐ ኃ/ጊዮርጊስ አየለ
17. አቶ ሳሙኤል አዲስ አለማየሁ
18. አቶ በላቸው አንሺሶ ኬምበጫ
19. አቶ አበበ መብራቱ ክብረት
20. አቶ መላኩ በዳዳ ሰንበታ
21. ወ/ሮ ዑባህ መሐመድ ሁሴን
22. አቶ ዳንኤል ጠንክር አረጋ
23. አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር)
24. ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ
25. ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)
26. አቶ መላኩ ፈንታ ባልቻ
27. አቶ ዣንጥራር አባይ
28. አቶ ተመስገን ጥላሁን
29. አቶ ታደለ ነጊሾ
30. አቶ ዘሪሁን መገርሳ ጅማ
31. አቶ ሽመልስ አዱኛ ባልቻ
32. አቶ አብዱራህማን ጀማል ኑርልኝ
በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን ጽ/ቤቱ አመልክቷል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮችን ሊንኮች ይጫኑ
Twitter: https://x.com/wolkaytzo
WhatsApp:
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ