ልጥፎች

በቃል መገኘት መልካም ነው። በቃል ወስጥ ተስፋ አለና።

ምስል
በቃል መገኘት መልካም ነው። በቃል ወስጥ ተስፋ አለና። የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ አካሄዱን ያቃናለታል“ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie 27.02.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ ·        መነሻ። Ethiopia ፡ ጠ / ሚ ዐብይ ለ 10 ወራት የያዙትን ሚስጥር አወጡት [ ሙሉመግለጫ ] Ethiopian news - PM Abiy Ahmed speech https://www.youtube.com/watch?v=2juObKZP3Io Ethiopia ፡ ጠ / ሚ ዐብይ ለ 10 ወራት የያዙትን ሚስጥር አወጡት [ ሙሉመግለጫ ] ክፍል 2 Ethiopian news - PM Abiy Ahmed speech 2 https://www.youtube.com/watch?v=s0kXEK0zXc8&t=2s ውዶቼ እንዴት ናችሁ? በዚህ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ገለፃ „ይህ ቀን ይመጣል ተብሎ አልተሰበም ነበር፤ ቀድሞ የተናገረ አንድም ፖለቲከኛ አልነበረም።“ ብለዋል እሳቸውን ጨምሮ ይህን ከሥር የለጠፍኩትን ሊንክ ገብቶ መፈተሽ ነው። ቀን ከሌት ነበር የተተጋበት።  ለማገናዘብም ሳተናው ድህረ ገጽም ላይ አብዛኛው የሙግት መንፈስ ይገኛል። የተወሰነው ቢነሳም ማለት ነው። „ምጥን እና ህሊና“ ሳተናው ላይ ባይኖሩም እዚህ አርኬቡ ላይ አሉ ሁለቱም ጹሑፎች። ቀሪዎቹ ደግሞ ሳተናው ድህረ ገጽ ላይ ይገኛሉ። ሳተናው እራሱ በምን ያህል ጥንካሬ እንደተጋ መዳህኒዓለም አባቴ ብቻ ነው የሚያውቀው። ፍጹም ቅን የሆነ ፍጥረት ነው ሳተናው። ያ መልካም ተስፋ በዛ ድህረ ገጽ ውስጥ ባይኖር ኖሮ እ...

እሸት ራዕይን ምራቁን በዋጣ ቻይነት ምህንድስና ብቻ አዋጭ ነው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከስርም።  „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣   የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ   እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 26.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። ደህና ናችሁ ወይ? በአንድ ጉዳይ ዙሪያ ትንሽ ነገር ልል አሰብኩኝ። አብን ሚሊዮነም አዳራሽ በተከታታይ ጠይቆ እንዳልተፈቀደለት ይልቁንም OMN እንደተፈቀደለት ገልፆል። በዚህ አብን ተከፍቷል። ተገልለኩኝ እያለ ነው። ይህን መጠበቅ ያስፈልጋል። ስለምን? አሁንም የዞግ ፖለቲካ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው። አውራው ፓርቲ ደግሞ ኦዴፓ ነው። የምናደምጣቸው ዝበት ያለባቸው ነገሮች ከኦዴፓ የመነጩ ሳይሆኑ ከራሱ ከኢትዮጵያ የዞግ ፖሊሲ ነው የሚመነጨው። አድሎ፤ መገለለ፤ መጫን፤ ጭቆና ዴሞክራሲ በሌለበት አገር ግድ ነው። ተጋድሎው እኮ ሁሉን እኩል የሚያደርግ ቋሚ ሥርዓት ይፈጠር ነው። ለዛ ደግሞ በአንድ ጀንበር የሚሆን አይደለም።  የለውጥ መሪዎቹ እራሱ እኮ ከዞግ ድርጅት የወጡ ናቸው። ሥነ - ልቦናቸው፤ ልምዳቸው ተመክሯቸው በዛ ዶክተሪን የተቃኜ ነው። ከዚህ ለመፈታ...

የኢዴፓ እጩነት /አዲስነት ትልሞሽ/

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የኢዴፓ እጩነት። የሚቀድመው   የትኛው ይሆን? ግን ገነገነ   ወይንስ ገነነ ልበል ከቶ! „የፃድቃን አፍ ጥበብን ያስተምራል፤ አንደበቱ ፍርድን ይናገራል።“ መዝሙር ምዕራፍ ፴፭ ቊጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.02.2018 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ትናንት በዋለው የአጋር ድርጅቶች ይሁን የአጋር ክልሎች ዓወደ ህዝባዊ ስብሰባ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ወጥ ፓርቲነት ድርጅታቸው እንደሚሸጋገር አብስረዋል። ጉደኛው ኢህአዴግ ወደ „ኢትዮጵያዊ ፓርቲነት“ ሊለወጥ ደስ ይላል። ኢትዮጵያዊ ፓርቲነቱን ሲያልም ግን የቋንቋ ፌድራሊዝምን ተሸክም ይሆን?   ብቻ መሰናክሉን ማለፍ ከተቻለ ወሸኔ ነው ማለፊያ። መሰናክሉ የህሊና ለውጥን ነው የሚጠይቀው። የቅርቡን የወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ቃለ ምልልስ ብቻ በቂ ነው። ምን ያህል የዘለበ ገማና ኢትዮጵያ እንዳለባት። አሁን እንኳን በዬቦታው የራስን ሰው ለመሸጎጥ ማራቶኑ ተንጠራርቶ አገር እያመሰ ስጋት እያቀና መሆኑ ነው የሚደመጠው። የሳቸው ቸር ምኞት ግን ሁልጊዜም ይገርመኛል። እስኪ ያሳካላቸው … አሜን አሜን ይሁን ይሁን ብለናል።      ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ እኔ እንዲያውም ኦዴፓ አውራ ፓርቲ ሆኖ ለመውጣት ሥም ሲያድል ብአዴን ተቀብሎ አዴፓ ነኝ ከዛሬ ጀምሮ ሲል ምን አለ ኢዴፓ ብትባል ብዬም ነበር/ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ። / ማለቴ አማራ ክልል ነው እና ኢትዮጵያዊነትን ተሸከም የሚበላው በዬዘመኑ። እነ አቶ በረከት ስምዖን፤ እነ አቶ አዲሱ ለገሰ፤ እና አቶ ዮሴፍ ህላዊ፤ እነ አቶ ተፈራ ዋልዋ፤ እና አቶ አለምነህ መኮነን ...