ልጥፎች

እህት ርዕዮት ከአላዛሯ ኢትዮጵያ ጎን መቆም ያስመሰግናል! ምርቃት!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  ከአላዛሯ ኢትዮጵያ ጎን መቆም ያስመሰግናል። ምርቃት ። „ ሳቅን   እብድ   ነህ፤   ደስታንም፤ ---  ምን   ታደርጋለህ ?  አልኩት። “   መጽሐፈ   መክብብ   ፪   ቁጥር   ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእማ ዚዊዘርላንድ። 25.04.2019 ·         መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=XVYqvBtLNxg&t=2s ቴዎድሮስ ጸጋዬ ለኢሳት የሰጠው ቃለምልልስ እንዳይሰራጭ በአፋኙ ቡድን ታግዷል … ጠያቂዋ ርዕዮት አለሙ የተፈጠረውን እንዲህ ታብራራለች፡፡ Reyot Published on Apr 24, 2019 ·     ልበጉዳይ። የኢሳት ጋዜጠኛ ወ/ት ርዕዮት ዓለሙ „ትኩረት“ ላይ አቻዋን ጋዜጠኛ አቶ ቴወድሮስ  ጸጋዬን የርዮት ሚዲያን ዋና አዘጋጅ ቃለ ምልልስ አድርጋ እንደነበር ትናንት  አዳመጥኩኝ።  ያ ቃለ ምልልስ ወደ ህዝብ ለማድረስ የድርጅቱ የኢሳት ኤዲቲንግ ክፍል ፈቃድ  ስለነሳው ይህን አስመልክቶ ርዕዮት ለርዮት በድጋሚ ተገናኝተው የተደረገ ቃለ  ምልልስ ግርም እያለኝ ነበር የተከታተልኩት። ከኢትዮጵያ አልፎም ውጭ አገር ይህን መሰል መከራ ከኖረ አገር ውስጥ ያሉ  ሚዲያዎች ዕድሜያቸው አጭር ስለመሆኑ ፍንጭ ይሰጣል። እርግጥ ነው ይህ አንድ  አፍታን የሚመለከት አይሆንም። የማያረግዱት ግን ነገ ቀ ጣይ ይሆናሉ ብዬ አላስብም። ኦንግ መሰረቱ እስኪጠ...