የሦስቱም የኃያላን አገሮች የድምፅ አቅጣጫ ሰውኛ መንፈስ አለው።

 

የሦስቱም የኃያላን አገሮች የድምፅ አቅጣጫ ሰውኛ መንፈስ አለው። 
 
• እኛንማ ብልፄው አይሰማንም።
 
« በጽድቅ ከሚገኝ ጥቂት ነገር በዓመጽ
ከሚገኝ ከብዙ ትርፍ ይሻላል።» (ምሳሌ ፲፮፡ ፰።)
 
 
"Ambassador Massinga discussed the importance of advancing religious freedom, interfaith harmony, and the right of all people to worship in peace with His Holiness Abune Mathias, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. The Ambassador underscored how these core American values animate U.S. foreign policy in Ethiopia."
 
#ጠብታ በሰላምታ እንዴት አድራችሁ፤ አርፍዳችሁ ዋላችሁ ማህበረ ቅንነት።
 
(ሀ) የነገረ ቅድስት ተዋህዶን በሚመለከት የአሜሪካ መንግሥት #አይዞሽን የመሰጠረ ዕውነት።
(ለ) የአሜሪካ ሴኔቶች ኢትዮጵያን በሚመለከት #ለመንግሥታቸው ያቀረቡት አቤቱታ።
(ሐ)#የG7 አገሮች እና የአውሮፓ ህብረት ደወል።
 
#አጭር ዕይታዬ።
 
ዘመነ ሪፓብሊካን #ለብልፄው #ጎልደን ወቅቱ ነበር ማለት ይቻላል ለይዋ ብልፄ። ችግሩ ብልፄ #ሲያዳድጥ ነው የባጀው። ሰውኛ ቃና እልኹን ይጨምርበታል። በሙዚቃ የሚበሳጭ እኮ ነው። አይደለም በሃሳብ ሙግት። በተለይ #በሰብአዊነት ላይ ያለው ጫናን ለማሻሻል፤ ቢቻልም ሙሉ ለሙሉ ለመቀየር ጥረት አልቦሽ ነው ዓውራው ፓርቲ ብልጽግና። ፍትህ ቀን ከሌት #ዕንባ ላይ ናት። 
 
የእኛን ኡኡታ፤ የእኛን አቤቱታ አንድም ቀን #ይሁነኝ ብሎ አድምጦን አያውቅም። እስረኞችን ለመፍታት እራሳቸው አመልክተው፤ እራሳቸውን ከሰውም፤ በደለኛ ነኝ ብለው በራሳቸው ላይ መስክረው ነው ወደ 600 እስረኞችን ፈታሁ ያለው ብልፄው። ቁጥሩ እንጂ ሊስቱ እንኳን አናውቀውም። በዘልማድ ታምኖ እንጂ #ዳታው የለንም። በዝርዝር በፆታ፤ በዕድሜ ምንም።
 
የቀሩት 30 ፖለቲከኞች ደግሞ በመሰሉ መንገድ ካልመጣችሁ #አሻም ብሏል። የህዝብ መፈናቀል፤ የድሮን ጥቃት፤ ያላባራው #ጦርነት፤ ሥርዓት አልበኝነት መንገሥ፤ #የንጹኃን ግድያ በከተሞች ከአቅም በላይ ሆኗል። 
 
ብልፄው ደግሞ #የእስካንዳንብያን አገር የሚመራ ይመስል በዓለም ዓቀፍ ጉባኤወች ከረባቱን አስተካክሎ፤ ገበርዲኑን #ፕስ አድርጎ በግሎባልም ይሁን በአህጉራዊ ጉባኤወቹ ይንጎባለላል። የሌላ የደላቸው አገር መሪ ነው የሚመስለው በየመድረኩ አጤ ብልፄው። በራሱም ርዕሰ መዲና ይሁን በክልል የሚያካሂዳቸው ፎረሞች።
 
የብልፄ ሚዲያወችም ሚዲያወን "ትንግርት፤ ታምር፤ ኢትዮጵያ የተገለጠችበት ዘመን፤ የዲፕሎማሲ ስበት" እያሉ ሲያንቆለባብሱት ውለው ያድራሉ። አዲስ ዘመን፤ አዲስ የምርጫ ሂደት፤ አዲስ ካቢኔ፤ አዲስ ፓርላማ፤ አዲስ የፌድሬሽን ምክር ቤት ግን አዲስ የሆነ #ሰውኛ #ቃና ያለው፤ #አይዟችሁን የሰነቀ የሚያጽናና ሁነት የለም።{}። ማጽናናት ይፈራል። ማረጋጋት ይሸሻል። 
 
በምንም ይሁን በምንም ሙሉ ፰ ዓመታት የተሰው ወገኖች ብልፄ በሚመራው ጉባኤ የህሊና ጸሎት ተደርጎላቸው፤ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ፤ የሃዘን ቀናት ሲታወጅ ተሰምቶ አያውቅም። ለምን? ፖለቲካው ሰውኛነት፤ ተፈጥሯዊነት ከውስጡ #ስለተለሞጠ።
የህዝብ #ሳቅ የሚናፍቀው አይመስለኝም ብልፄው። አሁን የሞያሌ ጉዳይን እሰቡት። ደንበር ተሻጋሪ ችግር ሆኋል። ማረጋጋት ሲቻል? 
 
የህዝብ እንግልትን መናፈቅ ካልሆነ በስተቀር አትራፊነቱ አይታዬኝም። ምን አልባት ሞያሌ ተጠሪነቱ ለፌድራሉ ለማድረግ ታስቦ ካልሆነ። አገራዊ ምክክር ብዙ ተዜመለት። ሲጠናቀቅ በሁሉም አቅጣጫ ችግር ቀጠለ። 
 
አዲሱ የአሜሪካ የግማሽ ምርጫ ዘመን ዴሞክራቶችን በብሥራት ያንበሸበሼ ነው። ገና በጥዋቱ #ሰውኛ የሆነ አቅጣጫ አመላካች መንፈስ አየሁበት። አሁን ፕሬዚዳንቱ ሪፓብሊካን ናቸው። በሌላ በኩል በቀጣዩ የዋና ምርጫ ሂደት ስፕሪቱ ዴሞክራቶችን #የሚናፍቅ ይመስላል። ይህ ከሆነ ለብልፄው ቀጣይ የሥራ ዘመን ሰፊ የሆነ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል ብዬ አስባለሁኝ።
 
በተለይ በሰብአዊ መብት አፈፃጸም ጉዳይ ጥረቱ በዳብል አድጎ ማስበል ካልተቻለ? በኢትዮጵያ የቋሚ #ሰላም ጉዳይ። ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮቿ ጋር ስለሚኖራት ግንኙነት። በዲፕሎማሲው ዙሪያም በሚኖራት #የተደማጭነት #ቴርሞ ሜትር ላይ ፈታኝ ሁኔታ ብልፄው ይገጥመዋል ብዬ አስባለሁኝ። 
 
እርዕስ አስይዤ ጽፌዋለሁኝ። ለብልፄው ከጥምዶ ይልቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕንባ በእዮር የመደመጥ አቅሙ ኃያል መሆኑን፤ የሳይለንት ማጆሪቲው የዝምታ አቅም እና ነገን ያሰበ ሁነት ይታሰብበት ብዬ ጽፌያለሁኝ። ብልፄ ጆሮ ዳባ ልበስ ባይ ነው። 
 
ይቅርብኝ፤ ልተወው፤ የህዝብን ድምጽ ልከተል፤ የህዝብን ዝምታ ላድምጥ፤ ለህዝብ ሰላም ቅድሚያ ልስጥ። ለህዝቤ መኖሩን እንዲወድ አዲስ ጎዳና ልከተል። ለህዝቤ ጭንቀቱን፤ ስጋቱን ልቀንስለት። "ላም እረኛ ምን አለን" ላዳምጥ የለም። የፈለገውን በፈለገው ሰዓት ይፈጥማል። ለእሱ ብቻ ይመቸው። ለራሱ እርካታ ይስጠው። በቃ። 
 
አሁን እኔ ሁሉንም አልሞግትም። እስኪ ጊዜ ሰጥቼ ልይ እላለሁኝ። ከፎቶ እንኳን ዓለም ዓቀፍ ሚዲያ የተጠቀሙበትን አልወስድም። እጠነቀቃለሁኝ። እንኳንስ አገር እየመራ ያለ መንግሥት። 
 
ከBBC እና ከአዲስ ማለዳ ያገኜኋቸውን ዘገባ ከሥር አያይዣለሁኝ። ፎቶወቹ የሚዲያወቹ ናቸው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ ማለት እፈልጋለሁኝ ለሁለቱም ሚዲያወች። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
 
ኑሩልኝ አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
12/11/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
 
(1) "ቀጥታ BBC, አምባሳደር ማሲንጋ በአርሲ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ከመንግሥት ጋር እየተወያዩ መሆኑ ተገለጸ"
 
«በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ በአርሲ አካባቢ በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርሱ ጥቃቶች ዘላቂ መፍትሔ እንዲገኝ ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መንግሥት አካላት ጋር እየተወያዩ መሆኑን መግለጻቸው ተዘገበ።
 
"አምባሳደሩ ይህን ያሉት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በጽሐፈት ቤታቸው ተገኝተው በተወያዩበት ወቅት ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው በአርሲ ሀገረ ስብከት በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም ዘላቂ መፍትሔ ማግኘት እንዳልተቻለና አሁንም ስጋቶች እንዳሉ»
 
«አሜሪካ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ውጥረትን ለማርገብ አሰብ ወደብን "በድርድር መሣሪያነት" እንዳታቀርብ አምስት ሴናተሮች ጠየቁ»
«የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ቀጣናዊ ግጭት ሊቀሰቅስ እንደሚችል አስጠነቀቁ"
 
ሐሙስ፣ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
 
"የኢትዮጵያ መንግሥት አሰብ ወደብን በኃይል ለመያዝ የሚያደርገው ማንኛውም ጥረት በአሜሪካ "ተቀባይነት እንደማይኖረው ግልፅ" እንዲደረግ የአሜሪካ ሴኔት አባል የሆኑ አምስት ዴሞክራቶች አሳሰቡ።"
"ሴናተሮቹ፣ አሜሪካ በሁለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በምታደርገው ጥረት ውስጥ አሰብ ወደብ "በድርድር መሣሪያነት እንዳይቀርብም" ጠይቀዋል።"
 
"በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ "የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባሕርን" አለመረጋጋት ውስጥ ሊከትት ወደሚችል "ባለብዙ ግንባር ግጭት" ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት ያነሱት ሴናተሮቹ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዲፕሎማሲያዊ ጣልቃ ገብነት እንዲያደርግ በድጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል።"
 
"ማክሰኞ ኅዳር 1/2019 ዓ. ም. ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ደብዳቤ የጻፉት በሴኔቱ የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ አባል የሆኑ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካዮች ናቸው። የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነት በአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የዴሞክራቶች ፕሬስ ጽሕፈት ቤት ለቢቢሲ አማርኛ አረጋግጧል።"
 
"ፊርማቸውን ካኖሩት ሴናተሮች መካከል የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ከፍተኛ አባል የሆኑት ጂን ሸሂን እና እኚህን ከፍተኛ አባል ይተካሉ ተብለው የሚጠበቁት ክሪስቶፈር ኤ ኩንስ ይገኙበታል።"
 
"የኤርትራ ኃይሎች ትግራይ ውስጥ እንደሚገኙ መዘገቡን" እንዲሁም ሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማቋረጣቸውን የጠቀሱት ሴናተሮቹ፣ "በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አዲስ ጦርነት የመቀስቀስ ዕድሉ ከፍተኛ ሆኖ ይታያል" ብለዋል።"
 
"ኢትዮጵያ እና ግብፅ አንዳቸው የሌላኛቸውን ዲፕሎማቶች ማባራራቸውን አስታውሰዋል። አዲስ አበባ እና ካርቱምም ታጣቂዎችን በመደገፍ እንደሚካሰሱ ጠቅሰዋል። በአገር ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች መቀጠላቸውንም እንዲሁ በደብዳቤያቸው አስፍረዋል።"
 
"ሴናተሮቹ፣ "ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያን፣ ሰፊውን የአፍሪካ ቀንድ፣ ቀይ ባሕርን፣ በባሕረ ሰላጤው የሚገኙ አጋሮቻችንን እና ወሳኝ የንግድ የባሕር መስመሮችን አለመረጋጋት ውስጥ ሊከት ወደሚችል ባለብዙ ግንባር ግጭት ሊያመራ ይችላል" ሲሉ አሳስበዋል።"
 
"ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጠረው "የሌላ አውዳሚ የእርስ በእርስ ጦርነት እና ቀጣናዊ ግጭት ስጋት" አንጻር፣ የዋሽንግተን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ይህንን የሚመጥን "አጣዳፊነት፣ ጉልህነት እና ቅንጅት" እንደሚጎድለው በማንሳት ተችተዋል።"
 
"አሜሪካ ሁሉንም የሚመለከታቸው አካላት ወደ ጠረጴዛ የሚያመጣ እና በአሁኑ ግጭት የሚታዩ የተቀየሩ ሁኔታዎች የሚያንጸባርቅ የታደሰ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲደረግ በአስቸኳይ ልትደግፍ ይገባል" ብለዋል።"
 
"ይሁን እንጂ ይህ ዓይነቱ ንግግር በሚደረግበት ወቅት በኤርትራ የሚገኘውን አሰብ ወደብ በወታደራዊ ኃይል የመያዝ ጉዳይ ከጠረጴዛው ውጪ መሆን እንዳለበት በአጽንኦት አንስተዋል።"
 
"የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱም በማንኛውም ድርድር ወቅት [አሰብ] ወደብን የመያዝ ጉዳይን እንደ ዲፕሎማሲያዊ መሣሪያ እንዳይጠቀም እናሳስባለን" ሲሉ በደብዳቤው አስጠንቅቀዋል።"
 
"በተጨማሪም፣ "የኢትዮጵያ መንግሥት አሰብ ወደብን በኃይል ለማግኘት የሚያደርገው ማንኛውም ሙከራ በአሜሪካ እንደማይደገፍ ወይም ተቀባይነት እንደሌለው ግልጽ መደረግ አለበት" ሲሉ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ መያዝ አለበት ያሉትን አቋም አስታውቀዋል።"
 
"የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በቀይ ባሕር ላይ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት እንዳለው ላለፉት ሦስት ዓመታት በይፋ ሲገልጽ ቆይቷል። የአሰብ ወደብ ጉዳይን በተደጋጋሚ ሲያነሳ የቆየው መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ይህንን ፍላጎት ማሳካት የምትሻው በንግድ ልውውጥ መሆኑን ገልጿል።"
 
"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም "ሰጥቶ የመቀበል አማራጭን" አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ አድሚራል ክንዱ ገዙ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባደረጉት ንግግር ደግሞ፣ ቀይ ባሕርን ለማስመለስ የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የማይሳካ ከሆነ፣ "የመጨረሻው እና የማንመርጠው መፍትሔ" ሲሉ በገለጹት መንገድ የባሕር በር ማግኘት "የማይቀር" መሆኑን ገልጸዋል።"
 
"ሲሆን በቀለለው፣ መለስተኛ ዋጋ በሚጠይቀው፣ በሠለጠነው መንገድ፤ ካልሆነ በመጨረሻው መንገድ ምርጫችን አድርገን መሄድ የማይቀር መሆኑን አምነን እየተዘጋጀን ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።"
 
"ኤርትራ በበኩሏ አዲስ አበባ "ሉዓላዊ የባሕር በር" የማግኘት ሐሳብን በማንሳት "ወረራ" የመፈጸም ዕቅድ አላት የሚል ክስ አቅርባለች።"
"በመስከረም አጋማሽ በመንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በድጋሚ ግጭት መቀስቀሱን ይህ በሁለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት አባብሷል።"
 
"በመስከረም መጨረሻ የኤርትራ ኃይሎች ግጭት ወዳለባቸው የትግራይ ክልል አካባቢዎች መግባታቸው ከተገለጸ በኋላ፣ ኢትዮጵያ "ራሷን ከመከላከል ውጪ አማራጭ እንደሌላት" ገልጻ ነበር። ኤርትራ ይህንን ክስ ውድቅ አድርጋለች።"
 
"የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከሦስት ሳምንት በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበሮቻቸው ላይ ወታደሮችን እንዳሰፈሩ ተናግረው ነበረው።"
 
"ይህ ዓይነቱ የሠራዊት እንቅስቃሴ ደግሞ "ወደ መጠነ ሰፊ ግጭት ሊያመራ ይችል ይሆን" የሚል ስጋት መፍጠሩን አንስተዋል። በዓለም ላይ ሌላ ግጭት እንዲፈጠር እንደማይፈለግም አክለዋል።"
 
"ሩቢዮ በወቅቱ፣ በኢትዮጵያ ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ ያሉትን ታጣቂዎች "ተገንጣይ ቡድኖች" በማለት የገለጹ ሲሆን "የሽብር" ጥቃቶችን ፈጽመዋል ሲሉም ከስሰው ነበር። አዲስ አበባ ውስጥ የድሮን ጥቃት መፈጸሙንም አንስተዋል።"
 
"አሜሪካ በትግራይ ጦርነት ወቅት ኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ግንቦት ላይ ማንሳቷ፣ አሁን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ለተፈጠረው ውጥረት አስተዋጾ አድርጎ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተጠይቀው ነበር።"
 
"ሩቢዮ፣ ማዕቀቡ መነሳቱ አሁን እየተፈጠረ ካለው ሁኔታ ጋር ግንኙነት እንደሌለው በመግለጽ ምላሽ ሰጥተዋል።"
"ማክሰኞ ለሩቢዮ ደብዳቤ የላኩት ዴሞክራት ሴናተሮች ግን፣ ግጭቶች በቀጠሉበት በአሁኑ ሁኔታ ውስጥ "አሜሪካ ለኢትዮጵያ አዲስ የጦር መሣሪያዎች ሽያጭ እንዳይደረግ መከልከል" እንዳለባት አሳስበዋል።"
 
"አምስቱ ሴናተሮች አክለውም፣ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ወደ ቀጣናው እንዳይስፋፋ አሜሪካ እርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል። "አሜሪካ ከኤርትራ፣ ከግብፅ፣ ከሱዳን እና ከሌሎች የቀጣናው ተዋናዮች ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ልትጠቀምበት ይገባል" ብለዋል።"
 
"ሦስቱ አገራት ላይ ይህንን ዓይነቱን አካሄድ በመከተል፣ "ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር፣ ለታጣቂ ቡድኖች የጦር መሣሪያ ወይም ሌላ ቁሳዊ አቅርቦት እንዳይደረግ እንዲሁም ግጭቱን ሊያሰፉ የሚችሉ ሌሎች እርምጃዎችን" እንድታስቀር ጠይቀዋል።"
 
"በሌላ በኩል ደግሞ፣ "ኢትዮጵያ የቀጣናዊ የውክልና ጦርነት ሜዳ መሆን እንደሌለባት አሜሪካ በግልጽ ማሳወቅ አለባት" ብለዋል።"
"ይህንን ደብዳቤ በተመለከተ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኩል በይፋ የተሰጠ አስተያየት የለም። ይሁን እንጂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጦርነቱ ማገርሸት በኋላ በጥቅምት መጀመሪያ ስለ ሁኔታው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተነጋግረው ነበር።
 
"ከኤርትራ ጋር እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት" በተመለከተ በተደረገው በዚህ ንግግር፣ ሩቢዮ "በሁሉም ወገኖች በኩል ውጥረት ማርገብን" እንደሚደግፉ መሥሪያ ቤታቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።"
 
"በወቅቱ ሩቢዮ "ሁሉም የአፍሪካ ቀንድ አገራት የጎረቤቶቻቸውን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር አለባቸው" ማለታቸው ተጠቅሷል። አገራቱ "ድንበር ተሻጋሪ ወረራ እንዳይፈጽሙ" ማሳሰባቸውም ተገልጿል።»
 
3) «የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ቀጣናዊ ግጭት ሊቀሰቅስ እንደሚችል አስጠነቀቁ»
 
ሐሙስ፣ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
 
«የቡድን ሰባት(ጂ 7) አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በፓሪስ ባካሄዱት ስብሰባ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ስጋት እና የድንበር አካባቢ ውጥረት ቀጣናዊ ግጭትን የመቀስቀስ አደጋ እንዳለው እንዲሁም ቀንዱን ሊያተራምስ የሚችል መሆኑን በመግለጽ ጥልቅ ስጋት እንዳላቸው እና ውጥረቱ እንዲረግብ ጠይቀዋል።»
 
«ሚኒስትሮቹ በጋራ ባወጡት በመግለጫቸው ወቅታዊው ውጥረት ይበልጥ ከተባባሰ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት፣ ቀድሞውኑም “አስከፊ ደረጃ” ላይ የሚገኘውን ሰብዓዊ ቀውስ፣ እንዲሁም በቀይ ባህር አካባቢ በሚደረግ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴና ደኀንነት ላይ ከባድ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል አጽዕኖት ሰጥተዋል።"
 
"በመሆኑም ሁሉም ወገኖች “በከፍተኛ ሁኔታ ራስን የመግዛት” እርምጃ እንዲወስዱ፣ ልዩነቶቻቸውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ፣ እንዲሁም ደኀንነቱ የተጠበቀና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖርና በተለይም የሴቶችን እና የሕፃናትን ጨምሮ የንጹሐን ዜጎችን ደኀንነት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።"
 
"በተጨማሪም ሀገራቱ የቀጣናው ሀገራት ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነጻነት እና የግዛት አንድነት መከበር ያለውን ወሳኝነት በድጋሚ እናረጋግጣለን ብለዋል። ቡድኑ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ሕብረት ውጥረቱን ለማርገብ እና በሁለቱ ወገኖቹ መካከል ውይይት እንዲጀመር የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን ብለዋል።" 
See less

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።