ልጥፎች

«አሜሪካ ከሶሪያ አማጺያን ጋር "ቀጥተኛ ግንኙነት" ማድረጓን አስታወቀች» እግዚአብሄር አምላክ ሶርያውያንን #በቃችሁ ይበላቸው። አሜን።

  እግዚአብሄር አምላክ ሶርያውያንን # በቃችሁ ይበላቸው። አሜን። የሰው ልጅ የማሰቃያ፤ የጭካኔ መሞከሪያ ማዕከል ነው የሆነው የሶርያ ህዝብ። የሚገርመኝ የማዝንበትም እንግሊዝ አገር ከሙሁር ቤተሰብ የተፈጠሩት፤ እሳቸውም ሊቅ የሆኑት ቀዳማዊ እመቤቲቱ ልጆች እያላቸው ይህን የሶርያውያን የጭንቅ እና የግፍ ዘመን እንደምን ባለቤታቸውን መክረው ሊያስታግሱ አልቻሉም ? ዲሞክራሲ ከሰፈነበት አገር ተወልደው አድገው ???? የሶርያ ጉዳይ የሰው ልጅ ጉዳይ ነውና ጭንቀታቸው፤ ስቃያቸውእንዲቀር ሁሉም የዓለም ህዝብ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። በዚህ የሶርያ የመከራ ዘመን ፍትህ ያጡ በአገራቸው ኢትዮጵያውያን ከመቃብር እስር ቤቱ ውስጥ እንደወጡ አዳምጫለሁኝ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ። ሁሉም ይቅርብን። የሰው ልጅ ግን የጨካኙች የጭካኔ የሥራ ማስኬያጂ ሊሆን አይገባም በሚለው በህረ ሃሳብ ዙሪያ መሰባሰብ ይገባል። ጨካኞችን ያገቡ አንስቶች ወደ ተፈጠሩበት ሚስጢር ሊመለሱ ይገባል። " ሚ " ብቻዋን ካልሆነች ሚስትነት አካልነት ነውና ጨካኝ የትዳር አጋሮቻቸውን # ሃግ ሊሏቸው ይገባል። ሶርያውያን ይህን ዕንቁ ዕድል ሳያፈሱ የሰላም አማራጮችን በመውሰድ ከሩቅም ከቅርብም ያሉ የጎረቤት አገሮች ጋር ሰላም ፈጥረው ይህ ለ 50 ዓመታት የዘለቀውን ጨካኝ ዘመን እንዳይመለስ አድርገው መቅበር ይኖርባቸዋል። የተንገላታው የሶርያ ህዝብም የተፈጠረበትን ሙሉ መብት ዕውን ያደርግ ዘንድ ሁሉ ነገር ሊመቻችለት ይገባል። ሃይሞኖት ሆነ የፖለቲካ አቋ...