ልጥፎች

Das Schweiz-Team ist mein Held.

ምስል
  Das Schweiz-Team ist mein Held.     Die Schweizer Fußballnationalmannschaft hat das Potenzial, mit jeder anderen Fußballmannschaft der Welt mitzuhalten.   Natürlich gibt es in der Schweizerische - Fußballmannschaft keinen Spieler wie Messi, keinen globalen Influencer wie Cristiano Ronaldo, der von den Schiedsrichtern an jedem Spieltag besonders geschützt wird.    Abgesehen davon ist die Fußballmannschaft von der Schweiz ein fähiges Team. Daher stellte er bei der Weltmeisterschaft 2026 seine Vielseitigkeit, sein Können und sein Talent unter Beweis.   Obwohl der Schiedsrichter im Spiel zwischen der Fußballmannschaft von der Schweizer und Kolumbien grossen Druck ausübte, gelang es Nati, alle Herausforderungen zu meistern und zu gewinnen.   Der Schiedsrichter des Tages hatte auch Einfluss auf das Spiel der Schweizer Mannschaft gegen Argentinien.   Doch der Schiedsrichter des Tages ging schweigend vorbei und beobachtete wiederholt die Fouls de...

"#እስረኛ #ይፈታል።" (ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።)

  " #እስረኛ #ይፈታል ።" (ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።)   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፈጠርልኝ።" አሜን።   በሰሞኑ የፓርላማ ጉባኤ ይህን ተናግረዋል ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ። ዜናው ጥሩ ነው።    ቀድሞ ነገር ሃሳብ ስለምን ይታሰራል?   ተጎድቻለሁኝ፤ ተገልያለሁ ሲል አቤቱታ በብዕሩ፤ በሰላማዊ ሰልፍ፤ በድምጹ ያቀረበ ኃይል ለምን ይታሰራል? በነፃነት ዙሪያ የተጋ፤ ያስተባበረ፤ ያደራጄ የመራም ሊሆን ይችላል ለምን ይታሰራል?   በሌላ በኩል ብልፄውን ደግፎ ያሻውን ቢጽፍ፤ ቢናገር፤ ቢያደራጅ፤ ቢያስተባብር፤ ቢመራም ሃግ የሚለው የሌለ በአንድ አገር ውስጥ አንዱ በሙሉ ይለፍ የሚንፈራሰስበት፤ ሌላው በካቴና የሚቀጣበት ሃሳብ በማቅረብ ብቻ ለምን ይህን ያህል የሰፋ የመብት የነፃነት ክፍተት እንደምን ሊፈጠር ይችላል?   ለዛውም በህወሃት ዘመን በሙሉ አቅም በብዕሩ የታገለ፤ ያታገለ ሰብዕና እንደምን ይታሰራል? አሁን ላለው የሥልጣን መንበር የሁሉም የተሳትፎ ጭማቂ አይደለምን?   #የእስረኛ ፍቹ ………   1) በመላ ኢትዮጵያ በህወሃት ዘመንም በብልፄው ዘመንም ያሉትን ያጠቃልላል ወይ? #የኢህአፓ እስረኞችም ስላሉ። 2) በማይታወቅ #በተሰወረ እስር ቤት ያሉትንስ ይጨምራል ወይ?   3) የማይነገርለት፤ አስታዋሽም ያጣው " #የቁም እስረኞችን" እነ አቶ ኦባንግ ሜቶን ይጨምራል ወይ? (አቶ ኦባንግ ሜቶ ድምጹ ስለጠፋ ሌሎችም እንዲሁ የቁም እስርም ይኖር ይሆን እላለሁኝ በግሌ። 4) ኦነግ ኢትዮጵያ ሲገባ አቀባበሉ በ1300 የአዲስ አበባ የኢትዮጵያኒዝም አቀንቃኞች ከጦላይ እስር ቤት ከተፈቱት የተወሰኑት ተለይተው እስራቸው የቀጠሉ አሉ እና እነሱን ይመለከታል ወይ? 5) ከአርቲስት ሃ...

ቤተ - ሥርጉትሻ #ዘለፋ፤ #ስድብ፤ #አሽሙር አይሰተናገድበትም! አቃሎ፤ አጣጥሎ ሳቅ ከተጨመረበት #ይፈቀዳል። ሳቅ የናፈቀን #ህዝብ ስለሆን።

ምስል
  ቤተ - ሥርጉትሻ #ዘለፋ ፤ #ስድብ ፤ #አሽሙር አይሰተናገድበትም!   አቃሎ፤ አጣጥሎ ሳቅ ከተጨመረበት #ይፈቀዳል ። ሳቅ የናፈቀን #ህዝብ ስለሆን።   "እንሆ አሳባችሁን፥ የመከራችሁብኝንም፡ ክፋ ምክር አውቄዋለሁ።" ይላል የእግዜሩ ቃል። (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፯)     #ምዕራፍ ፲፱።   ፌስቡክ እጅግ በጣም ዘግይቼ ነው የጀመርኩት። የእጅ ስልክም አልነበረኝም። የስልክ ፍቅርም የለኝም። መደወልም፤ መቀበልም ለእኔ ሁለቱም የጭንቀት ማዕከሎቼ ናቸው። እኔ ኢሜል ነው የምወደው። መልሴ ፈጣን፤ በሙሉ አቅም የምሳተፍበትም መስክ ነው። ፌስቡክ ስጀምር ይህ ቤት እንዲህ የተከበረ፤ ጨዋ፤ ከትርፍ ነገር የታቀበ፤ ዘለፋ፤ ስድብ የማይዘወተርበት አልነበረም። ከዚህም አልፎ በማህበረሰባችን የሚነወር ፆታዊ ጉዳዮችም በይፋ #የሚቀነቀኑበት ነበር።   ሌላው የሰውን ልጅ በእንሰሳ ምስል መስራት ይዘወተርበት ነበር። ምስልን መዘቅዘቅ፤ ኤክስ ማድረግብ ተዘውትሮ የሚሠራበት ነበር። የሃይማኖታዊ ጉግሱም ጠና ያለ ነበር። ሁሉንም መስመር ለመያዝ ጊዜ ጠይቋል። ተደክሞበታልም። ተለፍቶበታልም።   አንድ ጊዜ ፖለቲካል ሳይንስ ያጠኑ በዕውቀት፤ በተመክሮም ዝልቅ አቅም ያላቸው፤ ሚዲያም አላቸው፤ በአንድ ዕውቅ ሌላ ፖለቲከኛ ላይ ፍየል በአፋቸው ላይ እየሸናች ፎቶ ለጠፋ። ውስጤ አዘነ። ሃዘኔን ዋጥ አድርጌ መራራ ስንብት ሆነ። ምክንያቱም ለቀጣዩ ትውልድ፤ አክሰሱ ላላቸው ታዳጊወች ይህን መሰል የፈጣሪን ፍጡር የተዳፈረ ትልልልፍ የሚያስተምረው በጎ ነገር ስለለ።    እኒያው ሰው ከአንዲት የቅርብ ወዳጄ ጋር ፌስቡክ እያዬን በእሷ ኮንፒተር ያልሆነ ነገር ፃፋ። እኔም ይህን ቃል አይጠቀሙ ብዬ ፃፍኩኝ። ...

ፈረንሳይ {} ስፔን #ሁለት። ስፔን #ለዋንጫ እጮኛ ስትሆን ፈረንሳይ ደግሞ #ለደረጃ።

  ፈረንሳይ {} ስፔን #ሁለት ። ስፔን #ለዋንጫ እጮኛ ስትሆን ፈረንሳይ ደግሞ #ለደረጃ ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በዳህላስ 70ሺህ ተመልካች በተገኘበት የሁለት ምርጥ የአውሮፓ ቡድኖች ጨዋታ አንዱ #ለሙሽርነት ሌላው #ላጃቢነት ሁኗል መቋጫው። እቴጌ ድንቡልቡል #ማጫ እያማታች ነው። ሌላም እየጠበቀች ነው። ማጫው በለጥ ላለው፤ ጥሩ አድርጎ ላጎናት፤ ለሰለቃት ታደላለች።    በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በከፍተኛ ራንክ ለዋንጫ የታጨው የፈረንሳይ ቲም፣ #ምን #እንደነካው አላውቅም በዛሬው በአገራቸውም ዛሬ ብሄራዊው #በዕላቸው ነው። ቀን ሳይቀናው ቀረ። ዛሬ ፓሪስ ምሽቱን እንዴት ታሳልፍ ይሆን?   የፈረንሳይ ቡድን እስከ 35ኛው ደቂቃ ድረስ #ምንም የግብ ሙከራ አላደረገም። አንድስም እንኳን። አይገርምም። በአንድ ጨዋታ ሦስት ጎል ያስቆጠረው ኮከብ አላቸው። ማፔም የተሰጠው ነው። በነፍስ ወከፍም በወልም ጠንካሮች ናቸው። ግን ዛሬ?    ይልቁንም ከመጀመሪያው የውሃ እረፍት በፊት #ስፔን የቅጣት ምት አግኝቶ አንድ ጎል አስቆጠረ። ከውሃ እረፍት እስከ ግማሹ መደበኛ እረፍት ጊዜ ድረስ ፈረንሳይ #ምንም ዓይነት የግብ ሙከራ ሳያደርጉ አንድ ለምንም ውጤት እረፍት ወጡ።   ከእረፍት መልስ የፈረንሳይ ቡድን ምንም ያሻሻሉት ነገር ሳይኖር ጨዋታው ቀጠለ። ስፔኖች አንድ መደበኛ የጎል ዕድል ቀንቷቸው #ሁለት #ለምንም መምራት ጀመሩ። በቀሪው ደቂቃ አካክሰው በአቻ ውጤት ጨዋታው ተራዝሞ ተጨማሪ ዕድል ይኖራቸዋል ብዬ ሳስብ፤ በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ የዕለቱ ጨዋታ ተጠናቀቀ።   ……… #ከዛስ ? ትንሽ ልመለስ መሰል።    ከዛማ በ64...