ልጥፎች

ማርከሻ!

ምስል
የብላሽ ግርሻ - ማርከሻ! ሥርጉተ ሥላሴ ( Sergute © Sselassie )   27.02.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „እግዚአብሄርም አለ ሰውን በመልካችን  እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ።“ ( ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፩ ቁጥር፳፮።) ይድረስ ለጸሐፊ ሰርጸ ደስታ እንደምን አሉልን? በንጹህ ህሊና እና በፍጹም ቅንነት  ሰላምታዬ ይድረሰዎት እላለሁ እኔ እህተዎት ሥርጉተ ሥላሴ ከዚህ ከኮሽ አይሊቷ ሲዊዝዬ። „ ማስጠንቀቂያ ለዶ / ር አብይ አህመድ ! ( ሰርፀ ደስታ )“ በለው ! እንዲህ ነው ማስጠንቀቂያ ¡ ስለ አበዙት ትንሽ ሃሳበዎት ሊደፈር ይገባል። ግርሻን ፌጦ ስለሚያስፈልገው። ንግግር ተስጥዖ ነው። ክህሎቱ ደግሞ በስልጠና የሚገኝ ነው። የሚገርመው ዶር አብይ አህመድ ተናገሪ ብቻ ሳይሆኑ ብቁ አድማጭም ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም ራዲዮ ጋዜጠኛ ስልጠና ላይ የድምጽ መግራት ልዩ ኮርስ አለው። ይህም ጸጋቸው ነው። ቃናው፤ ለዛው፤ የ እጅ እንቅሰቃሴው፤ የ አትኩረት ሁነቱ፤ የፊድ ባክ ቁጥጥሩና አስተዳደሩ ብቁ ነው። እሚወጣለት የለም። በራሳቸው ውስጥ የሚኖረ ናቸው።ሙግት ላይ ተናጋሪ ተሁኑ ማድመጥ ካልተፈቀደ የንግግር ጥበብ ሥነ - ምግባሩ አይፈቅድም። የሆነ ሆኖ እርስዎ የሄዱበት መንገድ ያሳፍራል።   http://www.satenaw.com/amharic/archives/51605 ·          ወ ዳጄ --- እንዲህ። የፈለጉትን ዕውነት ነው ብለው መከተል ብቻ ሳይሆን ማምለክ መብተዎት ነው። ከቻሉም መሬት ላይ የሚሆነውን ማድረግ። ድርጅታዊ ነፍስ አዬር ላይ አይፈጠርም - በስልክ፤ ሰብሉ በሞባይል - አ...