ዝበት ወይንስ ስክነት?
እንኳን ደህና መጡልኝ። ዝበት ? ስክነት ? „በዓመታት መካከል ትታወቅ፤ በማዓት ጊዜ ምህረትን አስብ“ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። · ማነው ጥፈተኛው? ማነውስ ይቅርታ ጠያቄውስ? https://www.youtube.com/watch?v=a7aWV6r9Q6k&t=3s ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚነሱ ግጭቶች ላይ የምሁራን አስተያየት Fana Television Published on Jan 10, 2019 ጋዜጠኛ አቶ አዳም ታደስ /አወያይ/ · ማካሄጃ። "ፕ /" አባባው አያሌው በአማራ ቴሌቪዥን አሁን ከሆነ ይቀርባሉ ለቃለ ምልልስ፤ ያው እሳቸው የሚፈ ለጉ ት የአማራ ብሄርተኝንት ጎልቶ ሲወጣ ወይንም ዩንቨርስቲዎች ችግር ተከሰተ ሲባል ብቻ ነው። ከዚህ ያለፈ፤ ከዚህ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተወክለው አይተን አናውቅም። ሌላው ቀርቶ ከታሪክም ከጥበብም አንጻር ብርቱ ሰው በሚያስፍልጋቸው አገራዊ ጉዳዮችም እንዲሁ ያን የመሰለ በፍጹም ሁኔታ የሚመሰጠው ብቃታቸው እዬባከነ ነው የሚታዬው የተገባውን ቦታ አላገኝም እንደማለት። ውጭ ያሉ ሊቃናት አገር እንዲገቡ ሲፈለግ አገር ውስጥ ላሉት ሊቃነት ያላቸውን አንጡራ ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል ያለው ዕድምታ ፈተናው አይሎ አያለሁኝ። መሰረታዊ ምክንያቱ ብቃት አቅም እውቅት ሳይሆን መለኪያው የፖለቲካ ድርጅት አባልነት ስለሆነ፤ የኮታ ጉዳይ ስለሆነ፤ ይህ ብቻ ነው እንዳልል ደግሞ ከዚህ የወጡ ሹመቶች እና ዕውቅናዎች ሲሰጡ ደግሞ አያለሁኝ፤ ...