ልጥፎች

የኦዴፓ መግለጫ እና ዕድምታው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ለአንቲፔን ደንበኞች ጥሩ የለሽታ መርፌ ነው። „ኃጢያት የሚሠሩ በውን አያውቁምን? እግዚአብሔርን አይጠሩትም“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 10.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።                       ተዚህ ሃቅ ጋር "ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው" ችሎት ላይ ይገናኝ።                                                    ወኔው ከኖረ .... ውዴቼ ትንሽ ስለ አገረ መንግሥት መሪ ስለሆነው ስለ አውራው እጬጌው ኦደፓ መግለጫ ትንሽ እንወያይ። እነ አጅሬ ያውቁበታል አንዱን ሳናደማ እና ከውስጣችን ሳናውህደው ልክ እንደ ፌንጣ መንፈሳችን ሲያሰዘልሉት ነው የባጁት። ከእንግዲህ ግን በሰል አድርጎ መጓዝ ያስፈልጋል። እንደ ሰንጋ በቅሎ የተጫነውን ተሸክመን ቤሎ ያዥ ከመሆን ለማዳን።  ያው መቼም የኦዴፓ የልማት ፕሮፓኦጋንዲስቶች ላልሆናችሁት ነው ይህን የምለው። እውነት ጋሻ እና መከታችሁ ለሆናችሁ ቅኖች ብቻ … ጥምዝ ሰው ክፍሌ አይደለም። ግርባነትም ርስቴ አይደለም፤ ልብ እንዲገጠምልኝም እማልሻ ሞገደኛ ሴት ነኝ ...  ·                መነሻ። በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ...