ልጥፎች

" Evita-Kult in Argentinien"

ምስል
  እ ንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።   „ምስጉን ነው በክፉወች ምክር ያልሄደ በኃጢያቶኞችም መንገድ ያልቆመ “ ( መዝሙር ምዕራፍ 1 ቁጥር አንድ። )   ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ ቁራሽ እንጀራ በሰብለ ህይወት አዝመራ በቢሆነኝ ብራ ለራህብ የሚራራ።     · ቀ ዳማዊ እምቤቷ አርጀንቲናዊቷ የተግባር ልዕልተኢቫ / ኢቢታ / ህይዋን / ማርያ ፔሩን ማን ናት ?   · በዝቀተኛ የኖሮ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያ ወጣቶችስምን ይማራሉ ?   ቀ ዳማዊት እምቤት ኢቫ ፔሩን አርጀንቲናዊ የጥበብ ሰው፤ የፖለቲካ ሰው፤ የቲያትር እና የፊልም አክተር፤ የሙዚቃ ተጫዎች የነበረች ድንቅ እጹብ ድንቅ የመብት ተሟጋች የነበረች ሴት ናት። በዘመን ማሀከል አንድ ጊዜ ብቻ የምትፈጠር። አርጀንቲናዊቷ ቀዳማዊት እመቤት ኢቫ / ኢቢታ ፔሮን / ከመካከለኛ ቤተሰብ ከጋብቻ ውጪ የተወለደች ልጅ ነበረች። እሷ በኖረችበት ዘመን ይህ እንደ ነውር ይታይም ነበር። ኢቫ ፔሩን ገና በጥዋቱ ነበር መንገድ ላይ የወጣችው። ከዛም በጾታዋ መተዳደር ጀምራም ነበር። በ ዕድል አጋጣሚ ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ቁልፉ ተገኜ እና ወደ የቲያትር ትወናው ዓለም ተቀላቀለች። የቲያትር ትወና ከአርቱ ሁሉ የተለዬ ነው ለእኔ። ከህዝብ ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ የጥበብ አውደ ምህረት ነውና። ከታዳሚው ጋር ቋንቋው ገጽ ለገጽም ነው። እርምቱም ሐሤቱም እንዲሁ። የጓዳ ግንኙነት የለውም። ...