ልጥፎች

#እርህርህናዬን #አልወቅሰውም።

ምስል
  #እርህርህናዬን #አልወቅሰውም ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     አገር እያለሁኝ ከቤተሰብ ጉዳት ከደረሰ ለተጎዳ ሳይሆን እሷ ምን ትሆናለች ነው ጭንቁ። እግዚአብሄርን ባገኜው የምጠይቀው ውስጤ በምን #እንደተሠራ እንዲነግረኝ ነው። ስልክ እማልወደውም፦ እማላነሳውም በፍራቻ ምክንያት ነው። የቤቴ ደወልም በጣም ነው የሚቀፈኝ። ውጭ አገር ለሚኖሩ ቤተሰቦቼ የሚልኩልኝን ዕቃ በአደራ ደብዳቤ እንዳይልኩ ሁሉ ነው እምነግራቸው። የቤቴ ደወል በፖስተኛ እንዳይጨናነቅ። የሆነ ሆኖ ፈንጠዝያ አያጓጓኝም። ፈንጠዝያም ውስጥ ኑሬ አላውቅም። የምመርጠው ከተቻለ ጸጥታ። …   … ካልሆኑም ጉዳት በደረሰበት አካባቢ መገኜት እና የድርሻዬን መሞከር ነው። በምሞክረው ውስጥ ብቻ #ሐሤት አገኛለሁኝ። ሐሴት ከደስታ በላይ ነው በእኔ ፍልስፍና። ለነገሩ የአደኩበት ቤተሰብ በልደት #ነዳያን #ድንኳን ጥሎ #አደግድጎ ታጥቆ #ከሚያደግፍ ከሊቀ ሊቃውንታት ደጋግ ቤተሰብ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የተፈጠርኩበት ዕለት እና ሳይንቲስቶች የሚሉት የደም ዓይነቴም ሊሆን ይችላል በተጎዳ አካባቢ ብቻ ህሊናዬ እንዲያተኩር የሚሆነው። ለዚህም አምላኬን አመሰግነዋለሁኝ፦ ይህን ስለሰጠኝ። እጅግ ብጎዳበትም።   ከተሰደድኩኝ አንድም የቤተሰብ መርዶ በቅጡ ነግሮኝ የሚያውቅ ደፋር የለም። ህልሜን አምናለሁኝ። በህልሜ ራሴን አርድቼ የሃዘን ጊዜዬን በመጨመት ይከወናል። ከሠርግ ቤት - ሃዘን ቤት፤ ከወል የፌስታ - መሰናዶ የታመመ መጠዬቅ ይቀናኛል። ይህን ፈጣሪዬ መርቆ ስለሰጠኝ አመሰግናለሁኝ። ብጎዳበትም ግን የውስጤ እርካታ ምንጩ ይህ በመሆኑ #ርህርህናዬን #መቼውንም #ቢሆን #አልወቅሰውም ። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተጠለፋ ሲባል ከ2 ወር በላይ ጥቁር ለብሻ...

.

ምስል
 

ዳኛህ

 በሰው ልጅ የመኖር ፈተና ውስጥ ግዙፋ ፈተና ባልተረጋጋ መንግሥት ሥር የታፈነ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ግራጫማ መሆኑ ነው። ያስፈራል። ይቀዘቅዛልም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021  በሰው ልጅ ፈተና ውስጥ እራስን መከዳት የመሰለ የሞት መንገድ የለም። እራሳቸውን ያመኑ ጭምቶችም፣ የስኬት ጎዳናም ናቸው። ትውልድ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021  በነደደ መከራ ውስጥም ቢሆን ፈጣሪህ እንዳለ እሰብ። መድህንህ ነውና። ማብረዱ ይቻለዋልና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/01/2021    ስኬትህ ቅንነትህ ይሆን ዘንድ ፍቀድለት። ህሊናዊነት የሚገኘው በቅንነትህ ልክ ነውና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021  ዳኛህ ተግባርህ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021 ዕውነት ክንንብህን ገልጣ እርቃንህን ታሥቀርኃለች። በሦስት ዓመቱ ጉዞ "ኢሱ" እና አብይዝም አልተዋወቁም። ከእንግዲህ ግን በደርበቡ ነው። ትንታ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021   #ክፋነት #በምድራችን #የሚተንበት #የተፈጥሯዊነት # #የነፃነት #ዘመን #ይናፍቀኛል #በጣሙን ! ሥርጉትሻ2024/03/29    ክፋወች ክፋት አያልቅባቸውም። ማምረቻቸው ግዙፍ ፦ጎታቸውም ሰፊ ነው ለክፋት ክዘና። ጥሪታቸው ክፋት እና ክፋነት ስለሆነ። ደጎች ደግሞ የክፋት ጎተራ ስሌላቸው በክፋት እረገድ መናጢ ደሃ ምስኪኔታ ናቸው። ታድለው። ውቦቼ በሉ ቸር ሁኑልኝ፦ ቅንነት ስንቃችሁ #ቀናነት ጥሪታችሁ ይሁንልኝ። አሜንወአሜን። ሥርጉትሻ 2024/03/29      

ያልተረጋጋ

 ያልተረጋጋ መንግሥት ያላት አገር ህዝብ እራሱን በራሱ ይጠብቅ፣ ለራሱ ዘብ አደር ይሆን ዘንድ ግድ ነው። በረገበ አስተዳደር የመኖር ዋስትና የለምና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021

#አትፍራ!! አጋጣሚውን ተጠቀም እና ቤትህ ተቀመጥህም አንብብ!!!

ምስል
      #አትፍራ !! አጋጣሚውን ተጠቀም እና ቤትህ ተቀመጥህም አ ን ብብ!!! ///መቸም የአባቶች ጥበብ እና ስልጣኔ!/// ''የተወሰደ'' ••✦ « የቀደምት ኢትዮጵያያን ✦•• ••✦ በራሪ ፈረስ (ፔጋሰስ) » ✦•• «Pegasi Aithiopes» ♡┈••✦ #ሼር_share_ሼር ✦••┈♡ ✦ የተፈጥሮን ኡደት ጠብቆ መኖር ሰዋዊ ነው ፤ ተፈጥሮን ማዘዝ መቻል ግን ልእለ ሰብዕና ነው ። ከዚህ ቀደም ስለ አፄ ሰንደቅ አለማ ገድል ስናነሳ አንዱን እፅዋት ወደ ሌላው እፅ የአንዱን አውሬ ዘር ወደ ሌላው እንዲዳቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅሎን ከአህያንና ፈረስን ጋር በማዳቀል ያስገኝ ኢትዮጵያዊ ጀነቲክስ ኢንጅነሪግ አባት እንደ ነበር አይተናል። : ✦ ዛሬ ደግሞ ወደ ባህር ማዶ እናቅናና የጥንት ኢትዮጵያያን 'በራሪ ፈረስ' ይጠቀሙ እንደ ነበር ከኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍት የተገኙ ማስረጃዎችን እንዲሁም የውጭ ፀሐፊያን በዚህ ጉዳይ ምን እንዳሉ እናያለን ። የጥንት ኢትዮጵያያን በዓለም ላይ ስልጣኔን ሲዘሩ የሚያገኟቸውን አህጉሮችን እና ውቅያኖሶችን በስማቸው እየሰየሙ.....ሲሻቸውም በሰማይ ላይ ግዛታቸው ሲያስፋፉ....በስነ - ተፈጥሮ ላይ ሲመራመሩ የኖሩ ድንቅ ህዝቦች ናቸው። : ✦ ታዋቂዋ አሜሪካዊት የታሪክ ተመራማሪ ድሩሲላ ዱንጅ.....የጥንትቶች ድንቅ ኢትዮጵያያን በርካታ የስነ ጥበብ ውጤቶች ባለቤቶች ናቸውነ ፣ በዘመናቸው የኤሌክትሪክ ባህሪያትን በማወቃቸው ከሜታል(ብረት) #ሮቦቶችን የሰሩ ፣ #Pegasus (በራሪ ፈረሶች) የፈበረኩ ጥበበኞች ..." ናቸው። : ✦ ፕሊኒ Natural History በተሰኝ መጻሕፉ ላይ በራሪ ፈረሶች በመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተዳቀሉ እና አካላዊ ገፅታቸውም ባለ ...

29.03.2020

  ጠያቂ ያጡ ተስፋዎች እንደ ወጡ ቀሩ። ቤተሰብም ዋዬ እንዳለ፣ አዛኞችም እንደ አነቡ? ህም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ፅናት።

ጋሽ ስብሀት ገብረእግዚአብሔር እንዲህ ይል ነበር

ምስል
  ጋሽ ስብሀት ገብረእግዚአብሔር እንዲህ ይል ነበር     " በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል። ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"    Tadios Lidetu  

አልገባኝ ያለው ነገር

 አልገባኝ ያለው ነገር ለምንድን ነው #በብርቱካማው ክስተት የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ኢትዮጵያ #በጠላት የተወረረች ይመስል ይህን ያህል የአብይዝም ሥርዓት የታወከው?! ትክክለኛው ዳኝነት ያለው በህዝብ ህሊና ነው።  ለምን ግራ ቀኙን አጥንቶ ህዝብ ዳኝነቱን እንዲሰጥ አይተውትም። ትምህርት ሚኒስተር እራሱ #መግለጫ እንዲሰጥ ተደረገ። ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። የአማራ ህዝብን በሚመለከት ከደቃቁ እስከ ገዘፈው ጉዳይ ድረስ ያለው ነገር እራሱን የቻለ #የምርምር #ተቋም ያስፈልገዋል።  ሰሞኑን እኮ 100 ተጓዦች በሁለት ዙር ከ፬ ኪሎ አፍንጫ ሥር ታግተዋል። ህዝብ በአውሮፕላን ካልሆነ በዬብስ መጓጓዝ አቁምም ነው መልዕክቱ። ሹፌሮችም #የጎዳና ላይ ኑሮ ይቅናችሁ ነው። የሰው ልጅ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሻሸመኔ ላይ ተሰቅሏል - ተገድሎ ተቃጥሏል - ታስሮ ተገድሏል። ያልታዬ ማዕት አለን በምድሪቱ? ምነው ኢትዮጵያ አንደበት በነበራት????  ሥርጉትሻ 2025/03/29

ስለምን ይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #አጽናኝነትን እንደ ጦር የሚፈራው?

ምስል
 ስለምን ይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #አጽናኝነትን እንደ ጦር የሚፈራው?  ለምንስ ይሆን #አይዟችሁ #ባይነት እንደ ወንጀል የሚታዬው?  በኢትዮጵያ ፖለቲካ #ሰዋዊነት #አደጋ ውስጥ ነው።  ይህ አካሄድ ጨካኞች፦ በጭካኔያቸው ጀግንነት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው።  የኢትዮጵያ ፖለቲካም ለጨካኞች ሽፋን ስለሰጠ የፖለቲካው አውራ መሪ እኔ ነኝ፤ ሥራም ሠርቻለሁ ይላል።  ፖለቲካ ሠሪው #ሰው ነው። ፖለቲካ የሚሠራውም #ለሰው እና #ለተፈጥሮ ነው።  ስለሆነም #ሰውኛነት ቢያስመሰግን፤ ቢያስከብር እንጂ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህግ #መሳደጂያ ሊሆን አይገባም።  የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሰውኛ ማዕቀፍ ውስጥ #ያፈነገጠ ነው።  ይህን ማረቅ እና ማሰተካከል ይገባል። #ሃግ ሊባል ይገባል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተፈጥሮው አዛኝ፤ ሩህሩህ፤ ደግ እና አጽናኝ ነው።  ሃዘኑን በወል በህብራዊነት አስከብሮ የኖረ ህዝብ ነው።  ይህን #ጸጋውን #የሚገፍ #አሳቻ ዘመን ላይ ነውና በጥሞና የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያስብበት ይገባል። ገዢወቹንም ሊያርማቸው፤ ሊገስፃቸው፤ ሊቆጣቸው ይገባል።  ሥርጉትሻ2025/03/26

አገር እናት ናት። እናትም አገር ናት። እናት እና አገር #ትርታ ናቸው ለመኖር።

ምስል
    አገር እናት ናት። እናትም አገር ናት። እናት እና አገር #ትርታ ናቸው ለመኖር።  መኖርም ሆነ አገር እናትነትን #ያከበሩ ሊሆን ይገባል።  እናትነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከክብሩ በታች እዬታዬ ነው። ትናንትም ዛሬም። ሁልጊዜ መገበር።  እናትነት የዓለም ገዢ #ምህዋር ነው። እናትነት ድንቅ እና ውድ ፀጋ ነው።  እናትነት አስማሚ፤ አረጋጊ፤ አጽናኝ እና ኃላፊነትነትን እና ተጠያቂነትን በተፈጥሮው ልክ ገቢር ላይ የሚያውል #ምሩቅ በረከት ነው።   #እናትነት #የፈጣሪ #የመመረቅ #መግለጫ ነው ማለት እችላለሁኝ።  እናትነት የፈጣሪ እና የተፈጥሮ የሚስጢር #ምስባክ ነው። እናትነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን #ሰቀቀን ውስጥ ነው የኖረው።  እናትነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሃዘን ድንኳን ውስጥ መኖሩ #እንዲከትም የተገደደ ክስተት ነው።  እናትነትን ሳያከብሩ መቅረት የአገርን #ምርቃት ከጉልላቱ ያስነሳል። የፈጣሪ ቁጣን መካችም የለም ከመጣ አፋጣኝ እርማት ሊወሰድ ይገባል። እናትነትን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በእጅጉ እዬተዳፈረው ነው።  የኢትዮጵያ እናቶች #ጡታቸውን አሽተው ቆርጠው ከረገሙ ወዮልሽ ኢትዮጵያ ነው። ይህን በጣም ነው እኔ እምፈራው።  እናትነት በኢትዮጵያ ጭቆና ውስጥ ነው። ግፍ እዬተፈጸመበት ነው። የእናቶች ንቅናቄ ከተነሳም አደጋው ዘርፈ ብዙ ነው። ብልጽግና እናትነትን ከጥንስሱ ጀምሮ ፈተና ውስጥ ጥዶታል። ተንገርግቧል - እናትነት።

መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው???? …

ምስል
  መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው???? ……   "አቤቱ ፀሎቴንም ስማ ልመናዬንም ቸል አትበል።"  (መዝሙር ፶፬ ቁጥር ፩)     • በጭካኔ በሰለጠኑ፤ • በበቀል በተነከሩ፤ • በቂም በበቀሉ፤ • በጥላቻ በተዘፈዘፉ፥ • በበታችነት ስሜት ወፈፍ ባሉ፥ • በህሊና አቅም ማነስ በሚባትቱ፤ • በአንጃ ግራንጃ ግንዛቤ ዬሚውተረተሩ፤   • በተለጠጠ ፍላጎት አገር ያህል ቁምነገር በከንቱነት ዬሚመሩ ዘመነኞችን ለመታገል _ መበሳጨት _ መጣደፍ _ መንቦጅቦጅ _ ሱሪ በአንገት አያዋጣም።    • ብዙ ነገር ዬተፈጠርንበትን ባዕት፤ ዬዘር ሐረግ፤ ዬአልረገጥም ጽኑ አቋም እና አሻምነት ባይመቻችሁ እንኳን በጣም በርቀት ዬሚታዩ ዕሳቤወችን እህ ----- ብሎ ማድመጥ ይገባ ነበር ቤተ ሰለሞን ላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አላችሁ። ግን ዓለማችን ዬጆሮ ገብያ አልከፈተች። በስልተ ቢስ እሰጣ ገባ፤ በግርግር ፖለቲካ፤ ወዳጅ እና ተቀናቃኝን ባለዬ ዬዝንቅ ጉዞ ባዶ እጅ እዚህ አደረሰ።    • ዛሬን ለማዬት ተስኖ አዳዲስ አዛይ ዕሳቤወችን እዬፈጠሩ ዬናዷችሁን አክ ብላችሁ ዕውነት - ሃቀኝነት - መርህ እና ዬትግል ታማኝነት ዬት ላይ እንዳለ መዝኖ መወሰን ይጠይቃል። አሁንም ለግብር ዬሚጠራው ማን እንደሆን አስተውላለሁ። በማን መሪነት? ምን አለን? ማን አለን? ነገስ ለማን - ልዕልና ይታሰብበት። ብቻውን ዬቆመው ዬአማራ ህዝብም ይሰብበት።    • ወደ ባህርዳር ጉዞ ዬሚታገትበት ዘመን ሊመጣ እንደሚችል እሰቡት። መታገት ዓይነቱ ብዙ ነው። ሁሉም እስረኛ እንደሆነ ይሰማኛል። ለዚህ ደግሞ መንገዱ ዬእስራኤሎች ጽናት እና ጥበብ ይመስለኛል። መሪ ማውጣትም ይለ...

ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ።

ምስል
  • ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ።   "ዬማዳንህን ደስታ ስጠኝ። በእሽታ መንፈስ ደግፈኝ።" (መዝሙር ፶ ቁ ፲፪)     (1) ያለን ነገር ማወቅ። (2) ያለን ነገር ማጥናት። (3) ያለን ነገር መመዘን። (4) በአለ ነገር መነሳት። (5) በአለ ነገር ላይ መደራጀት። (6) ዬአለን ነገር ለመምራት በአለን ነገር ውስጥ ያለውን ዲስፕሊን ጠንቅቆ ማወቅ። (7) በአለን ውስጥ ያሉ መልካም ነገሮችን ከደም ጋር ማዋህድ። ( 8)ብስጭትን - ገረጭራጫነትን - ሞረድ አንጀትን ዬክፋት አውራ ጎዳናወችን አክ ማለት። አለን ለሚባለው ሁሉ ቀና ጎዳና ቀያሽ ነው። ለዚህ ደግሞ እራስን መግዛት ይጠይቃል። በአንድም በሌላማ ዬውርጅብኝ ናዳ ዬሚወርድባቸው ሰብዕናወች በዬዘመኑ አሉ። እነሱን ዬራስ ለማድረግ አለን ዬምንለውን በጥንቃቄ ይዘን …   • ተደማጭ፤    • አሸናፊ ማድረግ ካልተቻለ ዬወቀሳ ተርቲም ዛሬን አያተርፍም፣ ለነገም ጭጎጎት ነው። እዮባዊቷ ቅድስታችን ከዬትኛውም ተቋም በላይ ዬዘመኑ ዓውራ እንድትከስም ዬተፈረደባት አሳረኛ ናት። • አጥኑት ዊዝደሟን።    • ሁሉን ረብ አድርጋ በከፍታ ላይ ትገኛለች። • ሁሉን ነገር ታውቃለች። መሪዋ መንፈሥ ቅዱስ ነውና። • ስለሆነም ተፍተፍ ዬለም። • ባጉም ባጉምም አይታሰብም። • ግልቢያም ትውር አይልም። • ዬቂም ብቅልም ዬላትም። • ያላት አርምሞ፤ ተደሞ፤ ጥሞና ፆም ጠሎት፥ ስግደት፤ ሱባዔ፤ ምስጋና፤ ዝማሬ፤ ቅዳሤ፤ ማህሌት ወዘተ … እዮባዊቷን አለችን ማለት ይገባል፤ ነገረ ፍጥረቷ ቫወል ነው። • እኛ እናሰግርሽ እንደ በቅሎ እንጋላብሽ ግን ቀኖናዋም፤ ዶግማዋም አይደለም። • እዮባዊቷ ዬፖለቲካ ድርጅት አይደለችም።   • ተፅዕኖ ፈ...