ግልበጣ በዬፈርጁ። ድንግዝግዝ በብርዝ ዲቃላዊ መንፈስ።
ቆራጣ ነገር ለሚዛናዊ ዕይታ። „እውቀትን ለማን ያስተመረዋል፤? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተው ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ‚ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፲ ከቁጥር ፱ እስከ ፲ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 16.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነ ሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=orfish9aARg Ethiopia - በአዳማ ከተማ የተነሳው ብጥብጥ ዝርዝር መረጃ ይመልከቱ v መንትዮሽ እይታ በዚህ ዜና ውስጥ። · አንደኛው። አንደኛው ዶር ለማ መገርሳን አዬሁኝ። ግን ከቀደሙት አመራሮች ከማውቃቸው አንድም ሰው የለም። ተሳታፊው ኬፕ ተዘጋጅቶለታል። ዓርማው ኦህዴድ የቀደመው ዓርማ ነው። ኬፑን እራሱ ሁሉም አላደረጉም። ስለምን የ ኦነግ አርማ ከዚህ እንዳልታዬ አላወቅም፤ ሚሊዬነም አዳራሽ ያን ያህል የፏለለ አርማ ... ታዳሚው እንደምርጫው መብቱ ተጠብቆለታል። ዶር ለማ መገርሳ ተዝቆ በማያልቀው የስሜን አሜሪካ የህዝብ ፍቅር ከተጠመቁ በኋዋላ ዛሬ ሳያቸው በዛ የሞራል ልዕልና ውስጥ ሆነው አይደለም። አብሶ የሚኒያ ንግግራቸው ድፍረት፤ ወኔ ቆራጥነት የጉድ ነበር፤ የማላውቃቸው እስኪመስለኝ ድረስ። እኔ ብቻ አይደለሁም ሌሎችም መሰል ዕይታ ነበራቸው ... ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ሲሆኑ ደስታቸውን የገለጹበትም ዘይቤ ልዩ ነበር። በተለይም የአንቦው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የ...