የማይድን ምርቅዘት። ግን እስከ መቼ?
ማራራቅ? ግን ለምን? የማይድን ምርቅዘት። „የኃጢያተኞች ሥራቸው ክፉ ነው ፍጻሜያሜውም ገሃነም ነው።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፲ ቁጥር ከሥርጉተ©ሥላሴ 21.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መነ ሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=oS3p3dEhNSA&t=191s ‹‹ ስለ አማራ ክልል የሰማነው እና መጥተን ያየነው የተለያየ ነው፡፡በፍቅር ተቀብሎ በፍቅር እያስተናገደን ነው፡፡ ›› ከትግራይ የመጡ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች ትናንት ማምሻ ላይ ከአማራ የብዙሃን ሚዲያ ይህን መረጃ አገኘሁ እንደ ገረመኝ አደርኩኝ። እኔ ይህ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚባል የጉድ ክምር መቼውንም ዘመን ቢሆን ከአማራ ጥላቻ ይወጣል ብዬ ለማሰብ የመጨረሻ ዕርሜን ያወጣሁበት ዕለት ነበር ማለት እችላለሁኝ። እንዴት አድርጎ ማስፈራሪያ ጭራቅ አድርጎ እንደሳለን ብቻ ሳይሆን የትግራይን ወጣቶች በምን መልክ በሥነ- ልቦናቸው ጢባ ጢቦሽ እንደሚጫወት አንድ የታሪክ ማህደር ሊሆን የሚቸል ሚስጢር ነው የወጣው። እንደምንስ ብለው እነኝህ ሰዎች አገር የመምራት እና ህዝባዊ ሃላፊነት እንደሚሰጣቸው ብቻ ሳይሆን እንደምንስ እንደ አገር ልጅነት ማዬት እንደሚቻል እጅግ ይመራል። የእውነት ይመራል። ከአንዚህ ሰዎች ጋር የሠሩ የአማራ ልጆችም ቢሆን በምን ያህል ትእግስት እና በምን ያህል ችሎት አብረው 27 ዓመት ሙሉ እንደ ዘለቁ ተመርምሩ ያሰኛል። አማራ መደራጀት ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ጥያቄ ቢያቀርብ ሊፈረድበት ፈጽሞ አይገባም። አማራ እኮ 43 ዓመት ሙሉ ብቻም ሳይሆን ዛሬም ጭራቅ ነው ለወያኔ ሃርነት ...