የገማው ጭንቅላት እገዳ፤ መጨረሻውን ያሳምረው። አሜን!
ወንዳታ ብአዴን። „አግዚአብሄርን ደጅ ጥና፣ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድርም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ሃጢያተኞች ሲጠፉ ታዬለህ።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፴፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 24.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · ልበ ገብ ውሳኔ። አሁን ነው የሰማሁት። ለአንድ ወርም ቢሆን ሳጅን በረከት ስምዖን ከማዕከላዊ ኮሜቴ ታግደዋል። እንዴት ወንድ ወጣው ብአዴን? ጉድ በል ጎንደርስ አሁን ነው። እርግጥ ነው እገዳው ለአንድ ወር ነው እስከ ቀጣዩ ጉባኤ ድርስ ቢሆንም ይህንም ድፍረት ማግኘቱ ብአዴን በሁለት እግሩ መቆሙን ያመላክታል። እስከ እሪሞከርኬው ድረስም ነው። ይህን አዝልቆ ከዚህ የመከራ ምንጭ፤ የሸር ፏፏቴ፤ የተንኮል ድንኳን ብአዴን ከተገላላገለ፤ ለዘለቄታ አይደለም ብአዴን ኢትዮጵያን ልኡል እግዚአብሄር ይወዳታል ማለት ነው። አንዱ ትልቁ የገማው ጭንቅላት ነበሩ አቶ በረከት ስምዖን። እስኪ መጨረሻውን ያሳምረው። እራሱ መደፈሩ፤ እራሱ መጀመሩ እራሱ መታሰቡ በራሱ የድል መንበር ነው። ስንት የአማራ ነፍስ በዚህ ሰው ሴራ ድራሹ ጠፍቷል። ስንት ቡቃያ መክኗል። ስንት መከራ አማራ ተሸክሞ ኗሯል። የኢትዮጵያ ፖለቲካስ ቢሆን በዚህ ሸረኛ ሰው ሀርድ ዌር፤ ሶፍት ዌር ስንት ፍዳውን ከፍሏል። እግዚአብሄር በቃችሁ የሚለው ይሄ ውሳኔ እውን ዘድቆ መሬት ሲረግጥ ነው። ይህ ገና ውጥን ነው። ብአዴን መኖር ከፈለገ በውነትም ይህን የመከራ ጉጉት ማስወገድ ነው ለዘለቄታው። ኢትዮጵያም ኢትዮጵያዊነትም ቀን የሚወጣለት ይህ የሴራ ካንፓኒ ውልቅልቁ ወጥቶ ሥራ ፈት ሲሆን ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር። ...