ልጥፎች

ልዕልት ርዕዮት አለሙን እስኪ እንዴት ባጀሽ ልበላት።

ምስል
ትናንትን ዛሬ በምልስት እስኪ ይቀፈው? ወርዱ ከቻለው?   „በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡ ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽ ው ፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥ ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡ ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡ ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡ ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም።“ ( ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫ )  ከሥርጉተ© ሥላሴ 21.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ማሰብ እና ማግኘት ጋዳ ናቸው። ልዕልት ርዕዮት አለሙን ዓይኔን በዓይኔ የማዬት ያህል ነበር የማስባት። እጅግም እሳሳላት ነበር የዛሬውን አያድርገው እና። ከእስር መፈታቷን ብቻ ሳይሆን የብርታትን እኩልነት ብርሃን ትሆናለች ብዬም በጽኑ አስባት ነበር። መመኘት ከልካይ ስሌለበት የውስጤ ሐሴት ትሆናለች የሚል ብሩህ ተስፋ ሰንቄ ነበር መፈታቷን የጠበቅኩት። የሚገርመው የእሷም የእህቷም መጠሪያ ሥም የእኔም  የእህቶቼም ነው። ሥምም ትርጉም ይሰጣል የውስጥ ሲሆን። እናም እጅግ አቅርቤ አያትም ነበር። በመጨረሻ ግን አሜሪካ ከገባች በኋ ዋላ ለእነዛ ካቴና ላይ ላሉ ነፍሶች ብጣቂ አዘኔታ ስታጣ ነፍሴን ጨነቃት፤ እጅግ ካዘንኩባቸው ጥቂት ነፍሶች አንዷ እሷው ሆነች። አሁን በቅርቡ በጀግኒት እማዋይሽ አለሙ ጉዳይ ታታሪ አቶ ተሎ...

የአቶ ወንድም የ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ተረብ...

ምስል
የጋዜጠኛ ፋሲል ተረብ ማለዘቤያ ቁራሽ መላሾ ነው። „አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል ?“ መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  21.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ዳውን ሎድ ማድረግ ተቸግሬ ጹሑፌን ሳላወጣ ቀረሁኝ። የትናንቱ በሌላ ዙሪያ ነበር። ዛሬ እሺ ካለ ይሞከራል። ስለዚህም ትናንት ቀጥዬ ልጽፍ የነበረኝ ፍላጎት ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ነው ብዬ በሌሎች የንባብ ፕሮግራሞች ላይ አተኮርኩኝ። ዛሬ በአዲስ አጀንዳ ብቅ አልኩኝ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/92059 የአዴፓ መሪዎች ምን ይላሉ ? – ፋሲል የኔዓለም እንድምን አለህ ወንድም አለም ልጅ ፋሲል የኔአለም። ደህና ነህ ወይ? ውዶቼ፣---- ዛሬ ከአቶ ወንድም ከጋዜጠኛ ፋሲል የእኔ ዓለም ጉዳይ ጋር አብረን እንዘናከት ዘንድ ወደድኩኝ። ጥሩ ነገሩ እንደ ድርጅቱ እንደ ግንቦት 7 አይደለም እሱ። ወቃሰው ሆነ ሙግቱ ቂም አብቅሎ ዘመቻ ግለት ጫና የሚያስከትል አይደለም። እንዲያውም እኔ እስኪ በቃው ሞግቼው ወጣቶች እንደ ነገሩኝ ከሆነ አንድ ጹሑፌን በቤተ መንግሥቱ ሚዲያ በአምስተርዳሙ ኢሳት እንደ አቀረበው ነግረውኛል። እስኪ ገርመኝ ድረስ። በሌላ በኩል አንድ ጊዜም አንድ ሃሳብ ኖሮኝ ስጽፍለት በጎ መልስ አክብሮ ሰጥቶኛል። ይህን በራሴ ደርሶ ስላዬሁት በአንድ ወቅት በዝርዝር ጽፌያለሁኝ። ሌላው ትልቁ ጸጋው የፈለገ አስተያየት ይጻፍ አክብሮ መልስ ይሰጣል። ትህትናው እንዲያውም እናቴን እብዬን ይመስለኛል። እናቴ የባዛ እጅግም የበዛ ደግ ቅን እና ትሁት ናት። ትህትናዋ ስለሚበዛ ልጆቿኝ እንደ ትዳሯ ታከብራለች፤ ትፈራናለችም። አዘዦቿ እኛ እንጂ እሷ...