የዶር አርከበ ዕቁባይ ሦስት ዓመት ልባም ጥሞና ለስኬት።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። · የ ዶር አርከበ ዕቁባይ ሦስት ዓመት ልባም ጥሞና ለስኬት። ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠበቂ በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። “ · ማ ዕዶተ ጠባቂ ማናቸው አጀንዳወች ይለፍ የሚሰጥ ዕልፍኝ። ዶር አርከበ እቁባይ የተመደ UNIDO ከመጨራሻወቹ ሦስቱ እጩወች አንዱ መሆናቸው ተደምጧል። የተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ተቋም UNIDO በዳይሪክተርነት ለመመራት ነው የታጩት። ዕንቁ ዕድል ነው። ለጭምት ፖለቲከኛ ይህ ከዕድልም በላይ ነው የሰማይ ስጦታ። አክብረው፤ ጥሞና ወስደው ሊቀበሉት ይገባል። ጸጸትንም ሊመግቡት ይገባል። ለፈጣሪ ከሳው ያ ነውና። እያንደንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊትም መልዕክትም ይዞ ይወለዳል የምለውም ለዚህ ነው። የአፍሪካ ህብረት አህጉሩን ወክለው እንዲወዳደሩ በእጩነት እንዲቀርቡም ወስኗላቸዋል። ከጀርመን እና ከቦልቡያ ጋር እኩል ተወዳዳሪ ናቸው ዶር አርከበይ እቁባይ ኢትዮጵያን ወክለው። · የ እጬጌው ሂደት የቤት ሥራ። ነገስ ዛሬ ፈቅዳ እና ወዳ በሥሞ ኢትዮጵያ ለምትሳጣቸው ይህ ሰማይ ጠቀስ ክብር ውለታዋን ይመልሱ ወይንስ ውለታ ቢስ ይሆኑ ይሆን? እጬጌው ሂደት ይመልሰው። ልዕልት ኢትዮጵያስ አመድ አፋሽ ወይንስ ሞገስ አፋሽ ያደርጓት ይሆን? በጭንቋ፤ በመከራዋ፤ በመከፈቷ፤ በልጆቿ ዕንባ ለ...