ለኢትዮጵውያን የልቅ እና በልዕልና የከፍታ ደረጃ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናቸው - ለእኔ። ክብርቷ ለክብርት ኢትዮጵያ #ልኳ ናቸው። #ተመድን ለመምራትም ልክ ትክክል ናቸው። የአፍሪካ አንድነትን ለመምራትም። ኢትዮጵያ አገር ብቻ አይደለችም ለእኔ - #ትንፋሽም።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።" ለኢትዮጵውያን የልቅ እና በልዕልና የከፍታ ደረጃ ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ናቸው - ለእኔ። ክብርቷ ለክብርት ኢትዮጵያ #ልኳ ናቸው። #ተመድን ለመምራትም ልክ ትክክል ናቸው። የአፍሪካ አንድነትን ለመምራትም። ኢትዮጵያ አገር ብቻ አይደለችም ለእኔ - #ትንፋሽም ። እንዴት አንዴት አደራችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ዓለማችን ብቁ ሴቶችን፤ ሞጋች ሴቶችን በፖለቲካው ዘርፍ፤ በዲፕሎማሲው ዘርፍ፤ በተፈጥሮ እና ማህበራዊው ሳይንስ ዘርፍ አፍርታለች። ኢትዮጵያም ድንቅ የሆኑ ሊቀ - ትጉኃን አንስቶችን አፍርታለች። ቀደም ባለው ዘመን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሴቶች እኩልነት በማይታሰብበት ዘመን አገርን የመሩ የተከበሩ ብቻ ሳይሆን የተቀደሱም ንግሥታት፤ እቴጌወች ነበሯት። ኢትዮጵያን ለመድፈር ሲታሰብ ጀግኖች እናቶቻችን ጦር መርተው ለድል መንበር አብቅተውናል። መኖርን በማስዋብ በተለያዩ የፈጠራ ሥራወች እና ስልጣኔወች፤ ከተሞችን በመቆርቆር እና በማደራጀትም ድንቆች - #ድንቅነትን #አብርተዋል ። ዛሬም ቢሆን እራሳቸውን ከደን አድርገው፤ "ሙያ በልብን" ሰንቀው #የልብ #አድረስ ተግባራትን የሚከውኑ አንቱ ሊባሉ የሚገባቸው እህቶች በዬዘርፋ አሉን። ከእነኝህ ሁሉ #ቁጥር #አንድ በብቃት፤ በተመክሮ፤ በትዕግሥት፤ በመቻል አቅም፤ ዘለግ ባለ ሁለገብ ተመክሮ በዕውቀት ባንታደል እንጂ ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን የሚልቅ አይደለም #ሴት #ተባዕት ኢትዮጵያዊ/ #ኢትዮጵያዊት አለን ብዬ እኔ በግሌ አላምንም። ከዘባጣ፤ ጠናና ሥርዓት ጋር በመሥራታቸው ወርቃቸው ጊዜ አጣ። ውስጣቸው በተመክሮ ዕንቁ የከበረ ነው። የመጨረሻው #የብቃት #ደረጃ ...