ርትህ ክፍል ሁለት።
ርትህ። ክፍል ሁለት። ከሥርጉተ © ሥላሴ 30.06.2018 (ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።) „ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብጹዕን ናቸው“ (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፮) · እ ፍታ እንዴት አላችሁልኝ የአገሬ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ዛሬ በርካታ ነገሮች ቢኖሩም ቅድሚያ ሰጥቼ ምልከታዬን ላጋራችሁ የምሻው የአፋሩም የሠመራ ጉባኤ ጥያቄ እና የመልሱን ዕድምታ ነው። እርግጥ ነው ይሄ መቅድም ስለሆነ ተያያዥ ነገሮች ማንሳቱ ግድ ይለኛል። የክልሎች ማሰረጊያም ጉባኤ ስለሆነ። ምክንያቱም የጠ/ ሚር አሜኑ አብይ የመንፈስ ነፍስ እኔን እንደ ገባኝ በሁለመና የተቃኘ ንድፍ አለው። የሠመራው ከክልል አንፃር ማጠቃለያው ነው። ቀጣዩ የተጎዱ የቀደሙ የክ/ አገር ከተሞችን እና በአቻነት የሚታዩት ላይ ቢሆን የሚል እሳቤ አለኝ። ቢሆን ምርጫዬ ነው እንደ ማለት። ደሴ፤ ጅማ፤ አሰላ፤ መቱ፤ ድሬድዋ፤ ሻሸመኔ፤ ሙያሌ፤ ነቀምት፤ ማርቆስ፤ ደብረታቦር፤ አርባምንጭ፤ ደብረብርሃን እንደዚህ በዓመቱ መርሃ ግብር ቢካተቱ መልካም ነው። አሁን ደሴዎች ሰሞኑን ከአቶ ገዱ አንዳራጋቸው ጋር ውይይት ነበራቸው፤ ተዜትኛው ምዕተ ዓመት እንዳለች ደሴ ግራ ያጋባል። አሁንም ሜዳ ላይ ነው ጉባኤው የተካሄደው። ይሰቀጥጣል። · ክ ብረቶቼ። ክፍል አንድ ላይ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ „የዙረት አበዙ“ መንፈስ አባዜም አፋር ላይም ተደምጧል። በክፍል አንድ የጉዞውን ዓላማው አቅጣጫ በሥርጉተ ግ...