እኛ የሚያስፍለግን የአብይ ጤነንት ከነቤተሰቡ ነው።
„አያ ጅቦ ሳታማህኝ ብላኝ።“ „በአምላክህ በእግዚአብሄር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይንም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሄር አትሰዋ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ቀልቤን የሳበው ጹሑፍ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የጻፈውን ከሳታናው ብራና ላይ አገኘሁ እና ሁለት ነገሮችን ነቅሼ ማውጣት ፈለግሁኝ። ጹሑፉ የትናንት ነው የሻሸመኔው አሰቃቂ ግድያ ከተፈጸመ በፊት እና በኋዋላ ስለመሆኑ እማውቀው ነገር ስሌለ ልዝለለው። እርእሱ እንደምታዩት ነው። አሁን ያለው መፈንቅለ መንፈስ ኩዴታ የማን ስለመሆኑ በማን ስለመማራቱ ፍንጭ ማውጣት አልፈለገም። ሁሉንም ችግር ጠቅልሎ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ላይ ነው የደፈደፈው። የችግሩ አንኳር ያለው ግን ኦህዴድ ላይ ነው። በተቀጥላ ብአዴን ላይም እዬታዬ ነው። አሁን በቅደመ ተከተል ሁለቱን እንሂድባቸው። „ህወሃት ከቤተመንግስት ተባሮ መቀሌ ከመሸገ ወዲህ ሁለት ግንባሮችን ከፍቶ በሰፊው እየሰራበት ነው ( መሳይ መኮንነ )“ August 12, 2018 · ቀዳሚው። „ከአንድ ሰሞን ዘመቻ ተላቀን በራዕይና ተልዕኮ በተቀረጸ የተግባር እርምጃ ላይ እናተኩር ዘንድ የሁላችን ቅን ልቦናና ዝግጁነት የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ነን።“ እህ ቅንነት? ? ? ? መቼ ነው የእኛ የነፃነት ትግል ከንፋስ ወጀብ ወጥቶ የሰከነ ሥራ ሠርቶ የሚያውቀው። ይህን እራሱ ድርጅቱን ይጠይቀው። ጥያቄ ሚዲያውን ሳይሆን የራሱን የፖለቲካ ድርጅትን ግነቦት 7 ማለቴ ነው። ባለፈው ...