ልጥፎች

የቃልቋንጣ (የወግ ገበታ)

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የቃል ቋንጣ ። „የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብን ና ክብርን ያጠፋል።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 10.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። የወግ ገባታ። ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute© Selassie) የአላዛሯ ኢትዮጵያ ራህቧ እውነት ብቻ ነው። ·          መ ቅድም ። ·          በ ድምጽ። ·            https://www.youtube.com/watch?v=HS0Gm_tMll8 የቃልቋንጣ (10 05 2019) ·          እ ፍታ። እንደምን ናችሁ የኔዎቹ ቅኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? የንጉሦች ንጉሥ አጤ ቴወድሮስ የሚታወቁበት ሥነ - ቃል „ቃል የዕምነት ዕዳ ነው“ የሚለው ዘመን ተሻጋሪ ፍልስፍናቸው ነው። ለነገሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድም በአብዛኛው ሰው ልብ ሊመሰጠሩ የቻሉበት „ቃል ይተክላል፤ ቃል ይነቅላል፤ ኢትዮጵያም የተተከለችውም፤ የተነቀለችውም በቃል ነው“ ያሉት ሁላችንም ልባችን የሸለምንበት አምደ ጉዳይ ነበር። ምን ያህል በቃላቸው ውስጥ እንዳሉ ህዝብ መስታውቱ ስላለው የህዝብ ህሊና ይዳኘው። መይሳው ካሳ አጤ ቴወድሮስ ግን በቃላቸው ውስጥ ሰክነው፤ ቃላቸውን ቋንጣ ሳያደርጉ፤ ቃላቸውን ሳያጠንዝሉ፤ ቃላቸውን ፍ...

ወንዝ፤ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ገባሪ ወንዝ (ቄንጠኛ ዝንጥ ያለ ወግ።)

ምስል
ወ ንዝ፤ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ገባሪ ወንዝ።   „የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት። የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፪   ከሥርጉተ©ሥላሴ   Sergute©Selassie   09.05.2019   ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። አ ልኳችሁ ዛሬ ቪንቲ በስጭት ብላ፤ ወጅብ ስትለቅብን ነበር የዋለችው። እናላችሁ እኔ እህታችሁ፤ ምኔ ሞኝ?! ዋናውን ሰቅሰቅ ጠበቅ አድርጌ ከርችሜ ቁጭ።   ግን እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁን አዱኛዎቼ ። እናንተን አያሳጣኝ ፈጣሪዬ። አሜን!   ቄንጠኛውን ወግ በድምጥ ከፈለጋችሁ ቅኖቹ . .. https://www.youtube.com/watch?v=mc-brGzchX4&feature=youtu.be አ ንድ አገር አንድ መንግሥት ያስፈልገዋል። ያ መንግሥት ግን የውጭጭ ያልሆነ፤ የእጣ እጣ ያልሆነ፤ የአድርሽኝ ያልሆነ ወይንም የሽሙጥ ያልሆነ ወይንም የደርሶ መልስ ያልሆነ ወይንም ባጣ ቆዬኝ ያልሆነ፤ በራሱ ውስጥ የሰከነ። የጸና፣ ለህግ ተገዢ፤ ሚዛናዊ እና ተጠያቂነትን የሚቀበል።   ዘ መኑ የዬሀገሩ መንግሥታት አብዛኙቹ የፖለቲካ ድርጅት አላቸው። በህሊና በሠለጠኑት በውድድር፤ በፉክክር፤ በፍቅር፤ በመቻቻል በምርጫ ተወዳድሮ ያሸነፈ በትረ መንግሥቱን ይይዛል።   እ ንደኛ ያልሆነ ማለት ነው። ያው በዚህ ስሌት ሲኬድ እኛ በዚህ ዘርፍ ደረጃችን እንቁላል ነው። ፍላጎቱን እንጂ መሆኑን ስላልሰጠን። በቃ ማለት ብቻ፤ ማለት አሁንም ማለት፤ ትናንትም ማለት፤ ዛሬም ማለት፤ ነገም ማለት፤ ተዚያ ወዲያም ማለት … የማለት...

በሴት የፖለቲካ ሊሂቃን የነበረው ተስፋዬ ወደ መቃብር እያሰኘው ነው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  በሴት የፖለቲካ ሊሂቃን የነበረው ተስፋዬ ወደ  መቃብር እያሰኘው ነው። „የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤  እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ክብርን ያጠፋል።“  መጽሐፈ መክብብ ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.05.2019 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                                                                                         እውን ይህ ጽናት በምን ሁኔታ ተጠለፈ?                                                     ድምጽ አልባዋ የአማራ እናትም ልጇ                                              ...