ልጥፎች
ግን እራሱ ምንድን ነው ምንድን ነው? …
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን? 25/07/2023 የተፃፈ። ገርሞኛል። ምንድን ነው እራሱ ምንድን ነው? እያሰብኩ እራሱን ሃሳብን አሰብኩት፤ በኃላፊነት እና በተጠያቂነት ማህል ጉልቻ ስለመፍረሱም ፁሁፋ ያነሳሳል የሚደንቁ አገላለፆች የእኔ መሆናቸውን ተጠራጠርኩኝ። እስቲ ፈትሹት ……… "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። (መዝሙር ፻፴፯ ቁ ፩) እንዴት አደራችሁልኝ ማህበረ ክቡራን እና ክቡራት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ አምላኬን ተስፋ አድርጌ ደህና ነኝ። ሰሞናቱ እንደ ደመናም፤ እንደ ወጀብም፤ እንደ ዝናብም ይቃጠዋል በቅድስቷ በዕቴ በቪንተርቱር ከተማ። ማሰብ። ማሰብ። ማሰብ። #እያሰብኩ #ሃሳብን አስበዋለሁኝ። ስለምን ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት ተሳነን? እኛም ሆን የቀደሙት ስለምን መዝራትን ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ #ከማብቀል ፤ #ተጠንቅቆ ከማሳደግ ጋር ምኑ አፋተን? #በኃላፊነት እና በተጠያቂነት መሐል ጉልቻው ከፈረሰ ቆዬ። ግን ለምን? #አደራ ምንድን ነው? #ትውፊትስ ምንድን ነው? #ትሩፋትስ ምንድን ነው? #ቅርስ ውርስስ ምንድን ነው? #ታሪክስ ምንድን ነው? #ባህልስ ምንድን ነው? #ወግ - ልማድስ ምንድን ነው? ግን ምንድን ነው እራሱ #ምንድን ነው? መልስ ይሻል? እንጀራን እዬበሉ እንጀራ የተፈጠረበትን ሥልጣኔ ማብጠልጠል? #አማርኛ #ቋንቋን እዬተናገሩ አማርኛ #ቋንቋን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት መፍጨርጨር? ሰንደቅ ዓላማው ባስገኜው የነፃነት ትንግርተ ቤተ - መንግሥት ተቀምጦ ሰንደቅ ዓላማን መፎካከር? ………ግን ምንድን ነው? እራሱ...
መሪነት መፍትሄ አመንጭነት ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
መሪነት መፍትሄ አመንጭነት ነው። #አጤ #ሽዋስ እንዴት አደረ ይሆን? ዬአጣዬ መከራ ከውስጡ ያልገባ የአመራር ሂደት ያ ሁሉ መከራ አልበቃውም፦ የአጣዬ የሽዋ ሮቢት ያ ሁሉ ስቃይ ተዘሎ አሁን ደግሞ እንደ ዳንቴል #በእጅ #በተሠራ #መከራ #አሳሩን እያዬ ነው። አዝናለሁ ሕዝባችን እንዲህ ከመከራ ላይ መከራ ተሸከም ተብሎ ፍዳውን ማዬቱ። ደብረብርኃን መጠለያ ያሉት ወገኖቻችን ስቃይ እራሱ #ሐዋርያ በሆነ ነበር። መጠለያ ላሉትም #ተስፋቸውን ሙልጭ አድርጎ #የዘረፈ // #ስጋትን #አጭቶ ያነገሠ ጉግስ ነው እያዬሁት ያለሁት። ልብ ይስጣቸው ለመሪወቹ። አሜን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ 2024/07/24
#ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል። ቢያንስ ለአማራ እናት #ዕንባ መቆም እንዴት ይሳናል? ባልተለመደ ሁኔታ #በእናቶች ላይ የሚፈፀመው፤ በግራጫማ ፀጉር ባበቀሉ ወገኖች ላይ ያዬሁት የእንብርክክ ስቃይ፤ የከፋም እርምጃም ሰማሁ ለዚህ ነው ሙሉ ቅኔው ጎጃም ከሐምሌ 5 ጀምሮ መኖሩን የሰጠው? ለዚህ ነው? ለጭካኔ? ከጨካኝ ተሽሎ መገኜት እንዴት አይቻልም? ሙሉ የጦርነቱ አቅም የፈሰሰው እኮ ቅኔው ጎጃም ላይ ነው። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አገዛዝ የውጭ አገር ቅኝ ገዢ እስኪመስለኝ ድረስ #በእልህ ማቱን ያፈሰሰው በዚህ ጨዋ ህዝብ ላይ ነው። ከመጀመሪያዋ ከሐምሌ 5ቱ የተጋድሎ ንቅናቄ ጀምሮ #በጠና አቅም እና #አቋም ሳይሽረከረክ፦ ለመደለያ ሳያድር የትግሉን መንፈስ ያስቀጠለ ጀግና ህዝብ እንዴት በተስፋወቹ ይቀጣ? ግፍ አይሆንም? አልቅሻለሁ። የት ይሂድ ይህ ህዝብ? ምርጫ አለውን? ማስተማር መንገር ማሳመን እያለ እንደዛ? ነገስ??? ሥርጉ2024/07/24
ብዙ ያልተነገረ ታሪክ እዚህ ቤት አለ! #italy#addisababa#gizachewashagrie#marakiweg ዕንባዬን መቆጠር አልቻልኩም መቀጠልም አልቻልኩም። ሼር ግን አደርገዋለሁ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የ200 ብር ቤት ኪራይ መክፈል አቅቶኝ ነበር | ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ክፍል 1 | Beyond the screen | ...
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
አዲስ ፈተና ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
አዲስ ፈተና ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በዚህ የጠለፋ እና የእገታ ክስተት ውሳኔያቸው ምን ሊሆን እንደሚችል እጠብቃለሁኝ። በእገታ፦ ከእጃችሁ የገቡት አርበኛ ኮነሬል አሰግድን እንደምን እንደሚይዟቸው አያለሁኝ። የቀደምቶችን ታሪክ ውስጥ የእኔ አሻራ አለበት ብለው በብዙ ሁኔታ አዳዲስ ሁነቶችን አያለሁ። ለምሳሌ ከሥሙ ጀምሮ ጨፍላቂ የሆነው ዓድዋድዋ " #ዜሮ ዜሮ" በዚህ ላይ ጽፌበታለሁ ተዚህ ቀደም። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ምን እና ምን እንደሆነ፤ የህወኃት እና የእርስወ መንግሥት ጦርነት የአገልግል የውሎገብ የጦር ዘመቻወት ከአንገተወት ላይ ስካርፕ እንደ ህወሃት ጣል አድርገው ብዙ በጣም ብዙ ነገሮችን ማንሳት እችላለሁኝ። እምዬ ሚኒሊክ ከእጃቸው የገቡትን የጣሊያን መኮንኖች እንደምን እንደያዟቸው ያውቃሉ። ያውም #በምርኮ ። ከንጉሦች ንጉሥ ከእምዬ ሚኒሊክ እስኪ ይማሩ። ይህ #ጠለፋ ነው። ይህ እገታ ነው። ፊትለፊት ተጋጥማችሁ በተመዘገብ የድል ስኬት የተገኜ ዕድል አይደለም። #ምርኮም ወይንም #እጅ #መስጠትም አይደለም። ይህን ተቆራርጦ ከተለቀቀው ቃለ ምልልስ ደጋግሜ ሳዳምጥ ያገኜሁት ግንዛቤ ነው። ዕድሉ #አጤ ስልክ ያመጣው ጣጣ ነው። የሆነ ሆኖ መሪነት በቀል አይደለም። መሪነት #ቂመኝነት አይደለም። መሪነት የአማራን ህዝብ እና ቱሩፋቶችን መሪወቹን፤ #ተምሳሌወችን #ማቃለል ፦ #ማጣጣል አይደለም። መሪነት በእጅ የገባን ዕድል በቅጡ መያዝ ነው። ማንገላታት፤ ዱላ፤ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመዋል መጣር፦ #ማዋረድ የሚገባ አይደለም። የሰው ልጅ ፈጣሪ ቤተ መቅደሱ አድርጎ የፈጠረው ክቡር ፍጥረት ነው። ዕምነት ሃይማኖት ክብርን ሲቀበሉ ፍጥ...