ክፍል አምስት - ርትህ።
ርትህ። ክፍል አምስት። ከሥርጉተ ሥላሴ02.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ዪሚያስታርቁ ብፁዕና ናቸው የእግዚአብሄር ልጆች ይባላሉና።“ (ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፱) · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c „ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar“ በዚህ ውስጥ የሠማራውን ጉባኤ መዳሰስ የምፈልገው ከ20.38 ባለው ደቂቃ ብቻ ያደመጥኩትን ነው። ቀሪው ክ/ጊዜ ደግሞ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህን እማደርግበት ዋናው ምክንያት ዛሬ ያለው የለውጥ ተስፋ እና እኛ ያለን መጣጠም መቀራረብ እንዲኖረው ለማድረግ ነው። ክፍተት ከኖረም መገጠም ስለሚያስፈልገው ነው። · ተጠቃሚና ጥቅሙ ትልልፍ። በዚህ በአፋሩ ስብሰባ የአፋሩ ጉባኤ አልተጠቀምነም የሚል ዕድምታ ቢደመጥም አፋር የተጠቀመበትን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለማመሳከሪያነት አንስተዋል። አውሮፕላን ማረፊያው እና የተሰበሰቡበትን አዳራሽ እንደ ምስክር አቅረበዋል። ይሄ ከሆነ ስለምን ትግራይ አልተጠቀመም የሚለውን አገላለጻቸውን በዚህ መነጸር ሊያመዛዝኑት እንደማይፍለጉ ብዙም ግልጽ አይደለም ለእኔ። ብሶትን ለማቀጣጠል ክብሪት መሆኑን መድፈር ባይችሉም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመጣ በ ኋ ዋላ የተወለዱት ልጆች ሳይቀሩ ደግሜ የተወለድኩ ያህል ይሰማኛል ያሉበት ምክንያት ጥናት ሊደረግበት ይገባል። ከዚህ በላይ በራብ ውስጥ፤ በሞት ውስጥ፤ በመፈናቀ...