ልጥፎች

ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው፤ በ2014 ፖስት ተደርጎ የነበረ።

ምስል
ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው - ለእኔ! „ስለ ጽዮን ታላቅ ቅናት ቀንቻለሁ። በታላቅም ቁጣ ስለ እሷ ቀንቻለሁ።“ ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፪ ከሥርጉ ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 11.01.2014 ·        ማግባቢያ ለመቅደሙ እና ለዕለቱ ጡሑፍ። ውዶቼ ይህ ጹሑፍ በ2014 ነው የተፃፈው። ያን ጊዜ ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ በሳተመው "ጥቁር ሰው" ላይ ወጀብ የጠናበት ጊዜ ነበር። እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት የመጡበት ያዙኝ ልቀቁኝ ይሉበት የነበረበት ዘመን ነው። ጠንከር ያሉ ፓኢልቶኮች ተከፍተው ኢትዮጵያዊነት ሲብጠለጥል የነበረበት ወቅት ነበር። በአንድ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ ኢትዮጵያ ተወክላ በእንሱ ዘመቻ እንዲቀር የተደረገበት ጊዜ ነበር ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ። እነሱም ደስታውን እያጣጠምን ነው ያሉበት ወቅት ነበር። ዛሬም ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ዘመን ራሱን ደግሞ እንሆ ትግራይ ላይ ሌላ የጦርነት አዋጅ ነጋሪት አለ። ጦርነቱ በኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። እትዮጵያዊነት አሸናፊ ሆኖ ስለወጣ። ኢትዮጵያዊነትን በጥልቀት ማዬት ከተሳነን ለድጋሚ ሌላ ጦርነት እንጋለጣለን። የሃሳብ ጦርነቱ ይሁን፤ በሃሳብ ጦርነቱ ውስጥ የጥቃት ሰለባ የሚሆኑ ዜጎች እንደሚኖሩ ማሰብ ግን ይገባል። እነሱም ከጠራው መስመር ጋር ለመሆን ማሰብ እና መቁረጥ ይኖርባቸዋል። የትግራይ መሳፍንታት ህልም ቁሞ ቀር ከሆነ እንሆ ሦስት ዓመት ተቆጠረ።  የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ የተጀመረ እለተ አቡዬ ሐምሌ 5 ዕለት የታላቋ ትግራይ ኢትዮጵያዊነትን ጥሶ ለማለፍ የነበረው ህልም አፈር ድሜ ጋጠ ። ምክንያቱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የማህል አገር መዳራሻ፤ ...

ነፃነት ቅኔ ነው!

ምስል
ነፃነት ቅኔ ነው! "በእውነት ጥበበኛ ሰው ራሱን ይጠቅማልን?" መጽሐፈ እዮብ ፳፩ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute© Selassie  16.06.2013 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ ይህም የ2013 ጡሑፍ ነው። ፡ እሜቴ ነፃነት እንድምን ይዞሻል? እንዴትስ ከርመሻል? ከእመናው ሸክማ ሸክምሽ ዘንድሮስ ከብዶሻል እልፈት የለው ኑሮሽ እንዲህ ይፈትልሻል። ተርጓሚ ሲገኝ ነፃነት ቅኔ ነው። ነፃነት ረቂቅ ጥልቅ የተባረከ የመንፈስ ውስጥ ፍላጎት ነው። ነፃነት የሰለጠነ ህዝብ ብቸኛ የግናዘቤ መለኪያ ነው። ነፃነት ሰፊ የሰብዕዊነት ማሳ ነው። ነፃነት የሃይማኖት መሰረታዊ ቃል ነው። ነፃነት በጥሬው ብቻ ሊተረጎም የማይችል ውስጥን በራስነት የማናፅ ሥልጡን ክስተት ነው። ነፃነት ዛሬ የዓለማችን ጉልተ - አጀንዳ ነው። ነፃነት ዛሬ የዓለምን መንፈስ በአንድ ሃዲድ ያገናኘ ቅዱስ አምክንዮ ነው። ነፃነት ህይወት ላላቸው ብቻ ሳይሆን ለግዑዛን ሳይቀር ተቆርቋሪ ጠበቃ ነው። ይህችን ትንሽ ዘርዘር ባደርጋት መልካም ነው ከተጠቀለለች እንዳትጠጥር … በመጠኑ ስለምን ነፃነት ለግዑዛን ሳይቀር አስትንፋስ ሆነ?  ምክንያቱም ግዑዛኑም ቢሆኖ በሰው ልጅ ታሪካዊ ሂደቶች ብቁ ታዳሚ ከመሆናቸው በላይ ትናንትን ለዛሬ - ዛሬን ለነገ፤ ነገን ለነገ ተወዲያ ያቀባባሉ፤ ያሰብላሉም  ባለውለታዎቻችን ናቸውና፤ አሁን የዋሻ ዘመናት ታሪክ በድንጋይ ላይ ተቀርጸው ይገኛሉ። ብዙም ይናገራሉ፤ መሬት በከርሷ እፍን ሽክፍ አድርጋ ያያዘቻቸው ቅሬተ - አካላት ትናትን አበክረው ያውጃሉ፤ ከመነሻም ይገነባሉ። ለዝንተ ዓለም ዝክረ ንዑዳን ናቸው። ለዛሬ ሥልጣኔም የምርምር ማዕከል እኮ የትናት ትንግርት ክንውን ነው...

ሴቶች ጥሩ ነገር አላቸው...

ምስል
ሴቶች ጥሩ ነገር አላቸው ጊዜ እሲኪሰጣቸው ድረስ ጠብቀው ይይዙት ዘንድ  እለምናቸዋለሁ። "አለመታገሥ ስለምን አይገባኝም?"  መጽሐፈ እዮብ  ፳፩ ቁጥር ፬     ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 23.12.2013 ·        መግቢያ። አሁን ሳስበው እኔ እና ሳምንበትም ጊዜ ሰጥቷናል እላለሁኝ። ግን እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። ይህ ብሎግ ሥራ የጀመረው በግንቦት 1 ቀን በ2018 ነው። ከዚህ ቀደም በስፋት የተሠሩባቸው ጉዳዮች በዘሃበሻ ወይንም በኢትዮ ርጅሰተር ነው። ቀደም ባለው ጊዜ በራሴ በጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ራዲዮም ነው። እኛ እራሳችን ሲሞላብን እንደምንቀንሰው ሁሉ ዘሃበሻም ሆነ ኢትዮ ሪጅሰተር ሆነ ዘሃበሻ እነሱ ደግሞ አርኬቡ ሲሞላባቸው መቀነስ ግድ ይላቸዋል። ግሎባል ጉዳዮችን ስለሚያስተናግዱ ጫና ይበዛባቸዋልና።   ስለዚህም ጹሑፎቼ ሊሠወሩ ይችላሉ። ታሪክ ነው። ታሪኩ የኢትዮጵያ የነጻነት ትግል በአንዲት ዜጋ ዕይታ እንደ ዘመኑ ነው። ዛሬ በ2013 እንደምጸፈው ዛሬ አልጽፍም። ስለምን? ዘመኑ በራሱ የሚያመጣው ለውጥ ስላለው።  ግን በዛ ዘመን የነበረው ዕይታ እና ግንዛቤ ዛሬን በሃሳብ በማገናኘት እረገድ ምን ድርሻ አበርክቷል የሚለውን ያሳያል፤ በሌላ በኩል ግን የአንባቢያን ዕይታም በዛ ዘመን በነበረው ንቃተ ህሊና ልክ የተሠራ ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል። ስለሆነም ከጻፍኳቸው ወዘተረፈ ወጎች ውስጥ በዚህ ብሎግ እንዲቀመጡልኝ የምፈቅዳቸውን በተከታታይ ፖስት ለማድረግ አስባለሁኝ። www.tsegaye.ethio.info ያለው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው። እንዲህ ነበር የተጀመረ...

ለዝክንትለኛዋ ዓለም ፈውስ ትሆን ዘንድ የተመረቀች - የተመረጠች - ሴት!

ምስል
መኖር እንዲያምርበት …. „ልቤ በመናፍቅ ዝሏል።“ መጽሐፈ እዮብ ፲፱ ቁጥር ፳፯ ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selasssie 09.02.2014 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ) ·        መግቢያ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። ይህ ብሎግ ሥራ የጀመረው በግንቦት 1 ቀን በ2018 ነው። ከዚህ ቀደም በስፋት የተሠሩባቸው ጉዳዮች በዘሃበሻ ወይንም በኢትዮ ርጅሰተር ነው። ቀደም ባለው ጊዜ በራሴ በጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ራዲዮም ነው። እኛ እራሳችን ሲሞላብን እንደምንቀንሰው ሁሉ ዘሃበሻም ሆነ ኢትዮ ሪጅሰተር ሆነ ዘሃበሻ እነሱ ደግሞ አርኬቡ ሲሞላባቸው መቀነስ ግድ ይላቸዋል። ግሎባል ጉዳዮችን ስለሚያስተናግዱ ጫና ይበዛባቸዋልና።   ስለዚህም ጹሑፎቼ ሊሠወሩ ይችላሉ። ታሪክ ነው። ታሪኩ የኢትዮጵያ የነጻነት ትግል በአንዲት ዜጋ ዕይታ እንደ ዘመኑ ነው። ዛሬ በ2014 እንደምጸፈው ዛሬ አልጽፍም። ስለምን? ዘመኑ በራሱ የሚያመጣው ለውጥ ስላለው።  ግን በዛ ዘመን የነበረው ዕይታ እና ግንዛቤ ዛሬን በሃሳብ በማገናኘት እረገድ ምን ድርሻ አበርክቷል የሚለውን ያሳያል፤ በሌላ በኩል ግን የአንባቢያን ዕይታም በዛ ዘመን በነበረው ንቃተ ህሊና ልክ የተሠራ ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል። ስለሆነም ከጻፍኳቸው ወዘተረፈ ወጎች ውስጥ በዚህ ብሎግ እንዲቀመጡልኝ የምፈቅዳቸውን በተከታታይ ፖስት ለማድረግ አስባለሁኝ። www.tsegaye.ethio.info ያለው እንደ ተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው። ·        እንዲህ ነበር የተጀመረው በ2014 ጡሑፈ … አዳም እንደተቆለፈ ነው …. ለገርገብም .. እእ - ግን አዳም እንዴት ነበር ...