ልጥፎች

የጽናት ዋልታ ፈላስፋው ፕ/ ምንዳርአለው ዘውዴ - ሰማዕትም!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  „ አንቺ አገር ኢት ዮ ጵያ ? ! “ እውነትም ምንዳርአለው ዘውዴ! "ምድር ሁሉ እግዚአብሄርን አመስግኑ ዕለት ዕለት ማዳኑን አውሩ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፳፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie 22.01.2019  ከእመ ዝምታ።  የጽናት ዋልታ! „ሰው የሰማ ዕለት ያብዳል ይላሉ“  ጎንደሬዎች ሲተርቱ። እንዲህ ዓይነት የመከራ ናዳ በድንገት ሲሰማ። ·        መነ ሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=e8JL-SoUHTQ „ትግሬ ሆነው ይህንን ግፍ ሲሰሙ ምን አሉ ግን ? ያሳዝናል በልጆቻችሁ ለ 27 አመት ያልተሰራብን ግፍና ወንጀል የለም :: እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጠን ብቻ :“ ውዶቼ እንደምን አላችሁልኝ? የ27 ዓመታት ደመመናዊ ፍዳ - መሳደድ በዬሁኔታው እንዲህ የመርዶ መባቻውን በተለያዬ ሁኔታ እንዴት ናችሁ እያለ ራሱን ገልጦ እያሳዬን ነው … ጠንከር ብለን መጋፈጥ ነው። ጆሮም አላድምጥም አይልም፤ ዓይንም አላይም አይልምና። ባንታ ደል የሆነ ነው ...  ·        ግ ርምታ። „አንቺ አገር ኢትዮጵያ“ ርዕሱ የእኔ አይደለም የባለ ቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የቅኔ ዕርእስ ነው። ትርጉሙን እንደ አቅሚቲ እኔው ሠርቸዋለሁኝ። ረጅም ጊዜ ነበር የወሰ ደብ ኝ ወደ ሦስት ወር ያህል። የፈተነኝ ጉዳይ ነበር። መጻፍ ለእኔ ሥራ አል ነበ ረም ይህ ግጥም ግን እሽት ነበር ያ ደረ ገኝ። እርግጥ ነው በዶር አብይ አህመድ በ...

ሰሞናቱ ለረ/አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን እንዲሆን በጸሎት እንትጋ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዛብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ አማኑኤል ዛሬ እና ሰሞናቱን  አንድ የተባረከ ነገር  እንዲያደርግልን እማጸነዋለሁኝ። ይርዳን አንድዬ! ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22.01.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                     የተባረከ አሜን ለተባረከ ትውልድ! ዛሬ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲዊዘርላንድ እንደሚመጡ ዜና አዳምጫለሁኝ። እመኛው እሻው የነበረ ቀን ነው። እዚህ አንድ ውድ የሆነ የኢትዮጵያ ጀግና አለን። ይህ ጀግና ጀግንነቱ በተግባሩ ብቻ ሳይሆን በሰብዕናውም ጭምር ነው ። ስለ አገሩ አብዝቶ ያስባል፤ ስለ አላዛሯ ኢትዮጵያ በበዛ ሁኔታ እስኪገርመኝ ድረስ ይጨነቃል። በፈጣሪው እጅግ ያምናል አብዝቶ ይጸልያል። በባህሪው ጨዋ ወልዶ ጨዋ ያሰደገው ከመልካም ቤተሰብ የተፈጠረ፤ አሳዳጊውን ይባርከው የሚያሰኝ ነው። በመልካም ቤተሰብ በጥንቃቄ ያደገ ወጣት በመሆኑ በሁለመናው እጅግ ቁጥብ ነው። ብዙ የማይናገር፤ ብዙ የማይል፤ ብስጭት የሌለበት በፍጹም ሁኔታ የተረገጋ ወጣት ነው።  ስላደረገው ብሄራዊ አር ያነት አብነት ያለው ብጡል ብሄራዊ የጥቁር አንበሳ ገድል እና ወጣትነቱን ሳይሳሳ የማገደበት፤ ህይወቱን የሰዋበት መንገዱን በፍጹም ሁኔታ ይህን በማድረጉ እና ነፍሱን ችግር ውስጥ ማስገባቱ የማይ...

ዘመን ሲባረክ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዘመን ሲባረክ! „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“  ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie  ከእመ ዝምታ።                   የፈጣሪ ቅኔ! እንዲህ ነው ዘመን ሲባረክ! ሁሉን የሰጠው የጸጋ ቅኔ! የአሮን በትር መንገዱ ሁሉ ለምለም ነው! ኢትዮጵያን ቁም ነገር የማድረግ ዓላማ ያልኩትም ለዚህ ነው። እኒህ የተባራኩ የደግነት ቅዱስ አባት ዛሬ የመንፈስ ሃዲዳቸውን እንሆ አግኝተዋል። መልካሞች እንዲህ በመልካምነት ጋለሪ እሱ በወደደው እንደ ፈቃዱ ይገናኛሉ። ይህ ትልም የሰማይ እና የምድር ንጉሥ ክርስቶስ ነው። ቅዱሱ ፓፕ ፋርንስሲኮ ጸሎተ ሃሙስን በእስር ቤት ተገኝተው እስረኞችን ምንም የሃይማኖት ክትር ሳይሰራላቸው በ2013 እግር ያጠቡ ቅዱስ ናቸው፤ ተመሰገን! ከአሜኑ ጋርም ፈጣሪ እንዲህ በማይመረመር ጥበቡ አገናኛቸው። ተመስገን! ሐሤት አድርጌያለሁኝ። ፍቅር በመደብኛ ት/ቤት መሰጠት አለበት የሚለውን ሃሳቤን በ2015 ለሳቸውም ልኬላቸው ነበር። ከውስጤ በፍጽምና የማምናቸው ናቸውና። እኒህ የካተቶሊክ ሃይማኖት እጬጌ ተፈጥሯቸው ፍቅር ነው። ዓለም እንዲዚህ ዓይነት ቅዱሳን ቢበራከቱላት አስፈሪ አትሆንም ነበር። https://www.youtube.com/watch?v=bQfOhkweNCI Pope meets with Prime Minister of Ethiopia, Abiy Ahmed https://www.youtube.com/watch?v=hGTO57afPag&t=485s Ethiopia's Prime Ministe...

ጦርነት ህግ የለውም፤ ጦርነት ርህርሄ ያልፈጠረለት የክስረት ክስተት ነው።

ምስል
ጦርነት ህግአልቦሽ ነው! „የማላዬውን ነገር አንተ አስተምረኝ፤“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፴፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.01.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። „ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ የሚል የአቶ ዳውድ ኢብሳ “ መግለጫን አዳመጥኩት - ከልቤ ሆኜ። በኦዴፓ እና በኦነግ መሃል ያለው  ጋብቻም ይሁን ፍቺ በውነቱ ይ ኼ ነው፤ ያ ኛው ነው ለማለት ይቸግራል። ለሰሚውም ለፈራጁም ግራ ነው ።   ግራ የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን መሰከረም 5 እና ጦሱን፤ ቡራዩንና እና ሰቀቀኑን ስላዳመጥን ከባድ ነው ይህን ይኼነው ለማለት። ማን ምን እንደሆነ አሁንም መወ ሰ ንም መወ ገ ንም ይከብዳል። ሰርገኛ ጤፍ የሆነ ነገር ነው ።  ማን የዬትኛው ድርጅት ደጋፊ እንደሆን በቅጡ አይ ታ ወቅም። የትኛው ኦዴፓ የትኛው ኦነጋውያን እንደሆነ አንጥሮ ማውጣት መቼውንም የሚቻል አይደለም። ለውጡ እና ተጠቃሚው የኦሮሞ ማህበረስብ ገና ልብ ለልብ አልተገናኙምና።    የሆነ ሆኖ ከሆነ፤ የሆነውን በሆነው ነገር በትክክል መንግሥት መግለጽ ይጠ በ ቅበታል። አድሮ የሚገኝ ነገር። የፈለገ ይሆን የሆነውን እንቅጩን መናገር የተገባ ነው። አብሶ ለመንግሥት ታማኝነት ወሳኝ ስለሆነ። አድርገዋል የሚባለው ነገር አለ። መንግሥት ደግሞ አላደረኩም እያለ ነው። ቆይቶ ዕውነቱ ከተገኜ አብሶ መንግሥት አላደርኩም ባለው ላይ አድርጎ ከተገኜ ጥሩ አይሁንም። መታመንን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ት/ቤት ገብተው መማር ያለባቸው ይመስለኛል። ስለምን? የወል ችግራቸው ስለሆነ። በመንፈስ አቅም ማፍራት እኮ ከመታደል በላይ ...