ዘመነ ቤርሙዳ ትርያንግልን ለመመከት #ጥንቃቄ በአደብ ይጠጣ። ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም ነውና። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" #እፍታ ። ወጀቡ አዬለ። አቅጣጫውም ድብ አለበት እናም ዘለግ ያለ ሃሳቤን ማጋራት ፈለግሁኝ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ከመጡ ጉዳዬን በምዕራፍ ከፋፍዬ ስለምሰራ አስረአራተኛው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ለቅኖች ለማስታወስ። ፁሁፋ ዘለግ ያለ ነው። ለፌቡ አይሆንም። ግን ብሎግም ስላለኝ ለዛም ጭምር ነው እምሰራው። ለወሳኝ ፖለቲካዊ አቅጣጫ በጭልፋ የልብ አያደርስም እና ተያያዥ ጉዳዬወችን አክዬ፦ ወይንም እያጣቀስኩ አብረን እንሁን ስል ትህትናዊ አክብሮቴ ይጠይቃችኋል - ክብረቶቼን። #ውስጤ ። እንዴት ነን? #አይዞን ። ሁለ የርሱ፤ ሁሉም በእርሱ የሆነ አምላክ አለን። አቅማችን #አምላካችን ፤ ተስፋችን #አላሃችን ነውና። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ከአንደበት ጀምሮ ማናቸውም ኩነታችን ጥንቃቄ ይመራቸው ዘንድ ከእያንዳንዳችን በግል፤ ከሁላችን በጋራ የሚፈለግ የወል መስመራችን ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ። የትናንቱ የአዲስ አበባ የሽብር ክስተት አሳቻው ዘመን እና አሳቻው መሪ ዶር አብይ አህመድ አሊ ከመጡ ጀምሮ የተኖረበት የአዬር ፀባይ ነው። ባለመታደል። ትጋታችን መራራው የህዋህት ዘመን፤ በዘመናዊ የሽብር አገዛዝ እንዲሸጋገር አልነበረም። ቲም ገዱ ጥረታችን ለስልጣን አልታገልንም ብሎ በአፍጢሙ ከነበለው - እንጂ። አሁንም አዳኛችሁ ነኝ ሲል አዳምጣለሁኝ። የፊተኛውን በምን ቀበርከው በሻሽ፤ የኋለኛው እንዳይሸሽ" ነገረ ኢትዮጵያ ከአንድ ጠቅላይ ሚር፦ ከአንድ ዩቱበር፤ ...