ዘመንን ያናገረ ድንቅ ሰብዕና #ሐዋርያ ነው፤ #ቅኔበቃናየቀና። የሰዋዊነት ካፒቴንም ነው ልክ እንደ ክቡር (ዶር)ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ።
ዘመንን ያናገረ ድንቅ ሰብዕና #ሐዋርያ ነው፤ #ቅኔበቃናየቀና ። የሰዋዊነት ካፒቴንም ነው ልክ እንደ ክቡር (ዶር)ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ። አቤቱ ኢትዮጵያዊው #NBC ይቅርታ ጠይቅ። መራራ ስንብት የሙዚቃ ድግስን ስለሚጸየፍ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፯ ጤና ይስጥልኝ ቤተ ቅንነት? እንደምን ሰነበታችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ሰሞኑን #ተግ ብዬ ነበር። ምክንያቴ ኢትዮጵያ የውስጧን #ቅኔበቃናየቀናውን ልጇን ሞት ስለወሰደባት ነበር። የሆነ ሆኖ በኢትዮጵያ ህዝብ የእኛ ሃዘን ብሎ የተቀበለበት ዕውነት የእናቱን የልዕልት ኢትዮጵያ ኦርጋኒክ ተፈጥሮን ያነበበ፤ የተረጎመ፤ ያመሳጠረ ክስተት ነበር። የዘመኑ የኢትዮጵያ ልጆች በብሄራዊ ሰንደቅ፤ በታሪክ፤ በብሄራዊ መዝሙር፤ በዞግ፤ በወሰን፤ በሃይማኖት፤ ከዚህም ባለፈ በቀጨር መጨሬው የነበረው ጉጉስ #በአደቧ ፤ #በአቅሏ ፤ #በዋርካዋ ዋርካ የሚለውን ትምህርተ ጥቅስ ያላስገባሁት በጽኑ መታመማቸውን ስሰማ እራሴው የፃፍኩት ኃይለ ቃል ስለሆነ ነው። የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ አደብ፤ የኢትዮጵያ አቅልን በሥጋ መለየት በሚመለከት ሃዘኑ እኩል ስለሆነ መጽናናቱን ለሁላችን ይስጠን ፈጣሪያችን // አላሃችን። አሜን። የኢትዮጵያም የምር ሃዘኗ ነው እና እናት ዓለም ሆዴ እግዚአብሄር ያጽናሽ። አሜን። አንድ መንግሥታዊ ሥርዓት በሚወስዳቸው ማናቸውም እርምጃወች ቀድሞ የጨመተውን ማህረሰብ ዕይታ ማጥናት ይገባዋል። ሪሰርች ሊሠራ ይገባዋል። ውድቀትን ስለሚያመጣ። የክቡር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ (ዶር) ከሃላፊነታቸው መገለል ወይንም የተገለሉበት ሂደት በምን ያህል ልክ ኢትዮጵያውያንን...