#የመኖር #ቃና
#የእናትነት ጸጋ ሰላሙን ያገኝ ዘንድ ናፈቀኝ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፰። የሚናፍቀኝ ይህ የተፈጥሮ ውበት #ፍጹም ሰላማዊ የሆነ #የመኖር #ቃና እንዲኖረው ነው። ይህቺ እናት የዓለም ዓቀፍ የሞዴል ሥርዓትን #አዲስ #ምዕራፍ ይከፍት ዘንድ ይጣራል የውበቷ አቅም። በአማራ ወቅታዊ ሁነት ከአንድ ዓለም ዓቀፍ ዘገባ አየር ላይ ነው የወሰድኩት። ቆይቷል። እየተደራረበ እንዳላሰለቻችሁ በሚል አዘገየሁት። ኮስመቲክስ የለም። ሜካፕ የለም። ኩል የለም። ልብሱ በዲዛን አልተሰራም። ጫማው አልባሌ ነው። በፎቶ ሞድ ስልጠና አልተሰጣትም። ህፃኗ እጇን ወደ ላይ አድርጋ የታሰረ ነገር አያለሁኝ። ለምን? እንዴት? እራሱ የውሃ መያዣ ጀሪካኑን ወደድኩት። የገጠሩ የባንቡውኃ በአካል አየሁት። ብዙ ነገር የአገሬ ይናፍቀኛል። #ያ ዝክንትልትሉን ተሸካክሞ እዬተኩረፈረፈ የሚጓዘው ብስጩው ጎርፍ ሳይቀር። የሙኃይ #ቂጣማ ተውት። ጠረኑ ይመጣብኛል። ሥርጉትሻ 19/02/2025