የተባባል አርምሞ!
ብራቦ! አቶ ተቀባ ተባባል። ከሥርጉተ © ሥላሴ 22.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። "ማቅ ለብሼ በአመድ ላይ ሆኜ ስፆም እጸልይና እለምን ዘንድ ፊቴን ወደ ጌታ አምላክ አቀናሁ" (ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፫) ተንደፋዳፊዎች። የመሸባቸው ይንደፋደፉ። ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዋዜማ ላይም የታዬው ታይቷል። ሲነሳም የታዬው ታይቷል። አማራ ግን ደሙን ቀድሞ ስለገበረበት በሰላሙ ቀን ማገዶ መሆን ምርጫው ሊሆን አይገባም። ጥቅሙን ተጻሮ የሚቆም ተጠቃሚ የለም። እንደዛ እንደ ማበሻ ጨርቅ የተጠላው የአማራ የህልውና ተጋድሎ ከውሉ መንበር ላይ ነው። ዓለም ዓቀፍ እውቅናውን እና ተቀባይነቱን ማዬት ነው። የመንፈስ ዲታነቱ ልዕልናው ለሥነ - ልቦና ያጎረሰው ዘመን ጠገብ ትሩፋት እዮራዊ ነው። ታገድሎ እንዲህ ለአማረ እና ለሰመረ ድል ሲበቃ የመጀመሪያው ነው የኦሮሞ ንቅናቄ እና የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ። ፍሬውን ሰብሉን አይቷል። የማያሰፍረው፤ ከቶውንም የማይሸማቀቅበት እጬጌውን ብቃት፤ ብልሃት፤ ማስተዋል፤ ትእግስት፤ ልቅና ጥበብ ዓለም እዬታደመበት ነው። እንኳንስ ለራሱ ለሌለውም ተርፏል የደሙ ዋጋ እና ዕሴት። ስለዚህ አሁን ለህውከት ለብጥብጥ ለልቅልቅ ሲያምስና ሲያተራምስ፤ በሚዲያው በብራነው በማይኩ የከራረመው ይውጣ ይውረድ … አልፏል ታሪክ፤ ታሪክ ሰሪውን ለድል አብቅቷል። ሌላው ደግሞ እንኳነስ አጀንዳ ለሙግት የሚሆን አቅም የለም። ባለቅኔው ጠ/ ሚር የሚያነሷቸው ነጥቦች ለስላሳ ግን የአንበሳ ግርማ ሞገስ ያላቸው ናቸው። ብትንትኑ እያወጡት ነው የ43 ዓመቱን የሴራ ጋድም ገደል ፖለቲካን። ፈቃድ ለሴራ ፖለቲካ መንሳት። አማራ መሬት...