ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ።
ዬሞት ተማህጽኖ፣ የስቃይባለተስፋ። ምን እና ለምን ስለምንስ። ምን አድርገን ተገኜን??? ጭንቀት ያነሰን መሰለወትን? መሬት ደብድበው ማት አውርድ ብለው መና ለቤተ እግዚአብሄር ዬሚልኩ መሪ ነበሯት። ኢትዮጵያ። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይም በድምጽ ያገኙትን በትረ ሥልጣን በደም ጎርፍ አጥለቀለቁት። እኛ ቋያ ላይ ያሉ ቅኔወቻችን ነገን እንዲዩ እንዴት ዞር ሊሉ ይችላሉ እያልን እንጨነቃለን ህግ በሌለበት አናርኪዝም በሰፈነበት ባዕት፣ ባረገረገ ዙፋን ልቀቀል ብሎ መፍቀድ ሥምዬለሽ ማት ነው።።።።።።። ውጭ አገር እንደሚሰለቻቸው አውቃለሁ። ግን ይህም መከራ መቀበል ነው። እናቴ አዘውትራ ፃድቅ ትለኝ ነበር። የቀረብኝን ነገር ሁሉ ኡስባ። ፆምም ሲመጣ የሁልግጤ ፆሚነሽ እኮ ትለኝ ነበር። ከሚወዱት ባተሌነት መለዬት መከራን ፈቅዶ መቀበልም ነበር። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ዛሬ ምዕራፍ ዘጠኝን ልጀምር ሃሳብ አልነበረኝ። ሦስት ሃሳቦች ሲሞግቱኝ አድረዋል። አንዱ በቤተሰብ ጉዳይ ነው። ሁለተኛው ውሳኔ ነው። ባርች ሆይ ይቅርታ አድርጊልኝ። ሰላም ስጧቸው ቢያንስ አንቺ በመልካምም ቢሆን ሥማቸውን እንዳታነሺ ብለሽ የህማማት ዋዜማ ቃል አስገብተሽኝ ነበር። ይህም በመሆኑ ያዘጋጁት ዬሽግግር ሰነድ በማን እና በምን አመክንዮ እንደ ተጨናገፈ ስገልጽ ኢዴፓ እያልኩ ነበር። የሆነ ሆኖ አሁን ሞት ውሰደኝ፣ ጭንቀት እና ስቃይ ራዕዬ ይሁን ብለው ሲወስኑ ዝም ልል ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። ፈጽሞ። ላም እረኛ ምን አለ ዬእኛ ፖለቲከኞች ድርቅ ዬመታው አመክንዮ ነው። የብዙ ነገር ውድቀት፣ የብዙ ነገር ኪሳራ ዬሚነገረው ስለማይደመጥ ነው። ላደለው ንግግር ብቻ አይደለም ዬሚደመጠው። ፀሃይ አድማጭ ትሻለች። ንፋስ አድማጭ ይሻል። ተፈጥሯዊ ወጀብ አድማጭ ይሻል። የወፎች ዜማ አድማጭ ይሻል መ...