ልጥፎች

#የሚገርመኝ የኮፒ ራይት የይገባኛል #ስውር ሂደት።

ምስል
  #የሚገርመኝ የኮፒ ራይት የይገባኛል #ስውር ሂደት።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     በመጠነ ሰፊ ጉዳይ #የኮፒ ራይት ፍልሚያ አለ። ጎልቶም፤ ደብዝዞም። ድርጊተኞች ዝም ስላሉ፦ ትውር አትበሉብን #ዳንኪራም አዳምጣለሁ። እንዲህ ዓይነቱ ዕሳቤ ብዙ ተሳትፎወችን ያለዛል፤ ያዝላል፦ ወይንም ያኮማትራል። የህውኃት እና የአብይዝም ጦርነት ማገባደጃ ሰሞናት አንድ ቅን ሰው ቤተሰቦቹን፤ ወዳጆቹን፤ የትምህርት ቤት ጓደኞቹን ይዞ ለአንድ በጦርነት ለተሰዋ ሰማዕት ፋኖ እያንዳንዱ #በዓመት 600 ዶላር ማዋጣት አለበት ለሰማዕታት ቤተሰቦች፤ መጦሪያ ወይንም ለልጆች ማሳደጌያ በሚል ንቅናቄ ጀመሩ።    ግብረ ምላሹ ጥሩ ነበር። በኋላ የፖለቲካ ድርጅቶች ፋኖን ውሃ በቀጠነ እያነሱ ተደመምንበት ሲሉ በሳይለንት ማጆሪቲ የተጀመረው ንቅናቄ #ቀጥ አለ። ዘመነ አስተሮዬ ነበር ወቅቱ? ይህ ጠቀመ ወይንስ ጎዳ???? መዝኑት። በሌላ በኩል አማራን በሚመለከት ከህወኃት እና ከአብይዝም ጦርነት ጦስ ጋር የገነነ መከራ ነበር አማራዬ ላይ። ከ2023 ግንቦት በፊት። ከዛ #ያ ጉዳይ #ፀጥ አለ። ነገር ግን ስኬቱ በኮፒ ራይት ተንገላታ። ከዛስ? ያ የቅኖች ጥረት አሁንም #ፀጥ አለ።   አሁን በቅርቡ "ፋኖ በሚል ሥም ራሱን የሚጠራው የሚል ድምጽ ተደመጠ።" የሰከነ ተግባር በተከወነው ስኬት መነሻነት ደርጅቶ ክትትል ቢደረግለት የተገኜው ስኬት #ጥበቃ የበለጠ ያገኝ ነበር። በተጨማሪም ለአዲሱ ቻሌንጅ በር አይከፈትም ነበር የገዘፈ የህልውና፤ የገዘፈ የማንነት ተጋድሎ የሚዲያ ሰብል ብቻ በመሆን አዬር ላይ ከቀረ ነገም ያሳስባል። ምክንያቱም እኛ እያለን ይህን ያክል መከራ አማራ ተሸከም ከተባለ እኛ ስናልፍስ????    የ...

ይገባወታል።

ምስል
  ተመስገን አማኑኤል። እንኳን ደስ አለወት የተከበሩ አቶ ያሬድ ኃ/ ማርያም ዘመነወት ሁሉ #ለተፈጥሯዊነት እና #ለሰዋዊነት የሰጡ ምስጉን። ይገባወታል። ሁሉም በአንድ ድምጽ የሚስማማ ይመስለኛል። ኦባንግሻም ይህን ዕድል ቢያገኝ ምኞቴ ነው። ትጋቱን ስለማውቅ። እርግጥ ከሁሉም ነገር ቅድሚያ ሕይወቱ ያሳሳኛል። እኔ ተጨማሪ ሽልማቶችንም እጠብቃለሁ። ሰብዕናወት ርጉ ማህበረሰብ ለመፍጠር መሠረት ይሆናል ብዬም አስባለሁ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ሥርጉተሥላሴ SerguteSelassie 04/06/2024 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። ዕውነተኝነት እራስን ያስከብራል።

ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።

  ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።  ዕውነት ወለምታ ስለማይነካው።  ዕውነት ጋራጅም አያሻውም።  የሚወላልቅ፤ ተወላልቆ የሚገጥም #ብሎናም ስላልሆነ። ሥርጉ 2024/06/03

ለአማርኛ ቋንቋ ሌላ አማርኛ ቋንቋ አትፍጠሩ።

ምስል
  ለአማርኛ ቋንቋ ሌላ አማርኛ ቋንቋ አትፍጠሩ። ግልጽ እና ቀጥተኛ ቋንቋ ነውና።    ጣዕሞ ያለውም ግልጽ እና ቀጥተኛ ከመሆኑ ላይ ነው። እርግጥ ነው የሚያድጉ ልሳኖች፤ የሚዘምኑ ቃላቶች ይኖራሉ። ዘመን እራሱ ሥልጣኔ ስለሆነ።   ፌስቡክ፤ ጉግል፤ ኢንስተግራም ወዘተ አዲስ ናቸው።  ለዛ ማለቴ ነው።    የተቸነከረ ወይንም በሩ የተከፈተ ነው ለማደግ ለመሰልጠን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉ 2024/06/03

ለትውልድ ጤናማ ዕድገት

  ለትውልድ ጤናማ ዕድገት ስክነት፤ መረጋጋት፤ ለችኩል ጉዳዮች አደብ ገዝቶ መመርመር፦ #መመካከር ያስፈልጋል። በስተቀር ኮሽ ባለ ቁጥር መበርገግ ዓላማን ያስታል። ተስፋን ያኮማትራል።  ሁልጊዜ ተደላድሎ በማድመጥ ብቃት ክህሎትን ስለሚያጎናጽፍ፦ ደራሽ ጉዳዮችን አትኩሮት በመስጠት አብሮም ባለመግለብለብ እራስንም ትውልድን ያድናል።  ጥድፊያ፤ ግልብልብ ነገር፤ ብስጭት፤ እልህ #ለሰብላማነት ሩቅ የሚያጓጉዙ ሳንኮች ናቸው። #ጥሞና ለዬትኛውም መስክ ጠቃሚ እና አትራፊ ነው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉ03/06/2024

#መሪ ለመሆን ስታስብ

ምስል
    #መሪ ለመሆን ስታስብ ለኢትዮጵያ ተፈጥሮ ከማይመጡኑት እንቅፋት ባህሪያት ጋር መፋታት ይኖርብኃል። ኢትዮጵያ #በመንፈስ #የገዘፈች ናት።   ልጆቿም ደግና ታማኝ ናቸው። ስለሆነም መመጠንህን ምርምር ስራበት። ሌላ የመሪ ቤተሰቦች ወዳ ጅ ዘመዶች ሁሉ ምህረት አልቦሽ ሆናችሁ ልትነገሩት ይገባል ለተላላፊ። ኢትዮጵያ ኋላቀርነቷ ይበቃታል።    በዘለፋ እና በስድብ ትታወቅ ዘንድ አትታትሩ። እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዜጋ የአገሩ አንባሳደር ነው ሲባል በዛ ዲስፕሊን ውስጥ መኖርን ይጠይቃል።    መሪው ይሁኑ ሌሎች ባለምኞቶች ህይወታችሁ ያስተምር ዘንድ በራሳችሁ ላይ ሥሩ። መዳፈር ህዝብን ወይንም የህዝብ አካል ወገንን መዳፈር ነውር ነው። ኢትዮጵያን እዬገላመጣችሁ፤ እያዋረዳችሁ እና እዩዘለፋችሁ መሆኑን እሰቡት። ትውልድስ ማንን፤ ምኑን ሮል ሞዴል ይኑረው???   እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉ2024/06/03

ጥቂት ስለአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ስለ ፋኖሻ። አፈጣጠሩ #ክስተትም ነው። የፋኖ መንፈስ።

ምስል
  ጥቂት ስለአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ስለ ፋኖሻ። አፈጣጠሩ #ክስተትም ነው። የፋኖ መንፈስ። (በኦዲዮም ሠርቼዋለሁ በመሃል የአሜሪካ መግለጫ ሲመጣ ታገስ ተብሎ ነው።)   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     #መቅድም ። ፈኖ መሠረቱ #ገጠር ነው። ገበሬው ነው መሠረቱ። ይህ ማለት ተፈጥሮው #ተፈጥሯዊ ነው ማለት ነው። ችግር ኖረ አልኖረ ፋኖ ለተፈጥሮም ጥበቃ ታጥቆ በተጠንቀቅ ይጠብቃል ሁልጊዜም። ውሩሱ ቅርሱም ነው። ፋኖ #ቆቅ ነው። ፋኖ ጥሪቱ በራስ የመተማመን አቅሙ እና ፈራሃ አላህ ፈርሃ እግዚአብሄር መሆኑ ነው። #መታመን ።   በፋኖ ቤት #ዕብለት ፤ #ክህደት ዝር አይልም። ታማኝነቱ ተማላ አይደለም። ፍፁም እንጂ። #ሰብዕናው ።   ሰባዕዊ ትጉህ እና ታታሪ። ሥራ ወዳድ፤ በቲም ወርክ የሚያምን ዓራት ዓይናማ ነው።   #በጀት ። በጀቱ የራሱ የመኖር ዘይቤ ብቻ ነው።   #አደረጃጀቱ ። አደረጃጀቱ በተፈጥሮዊነት በሚያውቀው በዕቱ አበጥሮ፦ አንተርትሮ የሚያውቀውን መሪ በመፍጠር #በጎበዝ #አለቃ ይመራል።   #ማዕከላዊነት ።   በፋኖ ቤት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚል ውራጅ ማንነትን አይቀበልም። ያስፈነጥረዋል። አያውቀውም።    #ተጠያቂነት እና ኃላፊነት።   በራሱ ፈቅዶ የሚደራጀው ፋኖ በተፈጥሯዊ ይትብኃል፦ በአባት አደሩ ዘይቤ በጎበዝ አለቃ ደስ ብሎት ይመራል። ይህን ወዶና ፈቅዶ ስለሆነ ይቀበለዋል። ደስ ብሎትም ይፈጽማል። እጅግ በጣም ዲስፕሊን ነው። የተከረከመ። ጥንቁቅ እና የተግባር አንባ ነው። #ፋኖ እና የፖለቲካ ድርጅት።   ፋኖ ፖለቲካ ድርጅት የሚባል የትውስት አሰራር እና አረዳድ ግጥሙ አይደለም። እሱ በተመሰጠረችው እ...

#ኦባንግሻ የት ገባ?

ምስል
    ውዶቼ እንዴት አደራችሁ? #ኦባንግሻ የት ገባ? የአገራዊ ምክክሩ ቀንዲል ሊሆን ሲገባ አላዬሁትም። የቁም እስር ሆነን? ግዞት ላይ ነውን???   እኔ እኮ በ2010 ነሃሴ ላይ ተስፋው መጠለፋን ነግሬው ግን ሄደ። በአብይዝም ዬምክክር ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅም አልነበሩም? ለምን?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ሥርጉትሻ2024/06/04