ዕውነት ዬሕይወት #ውበት ነው። ዕውነት ከህይወት ጋር ሲዋህድ ጠረኑ ለሰው ልጅ #ቅርብነት ነው። ዕውነት ሲኖር ቅርብ የሆነ የሰው ልጅ #ሽታ #በጣዕም ይከሰታል። ዕውነት ስለሰው ልጅ #ቅርፅ አይደለም። #እእ ። የሰው ልጅ ሰብዕና የይዘቱ ፍልስፍና የዕውነት ውበት ነው። ሥርጉትሻ2024/07/19 #ስኬት የሰማይ #መና አይደለም። ስኬት የአመራር #ብቃት ውጤት ነው። #ልቅናም የአመራር ጥበብ ሥልጣኔ ከከፍተኛ እርከን ሲደርስ የሚገኝ ውጤት ነው። #የአመራር #ብቃት + የአመራር ጥበብ #ልቅና = #የአመራር #ልዕልናን ብራንድን ይፈጥራል። ይህ እንግዲህ ለታደሉት የሚሰጥ ፀጋ ነው። መማር ብቻውን ለዚህ የሚያበቃ አይመስለኝም። የማስተዋል፤ የአትኩሮት፤ የማቀድ፦ የመረጋጋት ተመስጦ እና የመፈፀም ክህሎታዊ አቅምን ይጠይቃል። ከሁሉ የፈቃደ እግዚአብሄር እና የፈቃደ አላህ መቅደም፤ ጥሞናዊ ራስን የመግራት ሂደት የስኬትን #ደርባባ #ቋሚ #አሻራን ይወልዳል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ሥርጉትሻ2024/07/19