ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት።
· ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት። ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራር። „ኃጣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታም“ (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 2 ቁጥር 9) ኢትዮጵያዊነትን ያከበረ፤ ያጸደቀ፤ ያሰበለ ለካቴና ሲሰጥ ኢትዮጵያ የት ነሽ ብሎ መጠዬቅ ይገባል። አወን ኢትዮጵያ ካቴና ላይ ናት። ለምን „በገዳ መደመር“ ስላልተካተተች። ይህን አሻም ያሉ ካቴና ላይ ናቸው። ወይንም በረጅም ገመድ በቁም እስር። እሺ ያሉ ደግሞ በከራባት እና በገበርዲን ሰርግ እና መልስ ላይ። ኬክም አለበት። ኢትዮጵያም ሙሉ ወርዱ ቀርቶባት ማቅ ለብሳ ትንፋሽ ባገኜች ምንኛ ዕድለኛ በሆነች ነበር። ህወሃት መራሹ ኢህዴግ የከታተፋት ኢትዮጵያ እንኳን አሁን የለችም። ድፍን ነገር። አቶ እስክንድር ነጋ ሲታሰር እኮ ነገሩ አብቅቷል። እ። ከዛ በፊት ኢንጂነር ስመኜው በቀለም ሲገደሉ የኢትዮጵያ ሉዕላዊነት ተረሽኗል። ነገረ አባይ እኮ ረግረግ ውስጥ የገባው ለዛ አሉታዊ ዴሞግራፊ የኮፒ ራይት ሽሚያ ላይ ሲዳካ ነበር። ግን ልብ መሸመቻ ይኖር ይሆን? እህ። ማፈላለጉ ይገባል ብዬ ነው። ገዳ አባይ የእኔ ነው አለ። ሊቃውንታቱ የፈለሰሙት፤ የመሩት፤ ያስተዳደሩት በእኔ ጠረን ነው ሲል ነበር አብይዝም ታላቁን ምስክር በአደባባይ በእርስ መዲናዋ ደመ ከልብ ያደረገው። የሄሮድስ መለስ ዜናዊን ፈጣራም በአደባባይ ነው የተዘረፈው። መስዋዕትነቱን እንደምን እንደ ተቀረደደ እራሱ ዘመን ይገልጠዋል። ዘመን ያብራራዋል። ተከድኖ፤ ተከርችሞ፤ የሚቀር ምንም ነገር የለም እና። ...