ልጥፎች

ደስታን በልክ መያዝ ይገባል። ሳያንጠራሩም //// ሳያንኳስሱም። የአምባሳደር ሬድዋን የእንኳን ደስ አለን መልዕክት

ምስል
  ደስታን በልክ መያዝ ይገባል። ሳያንጠራሩም //// ሳያንኳስሱም።     ለምን? 1) ዬአሳቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሶፍት ዌር ስለ ነገ ምን ፕሮግራም እንዳደረገ ስለማናውቅ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዚህ ቦታ ቢኖሩ ብላችሁ እሰቡ። ላይ ላይ ጋላቢው እና ፈረሰኛው የዶክተር አብይ ሶፍት ዌርን በማስተዋል እንደማለት። ይልቅ አቶ ሬድዋን ሲሸኙ ለአህጉር፤ ለዓለም አቀፍ ተቀጣሪነት እጮኛ ለመሆን መደላድሉ ተሠርቷል። 2) የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ልብ የሚጣልባቸው አይደሉም። ሁሉም። 3) ዬኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅኝቱም ሆነ ተፈጥሮውም ጆሮ ደግፍ የያዘው ነው። 4) ሌላ ተጨማሪ ደሥታ ካገኛችሁ መደርደሪያው እንዳይሞላባችሁ ቀንሳችሁ ተደሰቱ። 5) በሌላ በኩል ደሥታው ህልም ዕልም ከሆነ ተስፋ ቆራጭነት፤ ሲከተል የሥና - ልቦና ህመም እንዳያመጣ። 6) በመጨረሻ ፈጣሪ አመጣጥኖ ባልተያዘ አመክንዮ ምርቃቱን ስለሚያነሳ በልክ ሁኑ፤ በልክ አግርጉት። በፐርሰንት ቢወጣ አትራፊው፤ ድል ያደረገው ማን እንደሆን ሆዳችሁ ያውቀዋል። ደግሞ ፍርስርሳችሁ ወጥቶ ለሦስተኛ ጊዜ ኖ ሞርን እዘሉልን ካላላችሁ??? ለዚህ ሁሉ ዬህዝብ ሠላማዊ ሠልፍ ብክነት ነበር። ለዚህም ነበር ሽሬ ላይ እኒያን ዬእግዚአብሄርን ሰው ሚዲያ ላይ ስታወጡ፤ ወሎ ላይ አስተኳሹን ስታወጡ ተው ያልኩት። ዬትናንትም የዛሬም ዬኢህዴግ ልሳን ይህን ብለዋል። "ዬዛሬው ቀን ኢትዮጵያ እና ሰላም ድል ያደረጉበት ቀን ነው። ልገልፀው ዬማልችለው ደስታ ተስምቶኛል።" አዲሱ የፋና አንባቢ እንዳቀረበው። ለዚህን ጊዜ ማን እንደሚፈለግ ታውቃላችሁ። ዬአንባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚሩ የደህንነት አማካሪ የተናገሩት ነው። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ደግሞ ይህን አስፍሯል። Daniel Kibret@danielkibret «ኢትዮጵ...

በጎርፍ ጥቃት ጋንቤላ ውስጥ የወገኖቻችን መፈናቀል።

ምስል
  በጎርፍ ጥቃት ጋንቤላ ውስጥ የወገኖቻችን መፈናቀል።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ከሀምሌ 17/2014 ጀምሮ በጋንቤላ ከጣላው ዝናብ መጠን ማለፍ ጋር ተያይዞ 12 ወረዳወች የጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ 185 ሺህ ነዋሪወች ጉዳት እንደረሰባቸው ታውቋል። ጎርፋ የዘመኑን የእርሻ ማሳም አብዛኛውን እጁን እንደጎዳው እና ነዋሪወች ቅጠላ ቅጠል ለመብላት እንደተገደዱ ዜናው አመላክቷል። ዘገባው የህብር ራዲዮ ሲሆን ምንጩ ኦቻ መሆኑን ህብር ገልፆል። እግዚዬሩ ምን ነካው ያሰኛል። መከራ ያነሰን ይመስል ቅጣቱ በዛ። ዬሆነ ሆኖ ዘመን ያለው የዶር አብይ መንግሥት ከቤተ መንግሥት ቤተ - መንግሥት ቅንጦትን ተግ አድርጎ፣ ለግብረ ሰላም፣ ለምቹ ሆቴል መስተንግዶ ሰርክ የሚወጣውን ወጪ ተግ አድርጎ ለጨዋ የጋንቤላ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ ትሁታዊ ማሳሰቢያዬን አቀርባለሁኝ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እንዴት አደራችሁ ክብሮቼ። ደህናም ዋሉልኝ። አሜን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 28/10/2022 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

ጁቪተር ላይ ዬባጁት ከፍተኛው የህግ ባለሥልጣን።

ምስል
  ጁቪተር ላይ ዬባጁት ከፍተኛው የህግ ባለሥልጣን።   "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ምን አደረግሁህ የማከብርህ ጋዜጠኛ አቶ ሥሜንህ ባይፈርስ ማህፀኔ የተቀረደደበት መልስ ነው ያዳመጥኩት። ጋዜጠኛ ሥሜነህ የሚደንቀኝ ጋዜጠኛ ነው። የእኔ ሥም በሥውር አዋጅ በዬትኛውም ሚዲያ አይነሳም። በግል መልካም የተደረገላቸው ሰብዕናወች እኔን ላለመጥራት ፓራሳይት ይፈልጋሉ። የሚጠለሉበት። የፖለቲካውን ትቼ ማለት ነው። ለነፍስ የሚደረስላቸው እንኳን አይደፍሯትም ሥርጉተ ሥላሴ የምትባልን ሥም። ሃሳቤን ይጠቀሙበታል። ግን ምንጩ ይሰወራል። የቁም እስረኛ። ለጥቂት ጊዜ እናቴን በስልክ አገኝ ነበር ከህወሃት ሽኝት በኋላ። አንድ ቀን እንዴት ያለ ደፋር፤ ጀግና ጋዜጠኛ ቢሆን ነው ሥምሽን ያነሳው፤ በዋልታ ቴሌቪዥን ሁለትጊዜ አነሳሽ። አንቺም ደፋር ዶር መራራ ጉዲናን ሞገትሽ። እና ይህን አዳመጥኩት። በአጠገቤ ብትኖሪ እሸልምሽ ነበር። ለእሱ ደግሞ እፀልይለታለሁ አለችኝ። ሥሜን ስለ አነሳ ሳይሆን አብዮት ስላካሄደ ነው እሚደንቀኝ። ዬእኔን ሥም ማንሳት እንደ ወንጀለኛ ነው ዬሚያስቆጥረውና። ይህን በመርኽ ደረጃ በረቂቅ ሁኔታ የሞገተ ነው። ውስጡን አይቸበታለሁኝ። ጠረኑ ምን ንጥረ ነገር እንደሚያፈላልግ ተረድቻለሁኝ። ዛሬ ጥዋት ያገኜሁት ቃለ ምልልስ ይገርማል። #ከህዲ ለፍትህ??? #ካሃዲ ለዕውነት??? #ዓይኔን ግንባር ያድርገው ባይ ለከፍተኛው የፍትህ አካልነት? ሥማቸው አልተጠቀሰም - ተጠያቂው ማህበረ ኦቦ ይሆናሉ። ኃላፊነታቸው አልተጠቀሰም የሁሉም ቦታገዢ ማን ስለመሆኑ መከደን ስላለበት። እንዲህ በመናጆ የሃሳብ ፈሰሱን ውልብልቢት ይዤ ስጓዝ ያው የእሱበእሱ ቤተ -ላዕላይነቱ ስለመሆኑ ውይይቱ ፍንጭ ሰጠኝ። "መግቢያው በዳኞች በአጠቃላይ ዬፍትህ አካሉ፤ ዬዳኞች የዲስፕሊ...

"የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሲጀመር ጥቁር፣ትውልደ ህንዳዊው አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ይሳካለት አይሳካለት፣ በቢሮው ይቆይ አይቆይ ጊዜ የሚፈታው ሆኖ "

ምስል
  Yaekob Yisahk   · ሥትሰለጥን…!   "…የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሲጀመር ጥቁር፣ ያውም ኬኒያዊ መሠረት ያለው ጥቁር፣ በዚያ ላይ ሙስሊም የነበረ ኋላ ላይ እስልምናውን የለወጠ ሰው ነው። በነጮች ዓለም። የመጨረሻውን ወሳኝ የሥልጣን ቁልፍ በጠይም ቆዳ፣ ያውም በጥቁር ይያዛል ተብሎ በማይታሰብበት ሃገር፣ በዚያ ላይ ሃይማኖቱ ብዙዎችን በሚያስበረገግበት ሰፈር አሳምኖ፣ ቆመው አጨብጭበውለት፣ አንድ አይበቃንም ድገመን ብለው 8 ዓመት እንዲመራቸው ወደውና ፈቅደው የታላቋ አሜሪካ ፕሬዘዳንት ሆኖ መርቶ በክብር ሥልጣኑን ለቋል። ይሄ የሆነው በሰለጠነ ማኅበረሰብ ዘንድ ነው። "…አሁን ደግሞ ልዑሉ ያገባት ሴት የቆዳ ከለሯ ነጣ ያለ አይደለም። የሚወለደው ልጅ ከለር ምን ሊመስል ይችላል? ብለው ንግሥቲቱ በጭንቀት ሊሞቱ በደረሱባት ሃገር ሌላ ክስተት ተፈጥሯል። እንግሊዝና ዘረኝነትን መንገር መቼም ለቀባሪ እንደማርዳት ነው። እናላችሁ እዚሁ ጎረቤት ሃገር እንግሊዝ ሌላ ኦባማዊ ታሪክ ተፈጥሮ ነጩ ዓለም ጉድ ጉድ እያለ ነው። "…ታላቋ እንግሊዝ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ Totally ይሉታል እነሱ ቶታሊ የሃገሯን 1ኛ ደረጃ ሥልጣን ጠቅላይነቱን የህንድ ዝርያ ላለው ሪሺ ሱናክ ሰጥታው የነጩን ዓለም አስደምማዋለች። በእንግሊዝ ነጩም፣ ጥቁሩም እርግጥ ነው ሠርቶ ይበላል። ለጠቅላይነት ግን የማይታሰብ ነው። ንግሥት ኤልሳቤጥ ይሄን ሳያዩ እንኳንም አረፉ የሚሉም አሉ። ትውልደ ህንዳዊው አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ይሳካለት አይሳካለት፣ በቢሮው ይቆይ አይቆይ ጊዜ የሚፈታው ሆኖ ለጊዜው አሁን የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ነገር ግን በሠለጠነው ዓለም ዓይናችን እያየ ጆሮአችንም እየሰማ ይሄ ተፈጽሟል። "…ነፍጠኛ ከክልላችን ይውጣ…!! ወራ...

ጋዜጠኛ ጎበዜ ጎበዙ እራህብ የወባ ወረርሽኝ፣ ሌላም ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚሻገር አባ ሰንጋ በሽታ መከሰቱን ገልፆ ነበር።

ምስል
  ጋዜጠኛ ጎበዜ ጎበዙ እራህብ የወባ ወረርሽኝ፣ ሌላም ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚሻገር አባ ሰንጋ በሽታ መከሰቱን ገልፆ ነበር።   አሁን የዓለም የጤና ድርጅት የወባ ወረርሽኝ መጠናከሩን በአማራ ክልል እና በትግራይ ገልፆል። በምን ምክንያት ስለመሆኑ በሚገባኝ ልክ በዚህ መግለጫው ለመጀመሪያ ጊዜ WHO "አማራ ክልል" የሚል አካቷል። ይህንን ያሳወቁት WHO የድርጅቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኢኃም አብዱላሂ ስለመሆናቸው ተገልጧል። ዘገባው የህብር ራዲዮ ነው። ስለ ወባ ወረርሽኝ ካነሳሁ ዘንድ ህወሃት ድርጅቱን የወባ ማጥፊያውን ቢሮ በአማራ ክልል ዘግቶት ነበር። የወባ ወረርሽኝ ተቋም ዬነበረው ትግራይ ብቻ ነበር። ስሜን ጎንደር በወባ ወረርሽኝ ከሚጠቁት አንዱ ነበር። ዬእኔ ቤተሰቦች በሙሉ ነበረባቸው። ያው ሰቲት ሁመራ ይኖሩ ስለነበር። የበሞቴ ልዕልቴ እናቴ ነበረባት፣ የአብርኃሙ ቤት አባባም ነበረባቸው። አስታውሳለሁ በልጅነት ደብረሰላም ትምህርት ቤት አንባጅኔ ከነበረው የወባ ማጥፊያ ድርጅት በጥዋት ሄደው ምርመራ ቤተሰቦቼ ሲያደርጉ። ነገርግን አንባጅኔ ዬነበረውን የወባ ማጥፊያ ድርጅቱን ዘግቶ፣ ብልኮ ያለውን በደሙ ዋጋ ያገኜውን የጎንደር ህዝብ ጄነሬተር ህወሃት ሥልጣን ሲይዝ ነቅሎ ወሰደው። በኋላ ስሰማ ጅማም፣ ወሎም መሰሉን የጠራራ ጠሐይ ዘረፋ መፈፀሙን አዳመጥኩኝ። መብራትም ጤና ህዝብን ነፍጎ 27 ዓመት አገር መራ። አሁን የሚኒሊክ ቤተ - መንግሥትን ኩንትራቴ ለ100 ዓመት ነው ብሎ በይገባኛል ጦርነት ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም ከ50 -60 ዓመት ብለውናል። ትውልድ የሚያንፁበት በገዳ ርዕዮት ማለት ነው። ወደ ቀደመው ጭብጤ ስመለስ ኃላፊው አያይዘው የገለፁት የትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ በትግራይ ችግሩ ተባብሷል ይላል። ...

የብዕር አንጋች ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ዕውነት። "ነፃ የተባለው ጋዜጠኛ ተመስገን"

ምስል
  የብዕር አንጋች ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ዕውነት። "ነፃ የተባለው ጋዜጠኛ ተመስገን"    አርቲስት ታሪኩ ደስአለኝ ያገኜሁት ነው። "ተመስገን ደሳለኝ ሲታሠርም ነፃ እንደሆነ አውቃለሁ። የታሰረውም ፍትህ ለማስከበረ ሳይሆን፤ የፖለቲካ ውሰኔ ለመሆኑ ከአስተሳሠሩ ጀምሮ እንደ አድር-ባይ ካድሬ አቋም ሲቀያየር የነበረውን የክሱን ሂደት የተከታተለ ሁሉ አብዝቶ የተረዳው እውነታ ነው። ይህም ሆኖ፣ የፍርድ ሂደቱን በተመለከተ ችሎቱ ላይ ከሚከናወኑት ነገሮች ውጪ ላለፋት አምስት ወራት የራሴን ሃሳብ ሳልጨምር ሂደቱን ብቻ አስተላልፌለሁ። ከአምስት ወራት በኋላ ጥቅምት 11/2015 የጋዜጠኛ ተመስገንን የፍርድ ሂደት ሲመለከት የቆየው ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት ተመስገንን በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ በወ/መ/ስ/ስ/ቁ 141 መሠረት መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት በመወሰኑ ሙሉ በሙሉ ነፃ ተብሏል። 3ኛውን ክስን በተመለከተ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 113(2) መሠረት በመለወጥ የጥላቻ ንግግርን እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 ላይ እንዲከላከል አዝዟል፡፡ አሁን ይከላከል በተባለበት አንቀጽ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ እንኳ ከገንዘብ ቅጣት ያለፈ የሚያሳስር አለመሆኑ በአንቀጹ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። በመጨረሻም፣ የዚህ ፍርድ ቤት ውሳኔ በብሔር መቀስ ተቆራርጠው ይንሻፈፉ ዘንድ የተፈረደባቸውም ሆኑ ኤዲት ለተዳረገ ክስ የተሰዉት የጋዜጠኛ ተመስገን እውነታዎች ወደ ክብራቸው ለመመለሳቸው በቸኛ ምስክር ሆኗል። እደግመዋለሁ ጋዜጠኛው ወንድሜ፦ ከታሰረ ጀምሮ ይሰሙ የነበሩት እነዚያ አሳዛኝ ስሁት ፍረጃዎች፣ እነዚያ ከአውዱ የተገነጠሉ የፌስቡክ ውንጀላዎች፣ ...

ዕውነት አያፍርም። መርኽም አይርድም።

ምስል
  ዕውነት አያፍርም። መርኽም አይርድም።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ዕውነት ለመርኽ፣ መርኽ ለዕውነት ባይተዋር አይደሉም። በመርህ ውስጥ ዕውነት ያሰበለ ነው። በዕውነት ውስጥም መርህ ዬፀደቀ ነው። ድልድያቸው ፋክት ነው። በዚህ ውስጥ የሰከነ ሰብዕና፣ በዚህ ውስጥ አደብ የገዛ ሰብዕና፣ በዚህ ውስጥ ዬተረጋጋ ሰብዕና ወጀብ፣ አውሎ፣ አያላጋውም። የመጣ - ቢመጣ፣ የሄደ - ቢሄድ አይደንቀውም። ዕውነት ጽኑ ነው። እርግጥ ነው ሠራዊት የለውም። መርህም ጽኑ ነው። እርግጥ ነው ሠራዊት የለውም። ፋክት ግን ለሁለቱም አይለያቸውም። የእግዚአብሔር ጥበቃም። ዕውነት አቋሙ የሆነ ሰብዕና ሲፈላ - አይፈላም፣ ወይንም ተንተክትኮ እሮ አይሆንም። ሲበርድም ቀዝቅዞ ወደ በረዶነት አይቀዬርም፣ ለብ ብልጭ ድርግም እያለ ሲልም አያንጎላችም። ምክንያት። ዕውነትም መርህም አይፈሉም፣ ወደ በረዶነትም አይቀዬሩም፣ ወይንም ለዘው አያፏሹኩም። በተከተታይ ትጋት፣ በተፈጥሯቸው ልክ አሽተው በልካቸው መስመራቸውን ዝንፍ ሳያደርጉ ይጓዛሉ። ስለዚህ በአንድ ወቅት የደገፋቸው በሌላ ወቅት ጥሏቸው ሊሄድ ይችላል። በአንድ ወቅት ያቃለላቸው እና ቸል ያላቸው ደግሞ ይመለስ እና ከጎናቸው ይቆማል። እነሱ ግን ያው እነሱ ናቸው። አይበልዙ፣ አይማርቱ። የወቅት አሞጋሾቻው ጎርፋ ሲያመጣው እና ሲወስደው ያያሉ፣ ያስተውላሉ፣ ይመዝናሉ። እነሱ ግን ጨለማ፣ ብርኃን፣ ቀን - ሌሊት፣ በጋ - ክረምት ፀደይ በልግ ቢፈራረቁም ምንጊዜም በወጥ ተፈጥሯቸው ይቀጥላሉ። ለክረምት ጋቢ ወይንም ካሊም፣ ለበጋ ቁምጣ ወይንም ቀለል ያለ አልባሳት አያሰኛቸውም። በሰወች ያለው ዕውነት እና መርህ፣ በተቋማት ያለ ዕውነት እና መርህ መለኪያቸው ነው። ዕውነት ዬተለዬ አጤ ዬለውም። መርኽም የተለዬ ጳጳስ የለውም። ሥርዓት ሲጣስ በህ...

ጓድ ገዛህኝ ወርቄ እና ማስተዋለቸው ጎንደርን ዳግም ወለደ። #ህወሃታውያን ከጓድ ገዛህኝ ወርቄ ተማሩ። እባካችሁ???

ምስል
  ጓድ ገዛህኝ ወርቄ እና ማስተዋለቸው ጎንደርን ዳግም ወለደ። #ህወሃታውያን ከጓድ ገዛህኝ ወርቄ ተማሩ። እባካችሁ???   በዚያ ከቆሙት ውስጥ የዐፄ ቴወድሮስን ጃንሆይ እንግዲህ መሞታችን ካልቀረ የዚህ ጦርነት ምክንያት የሆኑትን፣ እነዚህን ዬታሠሩትን፣ እንግሊዞች መጀመሪያ ገድለን፣ እኛም ሄደን እንሙት ብሎ አማከራቸው፣ ንጉሡ ግን ያገሬን ሕዝብ አንድ ለማድረግ እኔ ያጉላላሁት አንሶ ደግሞ እነዚህን ገድዬ ሕዝቤን በውጪ አገር ሕዝብ እንዲሰቃይ አላደርግም" (ከሊቁ ብላቴ ጌታ ፀሐፊ ተክለ ፃድቅ መኩሪያ ከዐፄ ቴወድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መጽሐፍ ዬተወሰደ ገጽ 38) "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ዬተከበሩ የጓድ ገዛህኝ ወርቄን ፎቷቸውን ለማግኜት ብዙ ደክሜያለሁ። ላገኜው አልቻልኩም። ጓድ ገዛህኝ ወርቄ የደርግ አባል ነበሩ። የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ነበሩ። የባሌም የጎንደር ክፍለ አገርም የኢሠፓ አንደኛ ጸሐፊ ነበሩ። ጎንደር መመደባቸው እንደ ልዩ መታደል ያዩት ነበር። ጎንደር የጦርነት ቀጠና ነበር። ወገራ አውራጃ፣ ስሜን አውራጃ ሁልጊዜ ጉድብ ውስጥ ነበር አዳሩ። ወደ ጋይንት መስመርም በለሳ አርባያ መሰሉ ችግር ነበር። የጎንደር ርዕሰ መዲናነት የተመረጠው በቀደመው ጊዜ እስትራቴጂካል ጠቀሜታው ተሰልቶ ነበር። የህወኃት የዘለቀ ህልሙ ጎንደርን መጠቅለል ነበር። ምክንያቱም መንፈሳዊውም፣ ተፈጥሯዊውም ሙሉዑ ስለሆነ። ይህም በመሆኑ ያለው ሥርዓት አልተመቸኝም የሚለው ሁሉ የሚተመው ወደ ጎንደር ተዋጊ እና አዋጊ መልክዕ ምድራዊ ቦታ ነበር። ከሁሉ በላይ ለምለም መሆኑ ለአማጽያኑ መኖር ምቹም ነው። ዬህዝቡ እርህርህና መለኪያ ዬለውም። ስለዚህ ጎንደር የውጥረት ማዕከል መሆኗ ተፈጥሮ ለእርግማን ይሁን ለጽድቅ የሰጣት ነው። ወቀሳው፣ ነቀሳው፣ በረዱ...

ብቸኛው በኖህ መርከብ ቅርፅ የተሰራ ቤተክርስቲያን የሚገኘው ኢትዮጵያ ብቻ ነው

ምስል
  ከአቶ ጋሻው አባተ ያገኜሁት ነው።    የዛሬ ዓራት ዓመት ፌስቡክ ስጀምር ፕሮፋይሌ ነበር። ዕትብቴ ዬተቀበረበት። ፊደል የቆጠርኩበት፣ ያደግኩበት። ማህሌቱ፣ ዝማሬው፣ እጣኑ ጠጅ እሳር እሪያኑ፣ ጉሬዛው፣ እንቁላል ግንቡ፣ ቅጽር ግቢው፣ የወይራ ፍሬ ለቀማው፣ የአባ በጠኃ ቅኔ ቤት፣ የአባ ጌራ እና አባ ኃይለማርያም ፈገግታ፣ የመላከ ብርኃናቱ ቤተሰቦቼ የአብርኃሙ ቤት ……የተድያን መስተንግዶ ……… ይህን በነፍሱ እስከነ ግጥሙ እኔ ሠርቼዋለሁኝ። ይህንን ያውቁ ኑሯል? "በዓለም ላይ ብቸኛው በኖህ መርከብ ቅርፅ የተሰራ ቤተክርስቲያን የሚገኘው ኢትዮጵያ ብቻ ነው በእጃቹህ ያለውን ወርቅ ተዋወቁት።ይህ የምትመለከቱት ቤተክርስቲያን በ16ኛው ክ.ዘ የነገሠው የአፄ ፋሲል የልጅ ልጅ አለም ሰገድ(አድያም ሰገድ) ኢያሱ በኖህ መርከብ አምሳያ ጎንደር ከተማ ላይ ያሰራው ቤተክስቲያን ነው ስሙም ደብረ ብርሃን ሥላሴ ነው ይህ ዓለም የሰገደለት ንጉሥ ክህነትን እና ንግሥናን ሁለቱን ስልጣን በማጣመር ኢትዮጵያን ገዝቷል ቤተመቅደስ ገብቶ ካህን ሁኖ ይቀድሳል ቤተመንግስት ደሞ ንጉሥ ሁኖ ሀገር ይመራል አንዲያውም ይሄ ንጉሥ አክሱም ጽዮን ማርያም በመሄድ ታቦተ ጽዮንን ተሸክሞ ንግሥና እንዳከበረ ይነገርለታል።ልብ በሉ በመፅሐፍ ቅዱስ በጣም ገናና ከሆኑት የእስራኤል ነጉሦች መካከል ንጉሥ ዳዊትና ጠቢቡ ሰለሞንን እንኳ የኢትዮጵያውን ንጉሥ ቋረኛው እያሱን ያክል ስልጣን አልነበራቸውም ለምን ዳዊትና ልጁ ሰለሞን የክህነት ስልጣን አልነበራቸውም ነበር የክህነቱን ቦታ የሚያገለግሉ የሌዊ ነገዶች ብቻ ናቸው የኢትዮጵያ ነገሥታት ግን ከንጉሥነት አልፎ ካህንም ነበሩ ለዛ ነው የውጭ ሀገር ታሪክ ጽሐፊዎች የኢትዮጵያን ነገሥታት ሲጠሯቸው "prester john" ነው ሚሏቸው ትርጉ...

"ዓለማየሁ ቴዎድሮስ

ምስል
ከአቶ ፈለቀ ዜና ያገኜሁት ነው። ከታሪክ መንበር። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።" "ዓለማየሁ ቴዎድሮስ በሌላ ቋንቋ ለማንበብ ለመከታተል     "ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የ ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ነበር። በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ በዛሬው የኛ አምዳችንም የዚህን ልዑል ባዕድ ሀገር ኑሮ ልናስቃኛችሁ ወደድን፡፡ ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብተረ ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡" "በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ከልዑሉ ጋር ሲጫወቱ መዋል አፄውን እጅግ የሚያስደስት ነገር ነበር፡፡ ተናደው እና ተበሳጭተው ከነበር እንኳን አለማየሁን ታቅፈው ሲስሙ ንዴታቸው ይበርድ ነበር ይባላል፡፡" "ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ ቡሀላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡ ፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡" "በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እና አጫዋቾች¬ ተመረጡለት፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡" "በመርከቢቱ ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ አለማየሁን ማስ...