Julay 12/ 2021
ከአራት ወር በፊት አዲስ አበባ በዝምታ ምርጫዋን አጠናቀቀች ብዬ ጽፌ ነበር። ያልኩት አልሆነም። የአጣዬ መቃጠል ለዛ ድል ነበር። ስጋት ሽብር ለማህበረ ኦነግ የድል ርካብ ነው። መከራውን በልኩ መረዳት ይጠይቃል። እኛ ገና ለብም አላልነም። "ተረኝነት" የሚሉ ፖለቲከኞች የገዳን ወረራ፣ የገዳን አስምሌሽን፣ የገዳን መስፋፋት ሲያቆላምጡት ባጅተዋል። የትግራይ እና የፌድራሉ ጦርነት የገብር አልገብርም መሆኑንም በጥዋቱ ገልጫለሁ። የኔታ ጎዳና ያዕቆብም ቆፍጠን ባለ አማርኛ ትግራይን የማበልፀግ ጦርነት ሲሉ ዕይታቸውን አጋርተዋል። ከሰሞናቱ አጤ አብይ ደግሞ ብልፅግናን ቢቀላቀሉ ይህ አይሆንም ነበር ሲሉ ውስጥ ዕቃውን የሂደቱን ዘረጋግፈውታል። አያችሁ መደማመጥ ቢኖር ያለ አቅም የምናፈሰውን አቅም አደራጅተን በሃሳብ የመሞገት፣ የማደራጀት ተቋማዊ ትግል መጀመር ይቻል ነበር። እኔ በግል ካልሆነ በድርጅት ደረጃ ከአጤ አብይ መዳፍ ውጪ የሆነ ድርጅት ስል ባጅቻለሁ። የሆነው የግርዶሽ ማርገጃ ነው። ለዕውቅናው በስውርም በግልፅ ተሆነ። መጪው ጊዜ ከባጀው ይከብዳል። ውኃ ያዘለ ተራራ ነው። በተለይ ለአማራ። የሆቴል እዬተከፈላቸው ከአውስትራልያ፣ ከስሜን አሜሪካ፣ ከአውሮፓ ሽርሽር ላይ የባጁት የሞጋሳ ምርኮኞች ከእንግዲህ አፍንጫህን ላስን ይጠብቁ። እንደ አሮጌ አካፋ እና ዶማ ይወረወራሉ። የጨበራ ተዝክሩ በኦነግ አሸናፊነት ተደምድሟል። ስልቡም ተሰልቦም፣ ተሰልስሎም ደመነፍሱን ይወዛወዛል። አዲስዬም አዲሱን ዘመናዊ የሉባውያን መረገጥን ታሽሞንሙን። የገዳዋ የምርጫ ቦርድ ልዕልትም ከአማካሪዋ ጋር ደረብ ካለ የዶላር ጉርሻ ጋር መፎረሽ ነው። ድል በድል¡ ኢትዮጵያን ክዶ ኦሮማይዜሽን ነገሰ። አቶ ያሬድ ጥበቡ ከኤርትራዊው ጋዜጠኛ ከአቶ ሰናይ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቦንብ የ...